በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት «ቅድሚያ
ለወንጌል» በሚል መሪ ቃል ሲሰጥ የነበረው የሥልጠና መርሐ ግብር በተሳታፊዎች የጋራ የአቋም መግለጫና በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኃላፊ መምህር ሰለሞን በቀለ ፤ መመሪያ ማጠቃለያ ተጠናቋል።
ከነሐሴ 25 እስከ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሦስት ቀናት በቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሲካሄድ በቆየው በዚህ ሥልጠና ላይ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ዋና ጸሐፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞች፣ ቁጥጥርና ገንዘብ ያዦች፣ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች፣ የወጣት ማኅበራት ተወካዮች፣ እንዲሁም ብዙ ንስሐ ልጆች ያሏቸው ካህናትና ሰባክያነ ወንጌል በሥልጠናው ተሳትፈዋል።
የሥልጠናው ተሳታፊ የሆኑት ሰባክያነ ወንጌል በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ባወጡት ባለ 12 ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ መርሐ
ግብሩን ላዘጋጀው ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነትና ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ዕዝራ ንዋይ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ መሰል አቅምን የሚገነቡ ሥልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረውና በተከታታይነት እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። አገልጋዮቹ በአብያተ ክርስቲያናትና በገዳማት የተሰጣቸውን
አደራ መሠረት በማድረግ በተሻለ ትጋት፣ ቅንነትና ትሕትና ለማገልገልና በሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር ለመለወጥ ቃል
የገቡ ሲሆን፣ ስብከተ ወንጌል የቤተክርስቲያን ቀዳሚና ዋና ዓላማ መሆኑን በመገንዘብ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤዎችና የበላይ
ኃላፊዎች ለወንጌል አገልግሎት ተገቢውን ትኩረትና ክብር እንዲሰጡ እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ አሳስበዋል።
በተጨማሪም በሰዓት አጠቃቀም ዙሪያ የሚታዩ አለመናበቦችን በመቅረፍ በተለይ በሰንበት ቀናትና በበዓላት ለስብከተ ወንጌል በቂ ጊዜ
እንዲመደብና ሰባክያነ ወንጌል ያለአግባብ ጣልቃ ገብነት አገልግሎታቸውን በሥርዓት እንዲያከናውኑ አስገዳጅ መመሪያ እንዲሰጥ
የጠየቁት ተሳታፊዎቹ፣ በአንዳንድ አጥቢያዎች ለስብከተ ወንጌል የሚመደበው በጀት እጅግ አነስተኛ መሆኑን በመጠቆም በጀቱ
ከአገልግሎቱ ስፋትና አስፈላጊነት ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ ተፈትሾ እንዲስተካከል ጠይቀዋል። በተመሳሳይም የተመደቡ አገልጋዮች የሙያ ብቃት፣ የዕውቀት ዝግጁነትና የአገልግሎት ተነሳሽነት ተፈትሾ አስፈላጊው የማሻሻያና የማብቃት እርምጃዎች እንዲወሰዱ አጽንዖት ሰጥተዋል። በዘመኑ ስብከተ ወንጌልን ለማጠናከር ማኅበራዊ ሚዲያና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በአግባቡና በጥንቃቄ በመጠቀም ከቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሳይወጡ ምዕመናንን ለማገልገልና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለማዳረስ ቃል ገብተዋል።
በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ሰለሞን በቀለ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፣ ራስን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር ጽሕፈት ቤቶችን በማደራጀት የሕዝበ ክርስቲያኑንና የአገልጋዩን ሁኔታ ለመፈተሽ መሰል ሥልጠናዎችና የልምድ ልውውጦች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸው፣ መርሐ ግብሩን ግንባር ቀደም ሆኖ ላዘጋጀው የአቃቂ ቃልቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዋና ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም፣ የሀገረ ስብከቱ ትምህርትና ሥልጠና ክፍል በአዲስ መልኩ በ2019
ዓ.ም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን አቅዶ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጀመረውን መልካም ተሞክሮ በማሳደግ በመላው ስምንቱ ክፍላተ
ከተማ ሰፊ ሥልጠናዎችን ለማዘጋጀት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል።
አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተም አስተዳዳሪዎች ሠራተኞችን ያላግባብ ከማገድ፣ ከማባረርና ከደረጃ ዝቅ ከማድረግ ተቆጥበው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዕርቅን፣ ሥልጠናንና መግባባትን እንዲያስቀድሙ አሳስበዋል።
በአስተዳደር ክፍተቶች ምክንያት አገልጋዮችና
ቤተሰቦቻቸው ለችግር እንዳይዳረጉ ክፍተቶችን በጋራና በፍትሐዊነት ማረም እንደሚገባ አስገንዝበው፣ “የእያንዳንዱ ደብር አስተዳዳሪ
የብቃት መለኪያ ሊሆን የሚችለው በደብሩ ያለውን ካህን እዚያው አሰልጥኖ፣ አስተምሮና አቅፎ ማኖር ሲችል ነው፤ ያኔ ነው ሥልጠናው
ውጤታማ ሆነ የሚባለው” በማለት አስተዳደራዊና መንፈሳዊ መመሪያ ሰጥተዋል።
መርሐ ግብሩ «ቅድሚያ ለወንጌል» የሚለው መሪ ቃል በተግባር፣ በእቅድ፣ በበጀትና በጊዜ አጠቃቀም በመተግበር በጋራ ለመሥራት በመስማማት በጸሎት ተጠናቋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት «ቅድሚያ ለወንጌል» በሚል መሪ ቃል ሲሰጥ የነበረው የሥልጠና መርሐ ግብር በተሳታፊዎች የጋራ የአቋም መግለጫና በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኃላፊ መምህር ሰለሞን በቀለ ፤ መመሪያ ማጠቃለያ ተጠናቋል።
ከነሐሴ 25 እስከ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሦስት ቀናት በቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሲካሄድ በቆየው በዚህ ሥልጠና ላይ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ዋና ጸሐፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞች፣ ቁጥጥርና ገንዘብ ያዦች፣ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች፣ የወጣት ማኅበራት ተወካዮች፣ እንዲሁም ብዙ ንስሐ ልጆች ያሏቸው ካህናትና ሰባክያነ ወንጌል በሥልጠናው ተሳትፈዋል።
የሥልጠናው ተሳታፊ የሆኑት ሰባክያነ ወንጌል በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ባወጡት ባለ 12 ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ መርሐ ግብሩን ላዘጋጀው ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነትና ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ዕዝራ ንዋይ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ መሰል አቅምን የሚገነቡ ሥልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረውና በተከታታይነት እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። አገልጋዮቹ በአብያተ ክርስቲያናትና በገዳማት የተሰጣቸውን
አደራ መሠረት በማድረግ በተሻለ ትጋት፣ ቅንነትና ትሕትና ለማገልገልና በሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር ለመለወጥ ቃል የገቡ ሲሆን፣ ስብከተ ወንጌል የቤተክርስቲያን ቀዳሚና ዋና ዓላማ መሆኑን በመገንዘብ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤዎችና የበላይ
ኃላፊዎች ለወንጌል አገልግሎት ተገቢውን ትኩረትና ክብር እንዲሰጡ እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ አሳስበዋል።
በተጨማሪም በሰዓት አጠቃቀም ዙሪያ የሚታዩ አለመናበቦችን በመቅረፍ በተለይ በሰንበት ቀናትና በበዓላት ለስብከተ ወንጌል በቂ ጊዜ እንዲመደብና ሰባክያነ ወንጌል ያለአግባብ ጣልቃ ገብነት አገልግሎታቸውን በሥርዓት እንዲያከናውኑ አስገዳጅ መመሪያ እንዲሰጥ የጠየቁት ተሳታፊዎቹ፣ በአንዳንድ አጥቢያዎች ለስብከተ ወንጌል የሚመደበው በጀት እጅግ አነስተኛ መሆኑን በመጠቆም በጀቱ
ከአገልግሎቱ ስፋትና አስፈላጊነት ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ ተፈትሾ እንዲስተካከል ጠይቀዋል። በተመሳሳይም የተመደቡ አገልጋዮች የሙያ ብቃት፣ የዕውቀት ዝግጁነትና የአገልግሎት ተነሳሽነት ተፈትሾ አስፈላጊው የማሻሻያና የማብቃት እርምጃዎች እንዲወሰዱ አጽንዖት ሰጥተዋል። በዘመኑ ስብከተ ወንጌልን ለማጠናከር ማኅበራዊ ሚዲያና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በአግባቡና በጥንቃቄ በመጠቀም ከቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሳይወጡ ምዕመናንን ለማገልገልና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለማዳረስ ቃል ገብተዋል።
በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፣ ራስን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር ጽሕፈት ቤቶችን በማደራጀት የሕዝበ ክርስቲያኑንና የአገልጋዩን ሁኔታ ለመፈተሽ መሰል ሥልጠናዎችና የልምድ ልውውጦች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸው፣ መርሐ ግብሩን ግንባር ቀደም ሆኖ ላዘጋጀው የአቃቂ ቃልቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዋና ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም፣ የሀገረ ስብከቱ ትምህርትና ሥልጠና ክፍል በአዲስ መልኩ በ2019 ዓ.ም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን አቅዶ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጀመረውን መልካም ተሞክሮ በማሳደግ በመላው ስምንቱ ክፍላተ
ከተማ ሰፊ ሥልጠናዎችን ለማዘጋጀት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል።
አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተም አስተዳዳሪዎች ሠራተኞችን ያላግባብ ከማገድ፣ ከማባረርና ከደረጃ ዝቅ ከማድረግ ተቆጥበው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዕርቅን፣ ሥልጠናንና መግባባትን እንዲያስቀድሙ አሳስበዋል።
በአስተዳደር ክፍተቶች ምክንያት አገልጋዮችና
ቤተሰቦቻቸው ለችግር እንዳይዳረጉ ክፍተቶችን በጋራና በፍትሐዊነት ማረም እንደሚገባ አስገንዝበው፣ “የእያንዳንዱ ደብር አስተዳዳሪ
የብቃት መለኪያ ሊሆን የሚችለው በደብሩ ያለውን ካህን እዚያው አሰልጥኖ፣ አስተምሮና አቅፎ ማኖር ሲችል ነው፤ ያኔ ነው ሥልጠናው
ውጤታማ ሆነ የሚባለው” በማለት አስተዳደራዊና መንፈሳዊ መመሪያ ሰጥተዋል።
መርሐ ግብሩ «ቅድሚያ ለወንጌል» የሚለው መሪ ቃል በተግባር፣ በእቅድ፣ በበጀትና በጊዜ አጠቃቀም በመተግበር በጋራ ለመሥራት በመስማማት በጸሎት ተጠናቋል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/