የቦታው ስም ቀራንዮ ነው
የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
የ40 ሀገራት አምባሳደሮች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ቅዱስ ላሊበላ ከተማ መግባታቸው ይታወቃል። በዚህ ጉብኝት ከ800 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩትን ውቅር አብያተክርስቲያናት ድንቅ የታሪክና የጥበብ ሥራዎች ከመመልከት ባለፈ፣ ከቤተክርስቲያን አባቶችና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ውይይት ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል። እንደ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ዘገባ ከሆነ ከ”ዘላቂ ላሊበላ ፕሮጀክት” ተወካዮች እንዲሁም ከፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር በመሆን ቅርሶቹን […]
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና ዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ በዘመናዊ የዲጂታል ዓለም ውስጥ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ተደራሽ ማድረግ የምትችልባቸውንና አስተዳደራዊ አቅሟን ለማሳደግ የሚረዱ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦችንና ስልታዊ ጥናቶችን በማቅረብ እንዲሠራ የተቋቋመ ኮሚቴ ነው፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ ዮሐንስ ተስፋዬ ለአስተዳደር ጉባኤ ባቀረቡት ጥናት “ቤተክርስቲያን በቴክኖሎጂ የዳበረ […]
የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በመርሐግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ልማትና ተራድኦ ኮሚሽን እና የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የበላይ ሊቀ ጳጳስ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ኃላፊ እና የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅች ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የድርጅቱ ልዩ ልዩ ኃላፊዎች […]
“ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
(ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ) አንጋፋውና ታሪካዊው የባቱ (ዝዋይ) ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ በሥራ አመራር የዲፕሎማ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 23 ደቀ መዛሙርት እንዲሁም በ67ኛው ዙር የሦስት ወራት የካህናት ማሠልጠኛ ክፍል የተከታተሉ 36 ዕጩ አገልጋዮችን በድምሩ 59 ተተኪ መምህራንንና አገልጋዮችን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። ይህ ታላቅ […]
የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛውን ዙር የነገረ መለኮት ደቀ መዛሙርት በታላቅ ድምቀት አስመረቀ።
ሰኔ ፳ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሣልሳይ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመሠረተው የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በነገረ መለኮት ትምህርት ዘርፍ ሲያስተምራቸው የነበሩ የሁለተኛ ዙር ደቀ መዛሙርት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። የሀገርና የቅድስት ቤተክርስቲያን ተተኪ አገልጋዮችንና ምሁራንን በማፍራት ላይ የሚገኘው የዚህ ኮሌጅ ታሪካዊ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በከፍተኛ መንፈሳዊ […]
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀት እና ለማጠናከር ያዘጋጀውን አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት አቀረበ።
ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የውይይት መርሐግብር ላይ፤ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ ኣፈ መምህር ኣባ ገብረ ሥላሴ በመንበረ […]
የአንድ ክፍለ ዘመን ጽናትን በታላቅ የወንጌል ፍሬ የመለሰው የጅማ ሀገረ ስብከት 81 ወገኖችን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መለሰ
ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም| ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በጅማ ሀገረ ስብከት፣ በኖኖ ቤንጃ ወረዳ በአልጋ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በታላቅ ድል ተጠናቀቀ። በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ቀደም ሲል የተለያዩ እምነቶችን ይከተሉ የነበሩ 81 ወገኖች ወደ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመመለስ የሥላሴን ልጅነት (የክርስትና ጥምቀትን) ማግኘታቸውን የሀገረ ስብከቱ […]
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
ሰኔ 9ቀን 2018 ዓ.ም /ቁልቢ/ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅና የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሕንጻ […]
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ-ኢትዮጵያ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ ለመመልከት ዛሬ ማለዳ ወደ ድሬዳዋ […]
ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
ሰኔ 6/10/2018 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፣በግንቦት 2018 ዓ በተካሔደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቄለም ወለጋን ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ መወሰኑ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ብፁዕነታቸው ይህንኑ ኃላፊነት ለመረከብ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ደቢዶሎ ከተማ ሲያቀኑ፣በከተሣው ነዋሪዎች ምዕመናንና ምዕመናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል […]