ለዘመናት የቤተክርስቲያንን ተልእኮ በማሳለጥ የሚታወቀው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በበጀት ዓመቱ ለሦስተኛ ጊዜ ዐቢይ ጉባኤ አካሄደ

ሚያዚያ ፲፱ ቀን ፳፻፲ወ፰ዓ.ም.
ኢኦተቤክ ሕዝብግንኙነት
አዲስአበባ ኢትዮጵያ
👉 እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮች ሊሆኑ ለተጠሩት ለቅዱሳን ሐዋርያት በመጀመሪያ የታወጀው አዋጅ የማይሻር፣ ለዘለዓለም ጸንቶ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ያለና ሲተላለፍ የሚኖር ሕያው ቃል በመሆኑ ብርሃናተ ዓለም ሐዋርያት፣ ሰባ ሁለቱ አርድዕት የስብከታቸውን ማዕከል ክርስቶስንና የአዳኝነቱን ሥራ በማድረግ አስዋከ ረሲዓንን እየነቀሉ፣ የወንጌልን ምርጥ ዘር በምዕመናን የልቡና ማሳ ላይ እየዘሩ በጋራም በተናጠልም ከፍተኛ ሐዋርያዊ ተጋድሎ የፈጸሙ ሲሆን ዘሩም በቅሎ አፍርቶ ፍሬው ከሐዋርያት ለሐዋርያነ አበው፣ ከሐዋርያነ አበው ለሊቃውንት ከሊቃውንት ወደ እኛ ዘመን መተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡
👉 የክርስቲያኖች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ በጥንድ እና በግል ሲመራ የነበረው የአመራር ስርዓት በመዋቅር የመምራት ስሌት ከመጣ በኋላም ብዙ አባቶቻችን ስለ ቤተክርስቲያን አያሌ ተግባራትን ማከናወናቸው ሌላኛው የስብከተ ወንጌል ፍሬ መሆኑም ይገለጻል።
👉 ለዘመናት በብዙ ፈተና ያለፈችው ቅድስት ቤተክርስታያናችን በ1950ዓ.ም ከግብፅ የአመራር
ስርዓት ወጥታ የራሷን ፓትርያርክ ከሾመች በኋላ በ1952ዓ.ም የመጀመሪያ ሥራዋን ያደረገችው የሀገሪቱን ንጉሥና ቅዱስ ፓትርያርኩ የበላይ ጠባቂነት የሚመራ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሳተፈ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ምክር ቤት ማቋቋም ሲሆን ምክር ቤቱ ከንጉሡ እና ከፓትርያርክ ጀምሮ ሁሉም ተስፋ የሚጥሉበት ስለነበረ ለአፈጻጸም የማይቸገር መሆኑን
ሊቃውንት ይገልጻሉ።
👉 የንጉሡ ዘመን ካለፈ በኋላም ሶሻሊዝምን አራማጁ የደርግ መንግሥት ለስብከተ ወንጌል ፈተና ቢሆንበትም ቅሉ ባለ ራዕዩ እና ልባሙ ቅዱስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ አማካኝነት ሰበካ ጉባኤንና
ሰንበት ትምህርት ቤት ወልዶ ራሱን በመዋቅር በ1972ዓ.ም አዲስና ለእንቅስቃሴው በር ከፋች ስርዓት በመፍጠር ሲሰራ እንደነበረ የዓይን እማኞች ይናገራሉ።
👉 ከለውጡ ማግሥት በ1984 እና በ1988 ዓ.ም. ደግሞ በሌላኛው ፓትርያርክ ልዩ መተዳደሪያ ደንብ ተሠርቶለት ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋቱ ረገድ አንቱ የተባለ ሥራ የተሠራ ሲሆን በ1992 ዓ.ም. ደግሞ ዓለም ዓቀፋዊ በሆኑት ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅደስ አቡነ ጳውሎስ መመሪያ ሰጭነት በብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የወቅቱ ሥራ አስኪያጅ አስፈፃሚነት የተቋቋመው የ120 ቤተሰብ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ኮሚቴ ደግሞ ሌላኛው የስብከተ ወንጌል ገፅታ ነው።
👉 በዚህ ልክ ራሱን እያሳደገ የመጣው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ዛሬም የምዕመናን ደጀንነቱንና የቤተክርስቲያን ብቸኛ ተስፋ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ በየጊዜው ስልጠናዎችንና ውይይቶችን እየደረገ ነው።
👉 በዛሬው እለትም ይህንኑ ስልጠናና ውይይት በወንጌል ሕይወታች ሆነልን በሚል ርዕስ ያካሄደ ሲሆን በስልጠናው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብጰት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ፣ የሐድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ የጠቅላይ ቤተክህነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡር ሊቀ ኅሩያን ይልማ ጌታሁን የኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጠቅላይ ጸሐፊ
ክቡራን የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎችና የየድርጅቶች ሥራ አስኪያጆች፤
ክቡራን የአህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጆችና የስብከተ ወንጌል ክፍል ኀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
👉 መርሐግብሩ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሲሆንሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም የበላይ ኀላፊ መሪነት የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ካልናት ጸሎተ ወንጌል አድራሽነት ተጀምሮ የስብከተ ወንጌል ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸው በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ በርሱም ላይ ወይይት ተደርጎ ከምሳ ሰዓት በፊት ያለው መርሐግብር ተጠናቋል።

በበርካቶች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ድረ-ገጽ አገልግሎት ጀመረ

ሚያዚያ ፲፭ ቀን ፳፻፲ወ፰ዓ.ም.
ኢኦተቤክ ቤሕአልድ
አዲስአበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለዘመናት በመኳንንት፣ በወይዛይርትና በግለሰቦች አማካኝነት በውርስ፣ በኑዛዜና በስጦታ መልክ የተሰጧትንና በይዞታ አስከብራ ያቆየቻቸውን ቤቶች፣ ሕንፃዎችና ይዞታዎች ረጅም ዘመናት በድርጅቱ ባሳለፉ ቅን የድርጅቱ ሠራተኞች አእምሮ ከመያዝ ባሻገር የሚመለከታቸው ሁሉ እንዲያውቁት በሚስችል መልኩ ተሰንዶ አለመቀመጡ ድርጅቱ በሥሩ የሚገኙ ደንበኞችን በአግባቡ ለማስተዳደር የሚቸገር ከመሆኑም በላይ የሚባክኑ ይዞታዎች መኖራቸውን ይነገራል ።
ይህንን የተረዱት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪጅ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ በድርጅቱ ሥር የሚተዳደሩ ቤቶች ፣ ሕንጻዎችና ይዞታዎች መላ ታሪካቸው ተመዝግቦና ተሰንዶ ለሚመለከታቸው አካላት ከማቅረብ ባሻገር በዲጂታል ቴክኖሎጂ እየተጫኑ እንዲሰነዱ ለማድረግ ለድርጅቱ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ክፍል ከማቋቋም ጀምሮ በመላው ዓለም ተዳራሽነቱን ለማስፋት የድርጅቱን ድረ-ገጽ ማበልጸግ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት በዚህ ሥራ ላይ ቤተክርስቲያንን ለማገልገል ቆርጠው የተነሱ ቅን የቤተክርስቲያን ልጆችን በማስተባበር የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የሚል ድረ-ገጽ በልፅጎ በዛሬው እለት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብጰት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ የጠቅላይ ቤተክህነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡራን የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎችና የየድርጅቶች ሥራ አስኪያጆች፤
ክቡራን እና ክቡራት የድርጅቱ ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።

ኋላ ቀር የገንዘብ አስተዳደርን በማዘመን የደንበኞችን ውጣ ውረድ የማስቀረት ዓላማን ያነገበው የሞባይል ባንኪንግ አገልግልግሎት በይፋ ተመርቆ ተግባራዊ ተደረገ

ሚያዚያ ፲፭ ቀን ፳፻፲ወ፰ዓ.ም.
ኢኦተቤክ ቤሕአልድ
አዲስአበባ ኢትዮጵያ
የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ይዞት የተነሳውን የደንበኛ ተኮር አስተዳደር ስርዓት አካል የሆነው የዘመናዊ ገንዘብ አስተዳደር ቴክኖሎጂ ማበልጸግ ተግባራዊ ለማድረግ ከበርካታ ባንኮች ፣ ድርጅቶችና ኤጀንትቶች አማራጭ መንገዶችን ለማየት ተደጋጋሚ ውይይቶችን ማድረጉን መዘጋባችን የሚታወስ ነው።
የቀረቡት አማራጮች ሙሉ በሚባል ደረጃ የሚያጓጉ ቢሆኑም ድርጅቱ ጥበብ በተሞላው ምርጫ በመምረጥ ከዐባይ ባንክ አክስዮን ማኅበር አራት ኪሎ ቅርንጫፍ ጋር ለመሥራት የወሰነ ሲሆን ባንኩ ያቀረበው አማራጭ እጅግ ዘመኑን የዋጀና በቀላል መንገድ ሊተገበር የሚችል መሆኑ ታይቶ ስምምነት ተደርጓል ።
በስምምነቱ ደንበኞች ያለምን ውጣ ውረድ ኪያራያቸውን በሞባይል ባንኪን እንዲከፍሉ ማድረግ፣ የመክፈያ ጊዜ ሲደርስ ማስታዎሻ መልእክት መላክ፣ ከክፍያ በኋላ አመስግኖ መቀበል፣ ጊዜው ያለፈባቸውን ከፋዮች ከእነቅጣታቸው እንዲከፍሉ ማንቃትና የመሳሰሉትን የሚተገብር ነው ተብሏል።
ይህንን ቴክኖሎጂ መላው ደንበኞች ተጠቃሚ በመሆን ክፍያን ከፍለው ደረሰኝ ለማወራረድ የሚያባክኑትን ጊዜ ይቆጥባሉ ተብሎ ይታመናል።
ይህ የደንበኞችን ልብ በሐሴት የሞላው ዘመናዊው የኪራይ አሰባሰብ ስርዓት በዛሬው እለት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
ክቡር ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር በማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ
ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ የጠቅላይ ቤተክህነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡራን የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎችና የየድርጅቶች ሥራ አስኪያጆች፤
ክቡራን እና ክቡራት የድርጅቱ ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።

ቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ይዞት የተነሳውን ደንበኛ ተኮር ስርዓት ተፈጻሚ ለማድርግ የመጀመሪያውን ምዕራፍ አጠናቆ በዛሬው እለት በይፋ አስመረቀ

ሚያዚያ ፲፭ ቀን ፳፻፲ወ፰ዓ.ም.
ኢኦተቤክ ቤሕአልድ
አዲስአበባ ኢትዮጵያ
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም የበላይ ኀላፊ በሚመሩበት በሳልና አባታዊ የአመራር ጥበብ ካደረጉት ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት ሥራ አካል የሆነው የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት በሚፈለገው ልክ ራሱ እየለወጠ ነው።
ድርጅቱ ጥር 15 ቀን 1990 ዓ.ም አሁን ባለው ተክለቁመና ልክ እንዲመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ካስተላፈበት ጊዜ ጀምሮ ደረጃ በደራጃ እየያደገ የመጣና ከ11 በላይ ዋና ሥራ አስኪያጆችን ያፈራረቀ ቢሆንም በ12ኛው የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ ድንቅ ጥበብ ቀማሪነት የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ በብዙዎች ዘንድ ዓመታትን ይፈጃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ተአምር በሚባል ደረጃ ለውጥጡን እንዲፋጠን አድርጎታል። በተለይም የወቅቱ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ የሚሰጡት አባታዊ አመራር ክንፍ ያላቸው ሁሉ እንዲበሩ የሚፈቅድ ነፃነትን የሰጠ በመሆኑ ለድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ታላቅ እድል ፈጥሮለታል ።
ድርጅቱ ራሱን በማዘመንና ደንበኛ ንጉሥ ነው የሚለውን ብሂል በማመን ደንበኛ ተኮር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ለደንበኞች ምቹ ፣ ማራኪ፣ ጽዱና ውብ ከባቢ በመፍጠር ዘመኑን የዋጀ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ለተፈጻሚነቱም ሲታትር የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
የዚህ ድንቅ ሐሳብ ባለቤትና የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረክርስቶስ ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አባታዊ መመሪያ በመቀበል ሌሊትና ቀን ያላሰለሰ ጥረት በማድረግና የድርጅቱን የሥራ ኀላፊዎች በማነቃቃት እንዲሁም የድርጅቱ ደንበኞች በየኔነት ሥሜት እንዲሠሩ በማስተባበር ላለፉት ሰባት ወራት ድንቅ አፈጻጸም ማስመዝገባቸውን በቅርቡ መዘገባች የሚታወስ ነው።
በተለያዩ ጊዜያት በዘገባ እናዳሳወቅነው በድርጅቱ በርካት ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን በድርጅቱ የዘመናት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማያውቅ መልኩ ደንበኛ ተኮር ስርዓትን ለማሳለጥ ሆድና ጀርባ ሆነው ይኖሩ የነበሩ የድርጅቱን ደንበኞች በማግባባትና የእኔ ነው ብለው እንዲያስቡ በማድረግ ከአሥራ አራት ሚሊዮን ብር በላይ የፈጀ የድርጅቱ መገልገያ ቢሮ እድሳት ሠርተዋል።
አዲሱ ቢሮ የድርጅቱን የበላይ ሊቀ ጳጳስ ቢሮን ጨምሮ 16 ዘመናዊ ክፍሎች የሉት ሲሆን ለደንበኞች ምቹ ከመሆኑ ባሻገር ሠራተኞች ደስተኛ ሆነው እንደሠሩ ተደርጎ የታነፀ በመሆኑ ከነባሩ ቢሮ ልዩ ያደርገዋል።
ሥራው ለወራት በልዩልዩ ሁኔታ የቆየ ሲሆን በዛሬው እለትም
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብጰት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
ክቡር ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት የክብር ጠቅላይ ሚንስትር በማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ፣
ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ የጠቅላይ ቤተክህነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡራን የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎችና የየድርጅቶች ሥራ አስኪያጆች፤
ክቡራን እና ክቡራት የድርጅቱ ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።

የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዕድሳት የደረሰበትን አሁናዊ ሁኔታ በተመለከተ ለቅዱስ ፓትርያርኩ እና ለብፁዓን አባቶች መግለጫ ቀረበ

ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም
‎የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዕድሳት አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ‎ብፁዕ አቡነ ሳዊሮሰ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አሀጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ‎ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱሰ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የራያ ሀገረ ስበከት ሊቀጳጳስ፣ ‎ብፁዕ አቡነ ሳዊሮሰ የቴክሳስ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ‎ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል ።

‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን የሚሳለሙት ታሪካዊው የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፣ የሕንጻውን ጥንታዊነት ለመጠበቅና ምዕመናን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሰፊ የዕድሳት ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
‎‎መገለጫዉን ያቀረቡት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮሰ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ ‎የዚህ ታላቅ የዕድሳት ፕሮጀክት ዓላማ በጊዜ ብዛትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በቤተክርስቲያኑ ጣሪያ፣ ግድግዳ እና ውጫዊ አካላት ላይ የደረሱ ጉዳቶችን መጠገን እና የቤተክርስቲያኑን ጥንታዊ የኪነ-ሕንጻ ጥበብና ታሪካዊ ይዘት ሳይለቅ በባለሙያዎች የታገዘ ጥገና ማካሄድ እንደሆነ ባቀረቡት ማብራሪያ ገልጸዋል ።
‎ብፁዕነታቸው ዕድሳቱ በብዙ ምዕራፎች የተከፈለ መሆኑን ገልጸው ጥናትና የዲዛይን ሥራዎችን ማጠናቀቅ ፣ የቤተክርስቲያኑን ዋና አካል (መቅደስና ቅኔ ማኅሌት) የመጠገን ሥራ ፣ የአጸዱንና በዙሪያው ያሉ አገልግሎት መስጫዎችን የማዘመን ሥራን ያካትታል ብለዋል ።
ብፁዕነታቸው ‎ይህ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት ሥፍራ ብቻ ሳይሆን የሀገር ቅርስ ቢሆንም ፤ ላለፉት 64 ዓመታት ዕድሳት ሳይደረግበት የቆየው ሕንጻ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ዕድሳቱ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። ለዕድሳቱ የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወጪ ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያሰፈልግም ተጠቁሟል ።
‎ለዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት ስኬት ምዕመናን በጸሎት፣ በጉልበትና በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በገዳሙ ስም በተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች አማካኝነት የድርሻቸውን እንዲወጡ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥሪ አቅርበዋል።©EOTCTV

ለፉት አራት ቀናት በኬንያ ንይሮቢ በሐዋርያዊ አገልግሎት ላይ የሰነበቱት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል

ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
በኬንያ ናይሮቢ ሐዋርያዊ አገልግሎት ሲያከናውኑ የሰነበቱ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ አመሻሹ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሁለቱ ብፁዓን አባቶች ሚያዚያ 9ቀን 2018 ዓ.ም ናይሮቢ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የናይሮቢ ደብረ መድኀኒት መድኅኔዓለም ቤተክርስቲያን ካህናት፣ምዕመናንና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በናይሮቢ ደብረ መድሃኒት መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያንም የአቀባበል መርሐ ግብር የተደረገላቸው መሆኑ ይታወሳል።
ብፁዓን አባቶቹ በናይሮቢ ደብረ መድሃኒት መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜና እሑድን በቅዳሴና በስብከተወንጌል አገልግሎት ሕዝበ ክርስቲያኑን ሲያገለግሉ መቆየታቸውና
ሚያዚያ 10ቀን2018ዓ.ም በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉብኝት ማድረጋቸውም በወቅቱ መዘገቡ የሚታወስ ነው።
በኬንያ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉብኝት ወቅት የሚሲዮኑ ዲፕሎማቶች እና ሠራተኞች ደማቅ አቀባባል ያደረጉላቸው ሲሆን፣ የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክቡር አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ለብፁዓን አባቶች ስለኤምባሲው አመሰራረት እንዲሁም በሁለቱ አገሮች መካከል ስላለው መልካም ግንኙነት እና ትብብር ገለጻ እንዳደረጉላቸው በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።
ሁለቱ ብፁዓን አባቶች በናይሮቢ ኬንያ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ዛሬ መምሻውን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በኬንያ ናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጎበኙ

ሚያዚያ 11ቀን2018ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉብኝት አደረጉ።
በጉብኝቱ ወቅት የሚሲዮኑ ዲፕሎማቶች እና ሠራተኞች ለብፁዓን አባቶች አቀባባል ያደረጉ ሲሆን፣ የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክቡር አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ለብፁዓን አባቶች ስለኤምባሲው አመሰራረት እንዲሁም በሁለቱ አገሮች መካከል ስላለው መልካም ግንኙነት እና ትብብር ገለጻ ሰጥተዋል ሲል ኤምባሲው በማኀኅበራዊ ሚዲያ ገጹ አስተታውቋል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ኬንያ ናይሮቢ ተጓዙ

ሚያዚያ 9ቀን 2018 ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለአራት ቀናት ሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ኬንያ ናይሮቢ ተጉዘዋል።
ሁለቱ ብፁዓን አባቶቻችን ናይሮቢ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የናይሮቢ ደብረ መድኀኒት መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን ካህናት፣ምዕመናንና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በናይሮቢ ደብረ መድሃኒት መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያንም የአቀባበል መርሐ ግብር ተደርጎላቸዋል።
ብፁዓን አባቶቻችን በኬንያ ቆይታቸው በናይሮቢ ከተማ በሚገኙ አብያተክርስቲያናት በመገኘት ምዕመናንን በማስተማርና በማጽናናት ሐዋርያዊ ተልዕኳቸውን እንደሚያከናውኑ ከተያዘው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
የብፁዓን አባቶቻችንን ሐዋርያዊ አገልግሎት በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብዝኃ ሕይወት ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ጥረቷን ለማጠናከር ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየመከረች ነው

ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም
‎የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያዊ ተራድኦ ኮሚሽን ( EOTCVDICAC) ቤተክርስቲያኗ ለዘመናት ጠብቃ ያቆየችውን የብዝኃ ሕይወት ሀብት በዘላቂነት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የምታደርገውን አስተዋጽኦ ይበልጥ ለማሳደግ ዛሬ ከአጋር ድርጅቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄዳለች ።
‎በውይይቱ ላይ ኮሚሽነር ይልቃል ሽፈራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣አቶ ገብረሥላሴ አጽብሃ የኮሚሽኑ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ፣ አቶ አበጀህ እሸቴ የኢትዮጵያ ደን ልማት ሪሰርቸር ዳሬከተረ ዳሬክቶሬት ፣አቶ ተዋናይ ሰይፈ ሥላሴ የሰላም ኢቲክስ አና አድቮኬሲ መምረያ ኃላፊ ጨምሮ ከተለያዩ የልማት አጋሮች የተወከሉ እንግዶች፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎችና የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል
‎ውይይቱ የተዘጋጀበት ዋና ዓላማ ቤተክርስቲያኗ በገዳማትና አድባራት ዙሪያ ያሉ ደኖችን በመጠበቅ ረገድ ያላትን ጥንታዊና ውጤታማ ልምድ ለዓለም አቀፍና ለአገር በቀል አጋሮች ድርጅቶች ማሳየት እንደሆንና እሰካሁን በተሠሩ ሥራዎች ላይ አሰተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምሰጋና ለማቅረብ ያለመ መሆኑን አቶ ይልቃል ሽፈራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር ገልጸዋል ።
‎አያይዘውም ኮሚሽነሩ እንዳሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያዊ ተራድኦ ኮሚሽን እነዚህን የደሴት ደኖች ከመጥፋት ለመከላከል ለትውልድ የሚሸጋገሩበትን ሳይንሳዊና ተቋማዊ አሰራር መዘርጋትም ተቀዳሚ ተገባሩ እንደሆነም አክለዋል ።
‎የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ደኖቹ ለካርቦን ክምችትና ለአካባቢ ጥበቃ የሚያበረክቱትን ሚና በማሳደግ ረገድ ኮሚሸኑ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በትብብር መሥራት ተቀዳሚ ዓላማው አድርጎ እየሠራ እደሚገኝ በመድረኩ ተነግሯል ።
‎ኮሚሽኑ እንዳመለከተው፣ ቤተክርስቲያኗ ያሏት ደኖች ለብዝኃ ሕይወት መሸሸጊያ ከመሆናቸውም በላይ ለሀገሪቱ የደን ሽፋን ከፍተኛ ድርሻ መኖሩን ገልጾ ይህንን ሀብት በተሻለ ሁኔታ ለማስተዳደርና ለማልማት ከመንግስት ተቋማት ጋር የፖሊሲና የቴክኒክ ድጋፍ ማጠናከር፣ ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ጋር የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነቶችን መፍጠር፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ከማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ጋር ማቀናጀት ላይ ትኩረት አደርጎ እየሠራ መሆኑን አቶ ገብረሥላሴ አጽብሃ የኮሚሽኑ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ገልጸዋል ።
‎ቤተክርስቲያን የፈጣሪን ፍጥረት የመንከባከብ መንፈሳዊ ኃላፊነቷን ስትወጣ ቆይታለች፤ አሁን ግን ይህ ጥረት ከዘመናዊ የልማት አጋሮች ጋር ሲቀናጅ ውጤቱ ለሀገርና ለዓለም የሚተርፍ ይሆናል” ሲሉ የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።
‎ውይይቱ በቀጣይ በሚተገበሩ የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል ።©Eotc tv