የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው ዓመት የፍልሠተ ዓፅም መታሰቢያ በዓል በግል ገንዘባቸው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።

July 11, 2026
ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
ሐምሌ 4 የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለተኛው ፓትርያርክ አጽማቸው በግፍ ተገድለው ከተቀበረበት ቦታ ከ13 ዓመት በኋላ በእርሳቸው መሪነት ወደታነጸው ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በክብር ያረፈበት ዕለት ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ፓትርያርክ የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው ዓመት
የፍልሠተ ዓፅም መታሰቢያ በዓል፣ በአዲስ አበባ በሚገኘው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ኃይለኢየሱስ ተመስገን ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል አስተዳዳሪ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ አገልጋይ ካህናትና በርካታ ምዕመናን
በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የቤተ ክርስቲያንን ነፃነት፣ መብትና ቀኖና ለማስጠበቅ ባሳዩት የማይናወጥ ጽናት ምክንያት በወቅቱ
በነበረው የደርግ ሥርዓት በ1968 ዓ.ም ለእስራት ተዳርገው፣ በ1971 ዓ.ም በግፍ ታንቀው ሰማዕትነትን የተቀበሉ ታላቅ የቤተ
ክርስቲያን አባት ናቸው።
የቅዱስነታቸው አስከሬን በወቅቱ በድብቅ ተቀብሮ ከቆየ በኋላ፣ የደርግ ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ በ1984 ዓ.ም በክብር ተቆፍሮ ወጥቶ (ፍልሠተ ዓፅም ተደርጎ) በአሁኑ ማረፊያቸው በሆነው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እንዲያርፍ ተደርጓል።
ይህን ታሪካዊና መንፈሳዊ ኩነት ለመዘከር ዛሬ እየተካሄደ ባለው መርሐ ግብር ላይ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙበት የጸሎትና የምሥጋና መርሐ ግብር ተከናውኗል። በተጨማሪም የሰማዕቱ ፓትርያርክ ለቤተ
ክርስቲያንና ለሀገር ያበረከቱት ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ትምህርታዊ አስተዋፅኦ እንዲሁም ስለ ሃይማኖታቸውና ስለ
መንጋቸው የከፈሉት ታላቅ መሥዋዕትነት በመዘከር ላይ ይገኛል።
የመታሰቢያ በዓሉን ሙሉ ሥነ ሥርዓት፣ የተላለፉትን አባታዊ መልእክቶችና ዝርዝር ዘገባዎችን በቀጣይ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።©EOTC t.v
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000031.jpeg 336 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-11 09:24:022026-07-11 09:24:02የሰማዕቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የ34ኛው ዓመት የፍልሠተ ዓፅም መታሰቢያ በዓል በግል ገንዘባቸው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።
Search Search

Recent Posts

  • ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
  • “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው በዛሬው ዕለት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቁ ። Link to: ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው በዛሬው ዕለት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቁ ። ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች... Link to: የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲግሪ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ሊቃውንት በድምቀት አስመረቀ Link to: የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲግሪ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ሊቃውንት በድምቀት አስመረቀ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top