ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ የአቡዳቢ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራልን የአገልግሎት ፈቃድ ሰነድ ተረከቡ።
ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስም የኢሜሬትስ መንግሥት ላደረጉት በጎነት ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ኢሜሬትስ የነጻነት ምድር፣ የሰላም ሀገር፣ የእስልምና አማናዊ መልክ፣ የስደተኞች ማረፊያ፣ እድገት ከባህል፣ ሥልጣኔ ከሞራል ጋር የተባበሩባት ናት ብለዋል። ወደ ፊት በሚኖረው ፍላጎትም ዙሪያ እገዛቸውን ጠይቀዋል።