የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው «ቅድሚያ ለወንጌል» ሥልጠና የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ።

September 5, 2026
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት «ቅድሚያ
ለወንጌል» በሚል መሪ ቃል ሲሰጥ የነበረው የሥልጠና መርሐ ግብር በተሳታፊዎች የጋራ የአቋም መግለጫና በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኃላፊ መምህር ሰለሞን በቀለ ፤ መመሪያ ማጠቃለያ ተጠናቋል።
ከነሐሴ 25 እስከ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሦስት ቀናት በቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሲካሄድ በቆየው በዚህ ሥልጠና ላይ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ዋና ጸሐፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞች፣ ቁጥጥርና ገንዘብ ያዦች፣ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች፣ የወጣት ማኅበራት ተወካዮች፣ እንዲሁም ብዙ ንስሐ ልጆች ያሏቸው ካህናትና ሰባክያነ ወንጌል በሥልጠናው ተሳትፈዋል።
የሥልጠናው ተሳታፊ የሆኑት ሰባክያነ ወንጌል በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ባወጡት ባለ 12 ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ መርሐ
ግብሩን ላዘጋጀው ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነትና ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ዕዝራ ንዋይ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ መሰል አቅምን የሚገነቡ ሥልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረውና በተከታታይነት እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። አገልጋዮቹ በአብያተ ክርስቲያናትና በገዳማት የተሰጣቸውን
አደራ መሠረት በማድረግ በተሻለ ትጋት፣ ቅንነትና ትሕትና ለማገልገልና በሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር ለመለወጥ ቃል
የገቡ ሲሆን፣ ስብከተ ወንጌል የቤተክርስቲያን ቀዳሚና ዋና ዓላማ መሆኑን በመገንዘብ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤዎችና የበላይ
ኃላፊዎች ለወንጌል አገልግሎት ተገቢውን ትኩረትና ክብር እንዲሰጡ እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ አሳስበዋል።
በተጨማሪም በሰዓት አጠቃቀም ዙሪያ የሚታዩ አለመናበቦችን በመቅረፍ በተለይ በሰንበት ቀናትና በበዓላት ለስብከተ ወንጌል በቂ ጊዜ
እንዲመደብና ሰባክያነ ወንጌል ያለአግባብ ጣልቃ ገብነት አገልግሎታቸውን በሥርዓት እንዲያከናውኑ አስገዳጅ መመሪያ እንዲሰጥ
የጠየቁት ተሳታፊዎቹ፣ በአንዳንድ አጥቢያዎች ለስብከተ ወንጌል የሚመደበው በጀት እጅግ አነስተኛ መሆኑን በመጠቆም በጀቱ
ከአገልግሎቱ ስፋትና አስፈላጊነት ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ ተፈትሾ እንዲስተካከል ጠይቀዋል። በተመሳሳይም የተመደቡ አገልጋዮች የሙያ ብቃት፣ የዕውቀት ዝግጁነትና የአገልግሎት ተነሳሽነት ተፈትሾ አስፈላጊው የማሻሻያና የማብቃት እርምጃዎች እንዲወሰዱ አጽንዖት ሰጥተዋል። በዘመኑ ስብከተ ወንጌልን ለማጠናከር ማኅበራዊ ሚዲያና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በአግባቡና በጥንቃቄ በመጠቀም ከቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሳይወጡ ምዕመናንን ለማገልገልና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለማዳረስ ቃል ገብተዋል።
በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ሰለሞን በቀለ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፣ ራስን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር ጽሕፈት ቤቶችን በማደራጀት የሕዝበ ክርስቲያኑንና የአገልጋዩን ሁኔታ ለመፈተሽ መሰል ሥልጠናዎችና የልምድ ልውውጦች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸው፣ መርሐ ግብሩን ግንባር ቀደም ሆኖ ላዘጋጀው የአቃቂ ቃልቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዋና ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም፣ የሀገረ ስብከቱ ትምህርትና ሥልጠና ክፍል በአዲስ መልኩ በ2019
ዓ.ም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን አቅዶ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጀመረውን መልካም ተሞክሮ በማሳደግ በመላው ስምንቱ ክፍላተ
ከተማ ሰፊ ሥልጠናዎችን ለማዘጋጀት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል።
አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተም አስተዳዳሪዎች ሠራተኞችን ያላግባብ ከማገድ፣ ከማባረርና ከደረጃ ዝቅ ከማድረግ ተቆጥበው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዕርቅን፣ ሥልጠናንና መግባባትን እንዲያስቀድሙ አሳስበዋል።
በአስተዳደር ክፍተቶች ምክንያት አገልጋዮችና
ቤተሰቦቻቸው ለችግር እንዳይዳረጉ ክፍተቶችን በጋራና በፍትሐዊነት ማረም እንደሚገባ አስገንዝበው፣ “የእያንዳንዱ ደብር አስተዳዳሪ
የብቃት መለኪያ ሊሆን የሚችለው በደብሩ ያለውን ካህን እዚያው አሰልጥኖ፣ አስተምሮና አቅፎ ማኖር ሲችል ነው፤ ያኔ ነው ሥልጠናው
ውጤታማ ሆነ የሚባለው” በማለት አስተዳደራዊና መንፈሳዊ መመሪያ ሰጥተዋል።
መርሐ ግብሩ «ቅድሚያ ለወንጌል» የሚለው መሪ ቃል በተግባር፣ በእቅድ፣ በበጀትና በጊዜ አጠቃቀም በመተግበር በጋራ ለመሥራት በመስማማት በጸሎት ተጠናቋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት «ቅድሚያ ለወንጌል» በሚል መሪ ቃል ሲሰጥ የነበረው የሥልጠና መርሐ ግብር በተሳታፊዎች የጋራ የአቋም መግለጫና በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኃላፊ መምህር ሰለሞን በቀለ ፤ መመሪያ ማጠቃለያ ተጠናቋል።
ከነሐሴ 25 እስከ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሦስት ቀናት በቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሲካሄድ በቆየው በዚህ ሥልጠና ላይ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ዋና ጸሐፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞች፣ ቁጥጥርና ገንዘብ ያዦች፣ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች፣ የወጣት ማኅበራት ተወካዮች፣ እንዲሁም ብዙ ንስሐ ልጆች ያሏቸው ካህናትና ሰባክያነ ወንጌል በሥልጠናው ተሳትፈዋል።
የሥልጠናው ተሳታፊ የሆኑት ሰባክያነ ወንጌል በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ባወጡት ባለ 12 ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ መርሐ ግብሩን ላዘጋጀው ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነትና ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ዕዝራ ንዋይ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ መሰል አቅምን የሚገነቡ ሥልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረውና በተከታታይነት እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። አገልጋዮቹ በአብያተ ክርስቲያናትና በገዳማት የተሰጣቸውን
አደራ መሠረት በማድረግ በተሻለ ትጋት፣ ቅንነትና ትሕትና ለማገልገልና በሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር ለመለወጥ ቃል የገቡ ሲሆን፣ ስብከተ ወንጌል የቤተክርስቲያን ቀዳሚና ዋና ዓላማ መሆኑን በመገንዘብ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤዎችና የበላይ
ኃላፊዎች ለወንጌል አገልግሎት ተገቢውን ትኩረትና ክብር እንዲሰጡ እንዲሁም ምቹ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ አሳስበዋል።
በተጨማሪም በሰዓት አጠቃቀም ዙሪያ የሚታዩ አለመናበቦችን በመቅረፍ በተለይ በሰንበት ቀናትና በበዓላት ለስብከተ ወንጌል በቂ ጊዜ እንዲመደብና ሰባክያነ ወንጌል ያለአግባብ ጣልቃ ገብነት አገልግሎታቸውን በሥርዓት እንዲያከናውኑ አስገዳጅ መመሪያ እንዲሰጥ የጠየቁት ተሳታፊዎቹ፣ በአንዳንድ አጥቢያዎች ለስብከተ ወንጌል የሚመደበው በጀት እጅግ አነስተኛ መሆኑን በመጠቆም በጀቱ
ከአገልግሎቱ ስፋትና አስፈላጊነት ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ ተፈትሾ እንዲስተካከል ጠይቀዋል። በተመሳሳይም የተመደቡ አገልጋዮች የሙያ ብቃት፣ የዕውቀት ዝግጁነትና የአገልግሎት ተነሳሽነት ተፈትሾ አስፈላጊው የማሻሻያና የማብቃት እርምጃዎች እንዲወሰዱ አጽንዖት ሰጥተዋል። በዘመኑ ስብከተ ወንጌልን ለማጠናከር ማኅበራዊ ሚዲያና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በአግባቡና በጥንቃቄ በመጠቀም ከቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሳይወጡ ምዕመናንን ለማገልገልና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለማዳረስ ቃል ገብተዋል።
በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፣ ራስን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር ጽሕፈት ቤቶችን በማደራጀት የሕዝበ ክርስቲያኑንና የአገልጋዩን ሁኔታ ለመፈተሽ መሰል ሥልጠናዎችና የልምድ ልውውጦች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸው፣ መርሐ ግብሩን ግንባር ቀደም ሆኖ ላዘጋጀው የአቃቂ ቃልቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዋና ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም፣ የሀገረ ስብከቱ ትምህርትና ሥልጠና ክፍል በአዲስ መልኩ በ2019 ዓ.ም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን አቅዶ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጀመረውን መልካም ተሞክሮ በማሳደግ በመላው ስምንቱ ክፍላተ
ከተማ ሰፊ ሥልጠናዎችን ለማዘጋጀት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል።
አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተም አስተዳዳሪዎች ሠራተኞችን ያላግባብ ከማገድ፣ ከማባረርና ከደረጃ ዝቅ ከማድረግ ተቆጥበው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዕርቅን፣ ሥልጠናንና መግባባትን እንዲያስቀድሙ አሳስበዋል።
በአስተዳደር ክፍተቶች ምክንያት አገልጋዮችና
ቤተሰቦቻቸው ለችግር እንዳይዳረጉ ክፍተቶችን በጋራና በፍትሐዊነት ማረም እንደሚገባ አስገንዝበው፣ “የእያንዳንዱ ደብር አስተዳዳሪ
የብቃት መለኪያ ሊሆን የሚችለው በደብሩ ያለውን ካህን እዚያው አሰልጥኖ፣ አስተምሮና አቅፎ ማኖር ሲችል ነው፤ ያኔ ነው ሥልጠናው
ውጤታማ ሆነ የሚባለው” በማለት አስተዳደራዊና መንፈሳዊ መመሪያ ሰጥተዋል።
መርሐ ግብሩ «ቅድሚያ ለወንጌል» የሚለው መሪ ቃል በተግባር፣ በእቅድ፣ በበጀትና በጊዜ አጠቃቀም በመተግበር በጋራ ለመሥራት በመስማማት በጸሎት ተጠናቋል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000087.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-09-05 18:15:412026-09-05 18:15:41በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው «ቅድሚያ ለወንጌል» ሥልጠና የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ።
Search Search

Recent Posts

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።
  • የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ !!!
  • ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)
  • የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ለተባባሪ ፕሮፌሰር ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር አካሄዱ።
  • “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ።

Archives

  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የወሊሶ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ቡኡራ ቦሩ አጸደ ሕፃናት ትምህርት ቤት በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተመረቀ። Link to: የወሊሶ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ቡኡራ ቦሩ አጸደ ሕፃናት ትምህርት ቤት በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተመረቀ። የወሊሶ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ... Link to: “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ። Link to: “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ” በሚል የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታ ድጋፍ ማስጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በተገኙበት ተሰጠ። “መስከረም በአታ የሃያ ሺህ ሰዎች ምሥረታ”...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top