የቦታው ስም ቀራንዮ ነው

የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ

ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡ አስታወቀ።

ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት አቅርቧል። ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ ያገኘው ጠቅላላ ገቢ ካለፈው 2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ18,562,565.21 ብር […]

የወልዳ ዱካ ቡኦታና ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት ከኦሮሚያ ክልል በክረምት ወራት የሚያሠለጥኗቸውን መምህራን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚሠሩትን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንና ሙዚየሙን ጎበኙ፡፡

አዲስአበባ -ኢትዮጵያ የወልዳ ዱካ ቡኦታና ወልዳ ሥላሴ ጠቅላላ ማኅበራት በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ድጋፍ ከኦሮሚያ ክልል በክረምት ወራት የሚያሠለጥኗቸውን መምህራን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሚሠሩትን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችንና ሙዚየሙን ጎበኙ፡፡ ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ […]

አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ ከተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ተከትሎ ከሀገረ ስብከቱ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረሰ የተከሰቱትን ችግሮች ማለትም ሕገ- ወጥ ቅጥር፣ዕድገት ፣ዝውውር፣ሕገ- ወጥ የፋይናንስ አሰራሮችና የገንዘብ ዝውውሮች፣ ሕገ -ወጥ የቦታና የቤት ኪራይ ውሎችን ሕገ- ወጥ ተደራራቢ ሥራዎችን ወዘተ …በዝርዝር በማጥናት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር የሚያቀርብ ኮሚቴ በመሰየም ወደ […]

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” (ዮሐ.14፥15)፤ […]

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያስገነባው 1B+G+8 ሕንጻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ ተመረቀ።

ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከበኲረ ምእመናን ከበደ ተካልኝ በስጦታ ባገኘው በ22 ማዞሪያ ጎላጎል ሕንጻ አጠገብ ያስገነባው B+G+8 ሕንጻ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቡራኬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ። በሕንጻው ምርቃት ብፁዕ […]

የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መ/ዮንቨርሲቲ ተካሔደ።

ሐምሌ፳፩ ቀን፳፻፲ወ፰ ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የአህጉረ ስብከቶች ሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህራን የአሰልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እያከናወነ ይገኛል ። በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር […]

በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራው የቤተክርስቲያን ልዑክ ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤልን በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱሰ ገብርኤል ገዳም አክብሮ በሰላም ተመልሷል።

ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ -ኢትዮጵያ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤልን በዓል በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓት በማክበር በሰላም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ተመልሷል። […]

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታንያ አምባሳደር እና በአፍሪካ ኅብረት የቋሚ መልእክተኛ ክቡር ዳረን ዌልችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታንያ አምባሳደር እና በአፍሪካ ኅብረት የቋሚ መልእክተኛ ክቡር ዳረን ዌልችን (HE Darren Welch | UK Ambassador to Ethiopia & Permanent Representative to the African Union) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። አምባሳደር ዳረን […]

“ለቅኖች ምስጋና ይገባል። “መዝ 32፥1

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜ ማለትም በታኅሣሥ እና በሐምሌ 19 ቀናት የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ለማክበር ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሚጓዙ መሆኑ ይታወቃል። ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በሚያደርጉት በዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ በድሬዳዋ ከተማ የሚደረግላቸው አቀባበል እጅግ ደማቅ ሲሆን በተለይም ከቅርብ […]

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም ሀዋሳ – ኢትዮጵያ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ያዳነበትን ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚዘክረው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግሥ በሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአባቶች፣ በመንግሥት ኃላፊዎችና ከመላው ኢትዮጵያ በተሰበሰቡ በርካታ ምዕመናን በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከትና […]

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ

የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ልማት በቤተ ክርስቲያን

ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል የቴሌግራም ቻነል