የቦታው ስም ቀራንዮ ነው

የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ

ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ያስገነባው መንበረ ጵጵስና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተመረቀ።

ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት አዲስ መንበረ ጵጵስና ሠርቶ መንበረ ጵጵስናው በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ በብፁዕ አቡነ ቄርሎስና በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ቡራኬ አስመርቋል። ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ አባታዊ መልእክት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው መንበረ ጵጵስና በ1940ዎቹ […]

እናንተ የነገዋ ቤተክርስቲያን ተስፋዎች ናችሁ:- ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬ 11 ደቀመዛሙርት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተመረቁ።

ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የከምባታ ሀላባና ጠምባሮ ሀገረ ስብከት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በአብነት ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 11 ደቀመዛሙርት በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ በታላቅ ድምቀት ተመርቀዋል። በሀገረ ስብከቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ይህ የምረቃ መርሐ ግብር የቤተክርስቲያንን መንፈሳዊ የትምህርት ጥራትና የሰው ኃይል ግንባታ ወደ ላቀ ደረጃ […]

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲግሪ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ሊቃውንት በድምቀት አስመረቀ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዕውቀት ማዕከልና የሊቃውንት መፍለቂያ የሆነው አንጋፋው የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ለዓመታት በሐዲሳት፣ በብሉያት፣ በሊቃውንት፣ በመነኮሳትና በነገረ መለኮት (ቲኦሎጂ) ትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 400 ሊቃውንት በዛሬው ዕለት በደመቀ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል። በምረቃት ስነስርዓቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀደማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ብፁዕ […]

የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው ዓመት የፍልሠተ ዓፅም መታሰቢያ በዓል በግል ገንዘባቸው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።

ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ሐምሌ 4 የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለተኛው ፓትርያርክ አጽማቸው በግፍ ተገድለው ከተቀበረበት ቦታ ከ13 ዓመት በኋላ በእርሳቸው መሪነት ወደታነጸው ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በክብር ያረፈበት ዕለት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ፓትርያርክ የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው ዓመት የፍልሠተ ዓፅም መታሰቢያ […]

ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው በዛሬው ዕለት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቁ ።

ሐምሌ 03 ቀን 2018 ዓ/ም በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቅራቢነት እና በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን ሙድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀ […]

የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የውል እድሳት አገልግሎትን በዘመናዊና ቀልጣፋ ሲስተም መስጠት ጀመረ።

ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም |የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት፣ ዘመኑን የዋጀ የዲጂታል አሠራርና የእንግዳ አቀባበል ሥርዓት በመዘርጋት የ፳፻፲፱ ዓ.ም. የደንበኞች ውል እድሳትን በታላቅ እመርታ መጀመሩን ይፋ አደረገ። ድርጅቱ የሚያስተዳድራቸውን የንግድ እና የመኖሪያ ቤት ተከራይ ደንበኞቹን የውል እድሳት አገልግሎት ከሐምሌ ፩ ቀን ጀምሮ በይፋ መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ […]

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የአራቱ ጉባኤያት የምስክር ጉባኤ ቤት 19 ደቀመዛሙርትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት አስመረቀ።

ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባሕርዳር-ኢትዮጵያ በምርቃት መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስካንዲቪያንስ እና የግሪክ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የምስክር ጉባኤ ቤቱ መምህር ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ሓላፊዎች ፣ የምስክር ጉባኤ ቤቶች መምህራን ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን […]

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ለሁለተኛ ዙር አስመረቀ።

ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ‎ሀዋሳ-ኢትዮጵያ ‎በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሽዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣መጋቤ ጥበባት አባ ዘሚካኤል የሲዳማ […]

ላይፍ አዲስ ሆስፒታል ከቤተክርስቲያን ተከራይቶ በዘመናዊ መንገድ የሚያሳድሰውን ሆስፒታል በብፁዓን አባቶች አስጎበኘ።

ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስአበባ -ኢትዮጵያ የላይፍ አዲስ ሆስፒታል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የተከራየውን ሕንጻና የሕክምና ተቋም አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማዘመንና ዓለም አቀፍ መሥፈርቶችን ወደሚያሟላ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር የጀመረውን ሰፊ የእድሳትና የማስፋፊያ ሥራ አሁናዊ አፈጻጸም ለመገምገም የሚያስችል የሱፐርቪዥን ጉብኝት ተካሂዷል። በዚህ መርሐ-ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ […]

የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።

ሰኔ ፲፱ቀን ፳፲፰ ዓ.ም የገዳሙ ጉባኤ ቤት “ሰንፔር” ሲል ለሰየመው “የሕክምና መንደር” ግንባታ 30,000 ካሬ ቦታ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሰኔ ፲፱ቀን ፳፲፰ ዓ.ም መረከቡም ይታወቃል። “የሕክምና መንደሩ” የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐ ግብር ላይ እንደተገለፀው የሕክምና መንደሩ ዋና ዓላማ ለሁሉም የሰው ልጆች በምሕረት፡ እምነትን፣ ዘርንና ማንነትን ሳይለይ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ የሚታዘንበት የምሕረት ማረፊያ እንዲሆንና ሁለንተናዊ […]

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ

የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ልማት በቤተ ክርስቲያን

ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል የቴሌግራም ቻነል