ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
መስከረም ፭ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ምዓባይ ባንክ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ ሶስት መቶ ሺ ብር የሚያወጣ ከአራት ሺ በላይ ደብተር በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረገ ።
አቶ አሰፋ ተፈራ የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት ፣አቶ ማርቆስ ደመቀ የባንኩ የሀብት ማሰባበሰብ መምሪያ ዳይሬክተር፣ አቶ አሰግደው ሽመልስ የማርኬቲንግ መምሪያ ዳይሬክተር ፣ አቶ አበጀ ተስፋ የአራት ኪሎ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ እና ሌሎች የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ተገኝተው ስጦታውን የበረከቱ ሲሆን አቶ አሰግደው ሽመልስ የባንኩ የማርኬቲንግ መምሪያ ዳይሬክተር ባንኩ ቅድስት ቤተክርስቲያን በምታካሂዳቸው የልማት እንቅስቃሴዎች ቀዳሚ የድጋፍ አጋር በመሆን እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
አክለውም በብፁዕነታቸው አማካኝነት በሸገር ከተማ የተገነቡት ትምህርት ቤቶችም የትውልድ ግንባታ አካል በመሆናቸው ባንኩ አጋርነቱን ማሳየቱን ገልጸዋል።
በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ድጋፉን ተረክበው በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ልጆች ከት /ቤት እንዳይቀሩ ዓባይ ባንክ የበኩሉን ድርሻ በመወጣቱ አመስግነዋል።
ወገንን መርዳት ቀዳሚነው በማለት ልጆች እውቀትን የሚያገኙበትን መንገድ መደገፍ ደግሞ ከሁሉ የሚበልጥ ተግባር መሆኑንም ገልፀዋል። ብፁዕነታቸው ዘመኑ የበረከት እንዲሆንም በመመኘት አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/