የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ::

September 2, 2026
ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም
​የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል አካሂዷል።
​በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክብሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተወካይ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ፤ ብፁዕ አቡነ መልኬጸዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት እና የአቡነ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ፤ ፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች የተለያዩ የቤተክርስቲያን ተወካይ አባቶች ፤ የልዩ ልዩ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች እና ሥራ አስፈጻሚዎች፤ የክልል እና የአዲስ አበባ ተወካዮች፤ የተቋሙ የቦርድ አባላት እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
​መርሐ ግብሩ በሃይማኖት አባቶች የመክፈቻ ጸሎት የተጀመረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የ15 ዓመታት የጉዞ ታሪክ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ቀርቧል።
​በተጨማሪም ጉባኤው ባሳለፋቸው 15 ዓመታት ከጎኑ በመቆም በአህጉራዊ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ፣ በሰብአዊ መብቶች እና በሴቶች ዙሪያ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አብረው ሲያከናውኑ የቆዩ እንደ UNICEF (ዩኒሴፍ) እና ሰተርሊንግ ፋውንዴሽን ያሉ በርካታ ዓለም አቀፍ አጋር ተቋማትና ተወካዮች፣ ወደፊት በሚያከናወኑት አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተልዕኮዎች ላይ ገለጻ በማድረግ የ15 ዓመታት ሰላማዊ የአብሮነት ጉዞን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
​የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፣ ጉባኤው በይፋ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ አባል የሃይማኖት ተቋማት ከመንፈሳዊ አገልግሎታቸው ጎን ለጎን በሀገራዊ የሰላምና የልማት ጉዳዮች ላይ የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ የማቀድ፣ የማስተባበርና የማመቻቸት ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል።
​አክለውም ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሰላምና የመከባበር የጋራ እሴቶች እንዲጠበቁ ሃይማኖታዊ አስተምህሮን መሠረት ያደረጉ የግንዛቤና የአብሮነት ሥራዎች በሀገር አቀፍ፣ በክልልና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ ሲከናወኑ መቆየታቸውንና አሁንም እየተሠሩ መሆኑን አብራርተዋል።
​የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ ኢድሪስ ባስተላለፉት መልእክት፣ በ15 ዓመታት ውስጥ በየደረጃው የተካሄዱ መድረኮች የልዩ ልዩ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የእርስ በእርስ አስተምህሮን እንዲረዱ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።
​ሚኒስትሩ አክለውም እንዲህ ዓይነቱ ጉባኤ የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ፍላጎቶችንን የምናሰፍንበት፣ እምነትን በተግባር የምናጸናበትና የአብሮነትን ታላቅ ቁምነገር የምናሳይበት፣ ባለፉት 15 ዓመታት የሕዝባችንን የሞራልና የስነ-ምግባር እሴቶች ሲቀርጹ የነበሩ የዕድገት ምሳሌዎች መሆናቸውን በመጠቆም፣ በቀጣይም “ለሃይማኖትና ለሀገር የማይሆን ዜጋ እንዳንፈጥር በርትተን ከዘመኑ ጋር በመፍጠን ልንሠራ ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
​በመጨረሻም ለጉባኤው ስኬት የሙያዊና የፋይናንስ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እና በሌሎች የሃይማኖት መሪዎች አማካይነት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000083.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-02 04:09:072026-09-02 04:09:07የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ::
Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ 11ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ፍትሐት ታሰበ። Link to: የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ 11ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ፍትሐት ታሰበ። የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ 11ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ... Link to: በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አይሲቲና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥራ ተጠናክሮ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ። Link to: በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አይሲቲና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥራ ተጠናክሮ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አይሲቲና ዲጂታል ቴክኖሎጂ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top