የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።

September 16, 2026
መስከረም ፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፱ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የመማር መስተማር ተግባሩን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርርክ ጠቅላይ ቤተክህነታ ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት መስከረም ፭ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም በይፋ አስጀመረ።
የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም አስተዳዳሪ መጋቤ ኅሩያን ቆሞስ አባ ኤልያስ በልሁ ለብፁዓን አባቶች የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን፣የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት ከተመሠረተ ዘንድሮ በ፳፻፲፱ ዓ.ም 53ኛ ዓመቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መጋቤ ኅሩያን አያይዘውም በወቅቱ የነበሩ አባቶች ትምህርት ቤት እንዲከፈት ያደረጉበት ሦስት ምክንያቶች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ “የመጀመሪያው ተማሪዎች መንፈሳዊውን ከዘመናዊ ትምህርት ጋር አጣምረው እንዲማሩ ለራሳቸው፣ ለወገኖቻቸው ለሀገር ለቤተክርስቲያን ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ታስቦ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ከርእሰ መምህሩ ጀምሮ እስከ ታች ያሉ ልዩ ልዩ ሠራተኞች በሙያቸው ሠርተው ደመወዝ እንዲያገኙ ሲሆን፤ በሦስተኛ ደረጃ ገዳሙ በመጠኑም ቢሆን ገቢ ያገኛል ተብሎ ታስቦ ነው” ሲሉ አስረድተዋል፡፡ የዛሬ 53 ዓመት ሲመሠረት በ39 ተማሪዎች፣ በ3 መምህራን፣ በ3 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የተመሠረተው ትምህርት ቤታችን በአሁኑ ሰዓት ከሦስት ሺሕ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የ፳፻፲፰ ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደትና አጠቃላይ የትምህርት ቤቱ የሥራ ክንውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ወርቁ አሸናፊ አቅርበዋል፡፡ ርእሰ መምክሩ አንዳብራሩት “ትምህርት ለሰው ልጅ የተሻለ ኑሮ ለመኖር በሚያደርገው ጥራት የተፈጥሮንና ሰብዓዊ ሀብትን የበለጠ ለማወቅና ለኑሮው ለማመቻቸት የሚስፈልገው ችሎታና አመለካከት ምንጭ ሲሆን ይኸው የሚሰናዳበት ደግሞ ት/ቤት ነው፡፡ አገር ያለመችውን ራዕይ ዕውን ሊያደርግ የሚችለው ወጣቱ የተሟላ ዕውቀት ለራሱ፣ ለወገንና ለሰው ልጅ በጎ አመለካከትና ችሎታ ያለው መሆኑ መረጋገጥ ሲችል ነው፡፡” ብለዋል፡፡ አያይዘውም “ይህንን የአገር፣ የቤተክርስቲያንና፣ የወላጆችን አደራ ለመወጣት የትምህርት ቤታችን ማኅበረሰብ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የገዳማችን አስተዳደርና አጋር አካላት ድጋፍ፣ እገዛና ማበረታታት የተነሣ በዘመኑ ከፍተኛ የሥራ ውጤት ያስመዘገብንበት ሆኖ አልፏል፡፡” ሲሉ በሪፖርታቸው አብራርተዋል፡፡
አቶ ወርቁ ትምህርት ቤቱ አሁን ያለበትን ደረጃ በማወቅና ለረጅም ጊዜ ለማቀድ የሦስት ዓመት (2018 – 2020 ዓ.ም) ዝርዝር ተግባራት የያዘ ስትራቴጂክ ዕቅድ በማቀድና ከዚህ ውስጥም የ፳፻፲፰ ዓ.ም የትምህርት ቤት መሻሻል ዕቅድ በማውጣት ሥራውን በማካሄድ አሳልፏል በማለት በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡
የተማሪዎችን ሁለንተናዊ ብቃት ለማሳደግ ትምህርት ቤቱ በትኩረት እየሠራ መሆኑን የገለጹት ርእሰ መምህሩ የተማሪዎችን የአካዳሚክ ውጤት ከማሳደግ አንጻርም 6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በ፳፻፲፯ ዓ.ም 99.7 ፐርሰንት ከነበረው በ2018 ዓ.ም 100 ፐርሰንት አድጓል፤ 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በ፳፻፲፯ ዓ.ም ከነበረው 97.6 ፐርሰንት በ2018 ዓ.ም 100 ፐርሰንት፤ 12ኛ ክፍል ዩኒቨርሲቲ መግቢያ በ፳፻፲፯ ዓ.ም 57.5 ፐርሰንት ከነበረው በ፳፻፲፰ ዓ.ም 86 ፐርሰንት (21 ፐርሰንት) ብልጫ አስመዝግቧል፡፡
“ተማሪዎችን በዕውቀትና በሥነ ምግባር አስተምህሮ ማሳደጉ ይህንን ባለብዙ ፈርጅ ያለበትን ፍላጎት ከግብ ለማድረስ ነው፡፡ በተለይም እንደኛ ያለ ከ3‚070 ተማሪዎችና ከ250 በላይ ሠራተኞችን በመያዝ በጥቂት የአመራር አካላት ውጤቶችን ማሳከላት የሚወስደው የጊዜ፣ የጉልበትና ራስን የመስጠት ጉዳይ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ ያሉት ርእሰ መምህሩ ለዚህ ሁሉ ብርታትና ጉልበተው የሆነን ብፁዕ አባታችን በሁለንተናዊ መልኩ የሚሰጡን ማበረታቻና ድጋፍ የገዳማችን አስተዳደር ሙያችንን በተማርነውና ባወቅነው ልክ እንድንሠራ የሚያደርግልን ድጋፍ ወላጆች በእኛ ላይ ያላቸው እምነትና ለምንጠይቀው ሁሉ ለመደገፍ የሚያሳዩት መነሣሣትና የሙያችን የሕዝባችን አደራ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ ሠርተን የተፈለገውን ዓላማ ለማሳካት እንድንችል የአባቶቻችን ጸሎትና ድጋፍ፣ የወላጆች የዕለት ተዕለት ክትትልና ማበረታታት እንዳይለየን በታላቅ አከብሮት እጠይቃለሁ፡፡” ሲሉ መልእክታቸውን አጠቃለዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ “ከ፳፻፲፰ ዓ.ም ዘመነ ማርቆስ ወደ ፳፻፲፱ ዓ.ም ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገራችሁ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡” ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አክለውም “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘመናት ታሪክ የትምህርትና የዕውቀት ሀብት ባለቤት ናት፡፡ ይህን መንፈሳዊ ሀብት ለመጠበቅ እንደ ምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የመሳሰሉ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ትውልድን የመጠበቅ አደራ እየተወጣች ትገኛለች፡፡” ብለዋል፡፡ ቤተክርስቲያን በዚህ ተቋሟ ውስጥ ዓላማዋ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሰውን የሚያከብሩ በዕውቀተው የተሞሉ፣ በሥነ ምግባር የታነጹ፣ ሃይማኖት ያላቸው ለሀገርና ለወገን የሚጠቅሙ ልጆችን ማፍራት ነው፡፡” ሲሉም የትምህርት ቤቱን ዓላማ አብራርተዋል፡፡ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ቡሁለንተናዊ ሕይወታቸው ከቤተክርስቲያናቸው የራቁ እንዳይሆኑ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
የምስካየ ኅዙናን ት/ቤት ማኅበረሰብ በሙሉ ትምህርት ቤታችን ኢትዮጵያዊና ኦርቶዶክሳዊ ዕሴትን በመጠበቅ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ተቋማት መካከል አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም ባሳለፍናቸው የታሪክ ምዕራፎች ውስጥ በርካታ ዜጎች ተምረውበት ለከፍተኛ ማዕረግ በቅተውበታል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙኀኑ በመልካም ስሙ ያወሱታል፡፡ ስለዚህ ጠቢቡ ሰሎሞን ምሳሌ ፯፥፩ መልካም ስም ከመልካም ሽቱ ይበልጣል እንዳለው በመልካም ሥራ የተገኘ መልካም ስማችንን በጋራ እንድንጠብቅ አደራ እላለሁ፡፡ ትምህርት ቤታችን በቀጣይ የተሻሉ ተግባራት በማከናወን ተውልድን የበለጠ ለመቅረጽ እየሠራ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ሁሉንም ወገን ሁሉን አቀፍ ትብብር እየጠየቅን አዲሱን የትምህርት ዘመን እግዚአብሔር አምላካችን ውጤታማ የሥራ ዘመን ያድርግልን ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርዊ ተልዕኮ መምሪያ ባስተላለፉት መልእክት ትምህርት የሰው ሁለተኛ መፈጠረያው ነው፡፡ ሙሉ ሰው የሚኮነው በትምህርት ነው፡፡ ወላጆችና መምህራን ትልቅ ኃላፊነት አለባችሁ፡፡ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የ፳፻፲፰ ዓ.ም በ 6ኛ፣ በ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሰርተፍኬት ሽልማት ተሰጥቷል። ከ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ላመጣው ተማሪ የወርቅ ሜዳሊያ ተበርክቶለታል፡፡ የላቀ የሥራ አፈጻጸም ላሳዩ የትምህርት ክፍሎች መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የማበረታቻ የሽልማት መርሐ ግብር በብፁዓን አባቶች ተከናውኗል።
በተያያዘ ዜናም ለአራት ዓመታት በላይ በገዳሙ የአብነት ትምህርት ቤት ሥር በሚገኘው የቅዳሴ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መምህራን በብፁዓን አባቶች ተመርቀዋል።©Eotc tv
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/100002.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-16 06:46:252026-09-16 06:46:25የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
Search Search

Recent Posts

  • ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ።
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
  • “በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ። Link to: የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ርእሰ ዓውደ ዓመት በማስመልከት ከቅዱስነታቸው ቡራኬና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ... Link to: ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ። Link to: ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ የደብተር ድጋፍ አደረገ። ዓባይ ባንክ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top