የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብዝኃ ሕይወት ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ጥረቷን ለማጠናከር ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየመከረች ነው

ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም
‎የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያዊ ተራድኦ ኮሚሽን ( EOTCVDICAC) ቤተክርስቲያኗ ለዘመናት ጠብቃ ያቆየችውን የብዝኃ ሕይወት ሀብት በዘላቂነት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የምታደርገውን አስተዋጽኦ ይበልጥ ለማሳደግ ዛሬ ከአጋር ድርጅቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄዳለች ።
‎በውይይቱ ላይ ኮሚሽነር ይልቃል ሽፈራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣አቶ ገብረሥላሴ አጽብሃ የኮሚሽኑ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ፣ አቶ አበጀህ እሸቴ የኢትዮጵያ ደን ልማት ሪሰርቸር ዳሬከተረ ዳሬክቶሬት ፣አቶ ተዋናይ ሰይፈ ሥላሴ የሰላም ኢቲክስ አና አድቮኬሲ መምረያ ኃላፊ ጨምሮ ከተለያዩ የልማት አጋሮች የተወከሉ እንግዶች፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎችና የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል
‎ውይይቱ የተዘጋጀበት ዋና ዓላማ ቤተክርስቲያኗ በገዳማትና አድባራት ዙሪያ ያሉ ደኖችን በመጠበቅ ረገድ ያላትን ጥንታዊና ውጤታማ ልምድ ለዓለም አቀፍና ለአገር በቀል አጋሮች ድርጅቶች ማሳየት እንደሆንና እሰካሁን በተሠሩ ሥራዎች ላይ አሰተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምሰጋና ለማቅረብ ያለመ መሆኑን አቶ ይልቃል ሽፈራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር ገልጸዋል ።
‎አያይዘውም ኮሚሽነሩ እንዳሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያዊ ተራድኦ ኮሚሽን እነዚህን የደሴት ደኖች ከመጥፋት ለመከላከል ለትውልድ የሚሸጋገሩበትን ሳይንሳዊና ተቋማዊ አሰራር መዘርጋትም ተቀዳሚ ተገባሩ እንደሆነም አክለዋል ።
‎የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ደኖቹ ለካርቦን ክምችትና ለአካባቢ ጥበቃ የሚያበረክቱትን ሚና በማሳደግ ረገድ ኮሚሸኑ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በትብብር መሥራት ተቀዳሚ ዓላማው አድርጎ እየሠራ እደሚገኝ በመድረኩ ተነግሯል ።
‎ኮሚሽኑ እንዳመለከተው፣ ቤተክርስቲያኗ ያሏት ደኖች ለብዝኃ ሕይወት መሸሸጊያ ከመሆናቸውም በላይ ለሀገሪቱ የደን ሽፋን ከፍተኛ ድርሻ መኖሩን ገልጾ ይህንን ሀብት በተሻለ ሁኔታ ለማስተዳደርና ለማልማት ከመንግስት ተቋማት ጋር የፖሊሲና የቴክኒክ ድጋፍ ማጠናከር፣ ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ጋር የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነቶችን መፍጠር፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ከማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ጋር ማቀናጀት ላይ ትኩረት አደርጎ እየሠራ መሆኑን አቶ ገብረሥላሴ አጽብሃ የኮሚሽኑ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ገልጸዋል ።
‎ቤተክርስቲያን የፈጣሪን ፍጥረት የመንከባከብ መንፈሳዊ ኃላፊነቷን ስትወጣ ቆይታለች፤ አሁን ግን ይህ ጥረት ከዘመናዊ የልማት አጋሮች ጋር ሲቀናጅ ውጤቱ ለሀገርና ለዓለም የሚተርፍ ይሆናል” ሲሉ የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።
‎ውይይቱ በቀጣይ በሚተገበሩ የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል ።©Eotc tv