የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም
(ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም )
ሰኔ ፳ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም| ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 9ቀን 2018 ዓ.ም /ቁልቢ/
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅና የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም የደረሰበትን ሁኔታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በዚሁ ጊዜ የሕንጻ ቤተክርስቲያኑ የዕድሳት ሥራ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ እየተካሔደ የሚገኝ ሲሆን የግንባታ ሥራውም ሰባ ፐርሰንት ተሠርቶ የተጠናቀቀ መሆኑንና በቀሪው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የግንባታ ሥራው ተጠናቆ
ሐምሌ 17 ቀን ታቦተ ሕጉ ከመቃኞ በመውጣት ወደ ሕንጻ ቤተክርስቲያኑ እንደሚገባ አማካሪ መሐንዲሱ ፕሮፌሰር ፋሲል
እና የሕንጻ ሥራ ተቋራጩ የአዶር ኮንስትራክሽን ባለቤት ኢንጂነር አዲሱ ደመቀ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ባስተላለፉት አባታዊ የሥራ መመሪያ ቀደምት አባቶች ሠርተው ያቆዩልንን ይህን የመሰለ ጥንታዊ ገዳም ተንከባክቦና ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ በሚቻለው መጠን በርካታ ሥራዎች እየሠራን መሆኑን በተግባር የሚያረጋግጥ ሥራ በዚህ ታላቅ ገዳም እየተከናወነ ስለሆነ ቀሪ ሥራዎች የቤተክርስቲያኑን ጥንታዊነትና ታሪካዊነትን በጠበቀ መልኩ በጊዜው ተጠናቆ ለምርቃት እንዲበቃ።ጠንክራችሁ ሥሩ ካሉ በኋላ የዕድሳት ሥራውን በማከናወን ላይ የሚገኘው አዶር ኮንስትራክሽን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ሥራ እዚህ ደረጃ ላይ ማድረስ በመቻላቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
በመቀጠልሞ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት የዚህ ታሪካዊ ሥራ አካል በመሆናችን እድለኞች
ነን ካሉ በኋላ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አባታዊ አመራር ሰጪነት
ይህን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ለማደስ በመቻላችን ደስተኞች ነን ብለዋል።አያይዘውም እየተሠራ ያለው ሥራ በጣም የሚደነቅና አፈጻጸሙም የሚያስመሰግን በመሆኑ ሥራውን የምታከናውኑ ባለሙያዎችም ምስጋና ይገባችኋል ካሉ በኋላ ይህ አንጋፋ ቤተክርስቲያን የእድሳት ሥራው እጅግ በጥንቃቄ መሰራት
የሚገባው መሆኑን ተገንዝባችሁ ሥራችሁን ከአሁን በበለጠ ትጋት እንድትፈጽሙ አደራ እንላለን በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።
ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ-ኢትዮጵያ
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ ለመመልከት ዛሬ ማለዳ ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
ሁለቱ ብፁዓን አባቶችና አብረዋቸው የተጓዙት የቤተክርስቲያናችን ልዑካን ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ በርቶሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ክቡር ከንቲባ ከድር ጅዋር የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፣ክቡር መልአከ ኃይል አባ ሰላማ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ ፣ካህናትና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ብፁዓን አባቶቹና የቤተክርስቲያናችን ልዑካን በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ከተመለከቱ በኋላ በቀሪ ሥራዎች አፈጻጸም ዙሪያ መመሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት ምንም አይነት የዕድሳት ሥራ ያልተከናወነለት በመሆኑ ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርጎ መቆየቱን ተከትሎ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተእህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት አባታዊ መመሪያ ታኅሣሥ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ወዲውኑ የዕድሳት ሥራው እንዲጀመር መደረጉ ይታወሳል።
በዘመን እርዝማኔና እርጅና ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ለጉዳት ተዳርጎ የቆየው የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የዕድሳት ሥራ በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት ተጠናቆ ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ተመርቆ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል።ለዚህ ውጤታማ ሥራም የኮንትራት ሥራውን አሸንፎ የወሰደው አዶር ኮንስትራክሽን በተለይም ደግሞ የድርጅቱ ባለቤት ኢንጂነር አዲሱ ደመቀና የገዳሙ የአስተዳደር ሰራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የከፈሉት መስዋዕትነት በእጅጉ የሚደነቅ ነው።
ሰኔ 6/10/2018
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፣በግንቦት 2018 ዓ በተካሔደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቄለም ወለጋን ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ መወሰኑ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ብፁዕነታቸው ይህንኑ ኃላፊነት ለመረከብ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ደቢዶሎ ከተማ ሲያቀኑ፣በከተሣው ነዋሪዎች ምዕመናንና ምዕመናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
ብፁዕነታቸው ወደ ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት በተጓዙበት ጊዜ
ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር)፦ የኢሉ አባቦርና የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የመቱ ፈለገ ሕይወት መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ መላከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር፦ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ።በኩረ ትጉህ ቀሲስ ምትኩ ከንቲባ፦ የጠቅላይ ቤተክህነት የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ በዳሳ ቶላ፦ የጠቅላይ ቤተክህነት የሊቃውንት ጉባኤና የኮዬ ፈጬ ክፍላተ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ላዕከ ወንጌል ኃይሉ አየለ፦ የጠቅላይ ቤተክህነት ሕዝብ ግንኙነት ምክትል መምሪያ ኃላፊ፣ መጋቤ ብሉይ ሣህለ ማርያም፦ የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ።
መላከ ሄዶም ቀሲስ ግርማ ኢማና፦ የደቢዶሎ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል ።
ብፁዕነታቸው ደቢዶሎ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እንደደረሱ፤ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የማህበራት ተወካዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት፣ የነገረ መለኮት ምሩቃን እና ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በስነ-ስርዓቱ ላይም የደብረ ፀሐይ ደንቢዶሎ መድኃኔዓለም ሰንበት ተማሪዎችና የአዲስ አበባና የሸገር ሀገረ ስብከት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያሬዳዊ ዜማ አቅርበዋል።
በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር) ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት አንድነት ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ ልማት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ በሁሉም ቋንቋ በቀረበው አገልግሎት መደሰታቸውንና ይህን የመሰለ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋ አቅርበው ስለ ወለጋ ክልል ሰላም የሚነገረውና በተጨባጭ ያዩት እጅግ የተለየ መሆኑን በመጠቆም የሕዝቡ አንድነትና ፍቅር ልባቸውን እንደነካው ከገለጹ በኋላ ይህ መርሐ ግብር በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉት ሁሉ ምስጋናቸውን በማቅረብ ቃለ ምዕዳንና ቃለ በረከት አስተላልፈው የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
ዘጋቢ የላዕከ ወንጌል ኃይሉ አየለ ነው፤
ሰኔ 4ቀን 2018 ዓ.ም
አርሲ-አቦምሳ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች የተከሰተውን ችግር ተከትሎ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ በሥፍራው በመገኘት ተጎጂዎችን እንዲያጽናና ጊዜያዊ ርዳታም እንዲያደርግ
ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ዛሬ ማለዳ ወደ አርሲ ዞን አቦምሳ ወረዳ በመጓዝ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች አጽናንቷል፤ ጊዜያዊ ርዳታም አበርክቷል።
በአቦምሳ ወረዳ የትንሣኤ ብርሃን ደብረ ገነት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት ተጎጂ ኦርቶዶክሳዊያንን ያጽናኑት
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ቅድስት ቤተክርስቲያን በበኦርቶዶክሳዊያን ልጆቿ ላይ በደረሰው ጉዳት እጅግ በጣም ማዘኗን ገልጸው እግዚአብሔር አምላክ ለሞቱት ወገኖቻችን መንግስተሰማያትን እንዲያወርስልን፣ለቤተሰቦቻቸው መጽናናት እንዲያድልልን የዘወትር ጸሎታችን ነው።በርቱ፣ጠንክሩ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ብለዋል።
አያይዘውም ቋሚ ሲኖዶስ በአካል ተገኝቶ እናንተን ለማጽናናትና ጊዜያዊ ድጋፍ ለማድረግ በመካከላችሁ ተገኝተናል ያሉት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታትና የተቃጠለውን ቤተክርስቲያን ለመሥራት የሚያስቼል አቢይ ኮሚቴ በጠቅላይ ቤተክህነት ተሰይሞ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ቅድስት ቤተክርስቲያን በተከሰተው ችግር ጥልቅ ኀዘን የተሰማት መሆኑን ገልጸው ምዕመናን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ፣በፈተና ሁሉ እንዲታገሱ አደራ ካሉ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ኀዘንተኞችን እንዲያጽናና ከዳግም ኀዘን እንዲሰውርልን ዘወትር እንጸልያለን በማለት ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ለተፈናቀሉ ወገኖች የተዘጋጀውን ርዳታ ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አስረክበዋል።በዚሁ ጊዜ የአቦምሳ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች ብፁዓን አባቶችን እንኳን ደህና መጣችሁልን በማለት በሀገሩ ባህል መሰረት የሰንጋ ስጦታ ካበረከቱ በኋላ የደረሰውን ጉዳት በመኮነን ሕዝቡ በስምምነት፣
በአንድነትና በመቻል የኖረና ወደፊትም የሚኖር ሕዝበብ መሆኑን ጠቅሰው የተፈጠረውን ችግር ሃይማኖታዊ መልክ ለማስያዝ የሚደረገው ጥረት ተገቢነት የሌለው ነው ብለዋል።ለብፁዓን አባቶች የተበረከተው የሰንጋ ስጦታም ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲደርስ ተደርጎ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
ሰኔ ፪ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓ/ም
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተፈጠረው የኦርቶዶክሳውያን ግድያና የቤተ ክርስቲያን መቃጠል ኃዘናቸውን ገልጸው በብፁዕነታቸውን መመሪያ ሰጪነት የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ፈቃደኛ መሆናቸውን አሳወቁ።
አስተዳዳሪዎቹ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በተካሄደው የጋራ ስብሰባ ለጽድቅና ለመንግሥተ ሰማይ ዓላማ የሚሰበሰብ የቤተክርስቲያን ገቢ አስመልክቶ ውይይትና ምክክር በተደረገበት ስብሰባ ላይ ነው።
በስብሰባው ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ወና ሥራ አስኪያጅ ፣ መጋቤ ትፍስሕት ሙሉጌታ ቸርነት የሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች ፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አክኪያጆች፣ የገዳማትና አድባራት እእተዳዳሪዎች የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነትና የአድባራት የሒሳብ ሹሞች ተገኝተዋል።
የስብሰባው ጉዳይ እውነተኞች ምዕመናን የሰጡትንና በተለያዩ የሰዋዊና ቁሳዊ ልማት ምክንያት ለቤተ ክርስቲያን ገቢ ያደረጉትን ገንዘብ ሕግና አሠራርን በመጠበቅ ቤተ ክርስቲያን ለተመሠረተችበት ሕያው ዓላማና መንፈሳዊ ሥራ ላይ አገልግሎት ላይ ይውል ዘንድ ምክክር ለማድረግ የተጠራ ስብሰባ እንደሆነ ተገልጿል።
በጉባኤውም በሀገረ ስብከቱ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሐላፊ ሊቀ ኅሩያን አስናቀ ሸዋየ አጭር ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በዚህ መነሻነትም ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ክርስቲያናት የያሉ ተሳታፊዎች ሐሳብና አስተያየት ሰጥተዋል።
አስተያያት ሰጪዎቹ እንዳሉት የቤተ ክርስቲያን ገቢዎችን ሕግና አሠራርን ጠብቆ ለተገቢው ዓላማ መዋል፣ ተቋማዊ ተናብቦትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ሁሉ የተፈጠሩ ችግሮችና ቁስሎችን የጋራ በማድረግ ከግል ፍላጎትና ሐሳብ ይልቅ ቤተ ክርስቲያን በማስቀድም መሥራት በሚሉ ጉዳዮች ላይ አስተያያቶች ቀርበዋል።
በተለይም በሀገረ ስብከቱ ደረጃ እየተለመዱ የመጡ ዘመኑን ያነበቡና ችግር በችግር ሳይሆን በመፍትሔ እናክማቸውን በሚል መንገድ የተጀመሩ የውስጥ አሠራሮችና የተጨባጥ የሆኑ የራስ አገዝ ልማቶች በእጅጉ የሚበረታቱና የሚያስመሰግኑ መሆናቸውን ከከፍተኛ አድናቆት ጋር ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስና መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱን የሥራ ሐላፊዎች አመስግነዋል።
በሌላ በኩል አስተዳዳሪዎቹ በገጠሪቱ ያለቸው ቤተ ክርስቲያን ስታነባ ያመናል ፤ ቁስሏም ይጠዘጥዘናል፤ በመሆኑም በሰሙኑ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ መመሪያ ሰጪነት ተባብረን ለመሥራት ፈቃደኛ መሆናችን እንገልጻለን ብለዋል።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ በበኩላቸው በብፁዕነታቸው የሚመራው ሀገረ ስብከት ነገን በማሰብ ዛሬ ላይ አቅዶ እየሠራ በመሆኑን በማስታወስ በዚህ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችን የሥራ ሐላፊዎች ድርሻቸው ሰፊ ነው ብለዋል።
አክለውም የተቀበልነው ሕያው ተልእኮ ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ብቻ ሳይሆን በታማኝነት በመንፈሳዊ ትርፍ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለቀጣዩ ትውልድ በክብር የማስተላላፍ ድርሻ አለብን ለዚህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ገቢ በአግባቡ መጠበቅና ቤተ ክርስቲያን ጠቀም ሥራዎችን በመሥራት መሆን አለበት ብለዋል።
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የተሰጠንን ሐላፊነት በአግባቡ መተርጎምና ለቤተ ክርስቲያን ብልጫ ላለው አገልግሎት ማውል ይኖርብናል ያሉ ሲሆን በተለይም አሠራራችን ዘመኑን የዋጀ፣ ለምእምናን ቅርብ የሆነና ዘላቂ ለውጥ ላይ መሠረት ያደረገ መሆን አለበት ብለዋል።
ቀጥለውም የቤተ ክርስቲያን ገቢ ከምእመናን መቀነት እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚደርስ መስመር ያለው ተቋማዊ አሠራር ያለው በመሆኑ አልቅሳ አንብታ ለሐጢአት ሥርየት ብላ የምትሰጥውን የአንዲት ምእመን ስጦታና ዛሬን ለነገ እናሻግር በሚል መርሕ የተሠሩ የራስ አገዝ ልማቶች ገቢዎች በሰዓቱ መሰብሰብና ለታለመው ዓላማ ማዋል ይገባናል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሁሉም አህጉረ ስብከት ደጋፊ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና መጋቢ የሁሉ መጠጊያ እንደሆነ የገለጹት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ በቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ህልውና እና ተልእኮ ማስፈጸም ረገድ ድርሻው ሰፊ ነው ብለዋል።
በመሆኑም የሰው ልማት ላይና የተቋማት ዕድገት ላይ በእጅጉ መሥራት እንደሚገባው የተጠቆሙት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሚሠሩ ወንጌልን የሚስፋፋባቸው፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሚረዱበት እና ራሳቸውን ያልቻሉ አህጉረ ስብከት የሚደጎሙበት ሁሉን አቀፍ የራስ አገዝ ልማቶች ላይ በማገዝ ትልቁን ድርሻ እንደሚወጣ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በተለያዩ አህጉረ ስብከት በበምእመናንና በአብያተ ክርስቲያናት ጉዳት ሲያጋጥም ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያዘው በፍጥነት ለችግር የሚደርስ ሀገረ ስብከት መሆኑ ይታወቃል።
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ግንቦት 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጠረው ጥቃት ንጹሐን ምእመናን በግፍ እንደሞቱና ከመቶ ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንደተቃጠለ የሚታወስ ነው ነው።
©የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ