የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

September 5, 2026
ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓም
ታሪካዊና ጥንታዊው የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም፣ የቤተ ክርስቲያናችንን የትምህርትና የመንፈሳዊ ሀብት መሠረት የሆነውን የአብነት ትምህርት ቤት ዘመናዊ ሕንጻ ለመገንባት የሚያስችል ታላቅ ሀገራዊና መንፈሳዊ ጥሪ አቅርቧል።
ገዳሙ “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው መርሐ ግብር፣ የመሠረት ድንጋይ ለማኖር የሚሆንና ግንባታውን ለማስጀመር የሚያስችል የ5,000 ብር ቻሌንጅ ማስጀመሩን አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞችና ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በንግግራቸው በአታ ለማርያም ገዳም ዛሬ ትልቅ ሥራ ለመስራት ጽንስ ላይ ነችና ቅዱስ እግዚአብሔር በሰላም ይገላግላት ዘንድ ልንማጸን እና ልንረዳ ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ወልዱ የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ዋና አስተዳዳሪ ”ግንባታ” ለበአታ 20 ሺህ ሰዎች ድጋፍን ተከትሎ በመስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በበአታ ለማርያም ዕለት የግንባታው የመሠረት ድንጋይ የሚቀመጥ መሆኑን ገልፀዋል ።
በመርሐ ግብሩም ጥንታዊውንና ታሪካዊውን የአብነት ትምህርት ቤት ደረጃውን የጠበቀ ሕንጻ በመገንባት ለተተኪ ትውልድ ሊቃውንት ምቹ የመማርያና የመኖሪያ ቦታ ማዘጋጀት ፤ 20,000 (ሃያ ሺህ) በጎ ፈቃደኛ ምእመናንን እያንዳንዳቸው 5,000 ብር በቻሌንጅ በማሳተፍ ለቦታው የመሠረት ድንጋይ ማኖሪያና ለግንባታ ማስጀመሪያ የሚሆን በቂ ገቢ መሰብሰብን ግብ አድርጎ መነሳቱ ተጥቅሷል።
ይህ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ጥሪ የሁላችንንም ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና ቅርሶቿን የምንወድ፣ የሃይማኖታችንና የታሪካችን ጥበቃ የሚያስጨንቀን ምእመናን በሙሉ በዚህ በጎ ሥራ ላይ በቻሌንጁ በመሳተፍ የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
የመሠረት ድንጋይ ማኖር ሥነ ሥርዓትም መስከረም 03 ቀን 2019 ዓ/ም እንደሆነም ተገልጿል። ይህ ታሪካዊ ገዳም የዳግማዊ አጼ ምኒልክ፣ የእቴጌ ጣይቱ እና የንግሥት ዘውዲቱ መካነ መቃብር የሚገኝበትና በርካታ ጥንታዊ ቅርሶችን የያዘ መሆኑ፣ ይታወቃል ።
ግንባታው 4 መሠረታዊ ሕንጻዎችን የያዘ መሆኑም፣ የግንባታ ፍቃድ መውሰዱም እና 2.5 ቢሊዮን ብር የሚፈጅ መሆኑን በተጨማሪም ግንባታው ሲጠናቀቅ 1500 የአብነት ተማሪዎችን እንደሚቀበል ተብራርቷል።
በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፤ አባ ተክለ ሃይማኖት የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ዋና አስተዳዳሪ ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
እያንዳንዱ የ5,000 ብር አስተዋጽኦ የአብነት ትምህርቱንና የታሪካችንን መሠረት ያጠናክራል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

See less
May be an image of dais and text. No photo description available.. May be an image of text that says ‘ំលមស្យ መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ም ምሥረታ <ኹላቸውም እረኞች ካልተሰበለል አንችልም። ጋዜጣዊ ጋዜማዊመግለጫ መግለጫ ግንባታ ለበአታ mpt MRUPE ፊኒልት 고그고사수 ያሴንጅ 我的行護护 አስተዋጽም ለማድረ O0 ንንክእና e ቁጥር- 0316 ቴሊ 1C+0950-433333 IC+0950-433333 IIN ንዶች ነባይ 2112675810916’. No photo description available.. May be an image of ‎dais and ‎text that says ‘‎ግንባታ ለበአታ 李街 HWEY 秋 ARGFE teV ንንባታለበአታ ግንባታ ለስኢታ 20 APICIe ንንጌታ ገንሳታለበአታ ለበእታ ግንናታ ለበእታ 秒以 ЛAP AMEPY ال ቴሌ ብር ንግድ ባንክ 1 አዋሽ ባንክ 0 .ዋሽ ባንክ 0 9 ግንባታ ለበአት 品 WETe ALA 14P ግገባታለበኢታ ግንባታ ሰበኤታ ግንባታ ለበአታ 二のぎ +. HPI ሰማርያም 1P ግንባታ ለበአታ ንተቁ “pTc‎’‎
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000088.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-05 18:19:342026-09-05 18:19:34“መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።
Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው «ቅድሚያ ለወንጌል» ሥልጠና የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ። Link to: በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው «ቅድሚያ ለወንጌል» ሥልጠና የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ። በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት አዘጋጅነት... Link to: የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ። Link to: የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ። የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top