የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ እንኳን አደረሰዎ መርሐግብር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሐፈት ቤት በደማቅ መንፈሳዊ ስነስርዓት ተካሄደ

April 13, 2026

ሚያዚያ ፭ ቀን ፪፻ ፲ወ፰ዓ.ም.
ኢኦተቤክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
አዲስአበባ , ኢትዮጵያ
በየዓመቱ በትንሣኤ ማግስት ፣ በአዲስ ዓመት ማግስትና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ማግስት ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ጀምሮ እስከ አዲስአበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት አገልጋዮች በመሰባሰብ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የእንኳን አደረሰዎ መርሐግብር ይካሄዳል።
በዚሁ መሠረት የዘንድሮ የ2018ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም የበላይ ኀላፊ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፣ የራያ ስድስቱ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅርሳቅርስ ወመዘክርና ቤተመጻሕፍት ፣ የማሕበራት ምዝገባ ፣ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያዎች የበላይ ኀላፊ፣
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስአበባ፣ የሐድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ለቃነ ጳጳሳት፣
ንቡረእድ ኤልያስ አብርሃ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ
ረ/ፕ ግርማ ባቱ (ቀሲስ) የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፣
መ/ም አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክልነት ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችና ሠራተኞች ፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችና ሠራተኞች፣የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት መርሐግብሩ ተካሂዷል።
መርሐግብሩ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃና ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መሪነት የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት ጸሎተ ወንጌል አድራሽነት በጸሎት የተከፈተ ሲሆን የበርካታ ሊቃውንት መፍለቂያ በሆነውና በአንጋፋው በሰዋስዋወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርትና መምህራን አማካኝነት ያሬዳዊ ዜማ መነሻነት የእለቱ ተከታታይ መርሐግብራት መቅረብ ጀምረዋል።
ከሊቃውንቱ ያሬዳዊ ዜማ በመቀጠል የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት ተወካዮች የትንሣኤውን ምስጢር በሚያብራራ መቅድም በመነሣት በልጅነት መታዘዝ ለቅዱስነታቸው የእንኳን አደረሰዎ መልእክት በጽሑፍ አቅርበው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማዕከላውያን የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና የጋሞኛ ዘማርያን በያሬዳዊ ዜማ ቅዱስነታቸውን እንኳን አደረሰዎ ብለዋል።
በመቀጠልም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እለቱን የሚመለከት ቅኔ በማቅረብ መርሐግብሩ ቀጥሏል። ከሊቃውንቱ ቅኔ በመቀጠል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለቅዱስነታቸው የእንኳን አደረሰዎ መልእክት ሲያቀርቡ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው በሚል ሐይለ ቃል በመነሳት የአሮጌው ዘመን ልዩ መገለጫ የሆነውን ስንፍና በሥራ ጥላቻን በፍቅር በመተካትና ዛሬን የሰጡንን የአባቶቻችንን ውለታ ባለመርሳት የቅድስት ቤተክርስቲያንን ይዞታዋን ማስከበር፣ የተጀመሩ ሕንጻዎችን ማስፈፀም፣ ቅጥር ጊቢውን ውብና ጽዱ ለማድረግ የቅዱስነታቸው ጸሎትና አባታዊ መመሪያ ዋጋው ላቅ ያለ መሆኑን ገልጸው ቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ እንዲሰጡ ጋብዘዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በዚህ መልኩ በተዘጋጀው የእንኳን አደረሰዎ መርሐግብር ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ጌታችን እና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር በሥጋ ማርያም በመገለጥ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን የቅረሰውና ደሙን ያፈሰሰው ይህንን ዓለም ለማዳንና ለማደስ ነው።
እግዚአብሔር ይህንን ዓለም አመቻችቶ ክቡር ለሆነው ለሰው ልጅ ሲሰጥ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን የጥል ግድግዳ በማፍረስና የዲያብሎስን ስልጣን በመሻር ነበር። ነገር ግን የተከፈለልንን የክርስቶስ ዋጋ የረሳ በሚመስል መልኩ እርስ በእርሳችን እየተበላላን እንገኛለን በማለት ማንኛውም አማኝ በተከፈለለት ልክ እንዲኖር አባታዊ መመሪያ ሰጥተው በቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/0025.jpg 546 360 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-04-13 09:59:342026-05-05 10:02:15የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ እንኳን አደረሰዎ መርሐግብር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሐፈት ቤት በደማቅ መንፈሳዊ ስነስርዓት ተካሄደ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በ2018 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በ2018 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ላይ ያስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በ2018 ዓ.ም የትንሣኤ... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብዝኃ ሕይወት ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ጥረቷን ለማጠናከር ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየመከረች ነው Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብዝኃ ሕይወት ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ጥረቷን ለማጠናከር ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየመከረች ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top