የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

June 11, 2026

ሰኔ ፪ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓ/ም
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተፈጠረው የኦርቶዶክሳውያን ግድያና የቤተ ክርስቲያን መቃጠል ኃዘናቸውን ገልጸው በብፁዕነታቸውን መመሪያ ሰጪነት የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ፈቃደኛ መሆናቸውን አሳወቁ።
አስተዳዳሪዎቹ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በተካሄደው የጋራ ስብሰባ ለጽድቅና ለመንግሥተ ሰማይ ዓላማ የሚሰበሰብ የቤተክርስቲያን ገቢ አስመልክቶ ውይይትና ምክክር በተደረገበት ስብሰባ ላይ ነው።
በስብሰባው ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ወና ሥራ አስኪያጅ ፣ መጋቤ ትፍስሕት ሙሉጌታ ቸርነት የሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች ፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አክኪያጆች፣ የገዳማትና አድባራት እእተዳዳሪዎች የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነትና የአድባራት የሒሳብ ሹሞች ተገኝተዋል።
የስብሰባው ጉዳይ እውነተኞች ምዕመናን የሰጡትንና በተለያዩ የሰዋዊና ቁሳዊ ልማት ምክንያት ለቤተ ክርስቲያን ገቢ ያደረጉትን ገንዘብ ሕግና አሠራርን በመጠበቅ ቤተ ክርስቲያን ለተመሠረተችበት ሕያው ዓላማና መንፈሳዊ ሥራ ላይ አገልግሎት ላይ ይውል ዘንድ ምክክር ለማድረግ የተጠራ ስብሰባ እንደሆነ ተገልጿል።
በጉባኤውም በሀገረ ስብከቱ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሐላፊ ሊቀ ኅሩያን አስናቀ ሸዋየ አጭር ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በዚህ መነሻነትም ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ክርስቲያናት የያሉ ተሳታፊዎች ሐሳብና አስተያየት ሰጥተዋል።
አስተያያት ሰጪዎቹ እንዳሉት የቤተ ክርስቲያን ገቢዎችን ሕግና አሠራርን ጠብቆ ለተገቢው ዓላማ መዋል፣ ተቋማዊ ተናብቦትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ሁሉ የተፈጠሩ ችግሮችና ቁስሎችን የጋራ በማድረግ ከግል ፍላጎትና ሐሳብ ይልቅ ቤተ ክርስቲያን በማስቀድም መሥራት በሚሉ ጉዳዮች ላይ አስተያያቶች ቀርበዋል።
በተለይም በሀገረ ስብከቱ ደረጃ እየተለመዱ የመጡ ዘመኑን ያነበቡና ችግር በችግር ሳይሆን በመፍትሔ እናክማቸውን በሚል መንገድ የተጀመሩ የውስጥ አሠራሮችና የተጨባጥ የሆኑ የራስ አገዝ ልማቶች በእጅጉ የሚበረታቱና የሚያስመሰግኑ መሆናቸውን ከከፍተኛ አድናቆት ጋር ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስና መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱን የሥራ ሐላፊዎች አመስግነዋል።
በሌላ በኩል አስተዳዳሪዎቹ በገጠሪቱ ያለቸው ቤተ ክርስቲያን ስታነባ ያመናል ፤ ቁስሏም ይጠዘጥዘናል፤ በመሆኑም በሰሙኑ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ መመሪያ ሰጪነት ተባብረን ለመሥራት ፈቃደኛ መሆናችን እንገልጻለን ብለዋል።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ በበኩላቸው በብፁዕነታቸው የሚመራው ሀገረ ስብከት ነገን በማሰብ ዛሬ ላይ አቅዶ እየሠራ በመሆኑን በማስታወስ በዚህ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችን የሥራ ሐላፊዎች ድርሻቸው ሰፊ ነው ብለዋል።
አክለውም የተቀበልነው ሕያው ተልእኮ ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ብቻ ሳይሆን በታማኝነት በመንፈሳዊ ትርፍ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለቀጣዩ ትውልድ በክብር የማስተላላፍ ድርሻ አለብን ለዚህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ገቢ በአግባቡ መጠበቅና ቤተ ክርስቲያን ጠቀም ሥራዎችን በመሥራት መሆን አለበት ብለዋል።
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የተሰጠንን ሐላፊነት በአግባቡ መተርጎምና ለቤተ ክርስቲያን ብልጫ ላለው አገልግሎት ማውል ይኖርብናል ያሉ ሲሆን በተለይም አሠራራችን ዘመኑን የዋጀ፣ ለምእምናን ቅርብ የሆነና ዘላቂ ለውጥ ላይ መሠረት ያደረገ መሆን አለበት ብለዋል።
ቀጥለውም የቤተ ክርስቲያን ገቢ ከምእመናን መቀነት እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚደርስ መስመር ያለው ተቋማዊ አሠራር ያለው በመሆኑ አልቅሳ አንብታ ለሐጢአት ሥርየት ብላ የምትሰጥውን የአንዲት ምእመን ስጦታና ዛሬን ለነገ እናሻግር በሚል መርሕ የተሠሩ የራስ አገዝ ልማቶች ገቢዎች በሰዓቱ መሰብሰብና ለታለመው ዓላማ ማዋል ይገባናል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሁሉም አህጉረ ስብከት ደጋፊ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና መጋቢ የሁሉ መጠጊያ እንደሆነ የገለጹት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ በቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ህልውና እና ተልእኮ ማስፈጸም ረገድ ድርሻው ሰፊ ነው ብለዋል።
በመሆኑም የሰው ልማት ላይና የተቋማት ዕድገት ላይ በእጅጉ መሥራት እንደሚገባው የተጠቆሙት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሚሠሩ ወንጌልን የሚስፋፋባቸው፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሚረዱበት እና ራሳቸውን ያልቻሉ አህጉረ ስብከት የሚደጎሙበት ሁሉን አቀፍ የራስ አገዝ ልማቶች ላይ በማገዝ ትልቁን ድርሻ እንደሚወጣ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በተለያዩ አህጉረ ስብከት በበምእመናንና በአብያተ ክርስቲያናት ጉዳት ሲያጋጥም ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያዘው በፍጥነት ለችግር የሚደርስ ሀገረ ስብከት መሆኑ ይታወቃል።
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ግንቦት 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጠረው ጥቃት ንጹሐን ምእመናን በግፍ እንደሞቱና ከመቶ ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንደተቃጠለ የሚታወስ ነው ነው።
©የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000012.jpg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-06-11 03:57:542026-06-11 03:57:54“በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ። Link to: ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ። ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት... Link to: በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ። Link to: በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ። በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top