የቦታው ስም ቀራንዮ ነው

የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ

ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም መንፈሳዊ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

ሐምሌ ፲፩ ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓ.ም በርካታ እውቅ ሊቃውንትን ያፈራውና በታሪክ ታላቅ ስፍራ ያለው የጥንታዊው የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም የመምህራንና ቀሳውስት ማሠልጠኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ያስተማራቸውን ደቀመዛሙርት የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በአሁኑ ሰዓት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ ታላቅ መርሐ-ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ […]

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለመንበረ ፓትርያርክና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዘመናዊ ኮምፒውተር በስጦታ አበረከተ።

ሐምሌ ፲ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ሰባት ደራጃቸውን የጠበቁ ኮምፒወተሮች በስጦታ አበርክተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው እንደተናገሩት መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ልዩ ልዩ ሥራዎች እየተሠሩ በመሆኑ ለዚያ የሚያግዙ አምስት ኮምፒውተሮች፣ለቅዱስ ሲኖዶስ ሁለት ኮምፒውተር በአጠቃላይ ሰባት ኮምፒውተሮች በስጦታ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ […]

የቤተክርስቲያንን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት በዘመናዊ መንገድ ለማጠናከር የሚያስችል የምክክርና የሥልጠና መርሐ ግብር የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሔደ።

ሐምሌ ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.፣ አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አዘጋጅነት ለአህጎረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በተዘጋጀው የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ላይ «የቤተ ክርስቲያን ትርክት» በሚል ርዕስ ልዩ ሥልጠና ተሰጠ። ሥልጠናው በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል በሐምሌ ፱ እና ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. በተካሄደው የሁለት ቀን መርሐ ግብር […]

የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተገነባ ያለውን ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የግንባታ ሂደትን ጎበኙ።

ሐምሌ ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.| ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ “የሕዝብ ግንኙነት ስኬት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል ለአገር አቀፍ የአህጉረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች የተዘጋጀው ፫ኛው ዙር ሥልጠና በዛሬው ዕለትም ተሰጥቶ የዋለ ሲሆን፤ ሠልጣኞቹ የዕለቱን መርሐ ግብር ካጠናቀቁ በኋላ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ሁለገብ ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽን የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል። ይህ […]

የቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሥልጠና በአሰልጣኞች ማጠቃለያ ሁለተኛ ቀኑን አጠናቀቀ

(ሐምሌ ፲ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም.፤ አዲስ አበባ)፦ “የሕዝብ ግንኙነት ስኬት ለቤተክርስቲያን አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል የተዘጋጀው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሥልጠና ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዞ ውሏል። በኢኦተቤክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በተዘጋጀው በዚህ ሀገር አቀፍ መድረክ ላይ በትላንትናው ዕለት (ሐምሌ ፱ ቀን) በምሁራን አማካኝነት ዋና ዋና የሙያ ትምህርቶች ተሰጥተው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ በሁለተኛው ቀን […]

“እረኛ ከሌለ በጎቹ ለአራዊት ይዳረጋሉ፤ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እውነትን ይዛችሁ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቁ” ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ

ሐምሌ ፱ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም.| ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል በጠዋቱ የክረምት አየር ውስጥ የቤተ ክርስቲያንን ድምፅ የሚያስተጋቡ ሙያተኞችን አስተናግዷል። መድረኩ “የሕዝብ ግንኙነት ስኬት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት” በሚል ታላቅ ዓላማ የተዘጋጀ የሥልጠና መድረክ ነበር። በዚህ ጉባኤ ላይ አዳራሹን ፀጥታ ያሰፈነ፣ የባለሙያዎችን ልብ ያነቃቃና የቀጣይ ጉዟቸውን አቅጣጫ የቀየረ አንድ አባታዊ ድምፅ ተሰማ። እርሱም የቅዱስ ሲኖዶስ […]

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ባዘጋጀው የሥልጠናና የምክክር መርሐ ግብር ላይ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፦

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱሶ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅትና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ፤ ክቡራን የጠቅላይ ቤተክሆነት ኃላፊዎች፤ የዚህ ታሪካዊ ሥልጠና ተሳታፊዎች፤ ክቡራንና ክቡራት፤ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴ 5:16 ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለዘመናት የዕውቀት ምንጭ፣ […]

በአህጉረ ስብከትና በማዕከል መካከል የተናበበ የሕዝብ ግንኙነት መዋቅር ለመፍጠር የሚያስችል ስልጠና መሰጠት ጀመረ”

ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.| ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመረጃ ፍሰትን ተቋማዊና ዘመናዊ ቅርጽ ለማስያዝ ያለመው ፫ኛው ዙር አገር አቀፍ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች የሥልጠናና የምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት በጁፒተር ሆቴል በይፋ ተጀምሯል። ሥልጠናውን በይፋ የከፈቱት የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ድምፅ ይበልጥ ተደራሽና […]

የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ያስገነባው መንበረ ጵጵስና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተመረቀ።

ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት አዲስ መንበረ ጵጵስና ሠርቶ መንበረ ጵጵስናው በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ በብፁዕ አቡነ ቄርሎስና በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ቡራኬ አስመርቋል። ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ አባታዊ መልእክት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው መንበረ ጵጵስና በ1940ዎቹ […]

እናንተ የነገዋ ቤተክርስቲያን ተስፋዎች ናችሁ:- ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬ 11 ደቀመዛሙርት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተመረቁ።

ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የከምባታ ሀላባና ጠምባሮ ሀገረ ስብከት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በአብነት ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 11 ደቀመዛሙርት በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ በታላቅ ድምቀት ተመርቀዋል። በሀገረ ስብከቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ይህ የምረቃ መርሐ ግብር የቤተክርስቲያንን መንፈሳዊ የትምህርት ጥራትና የሰው ኃይል ግንባታ ወደ ላቀ ደረጃ […]

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ

የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ልማት በቤተ ክርስቲያን

ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል የቴሌግራም ቻነል