የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

June 28, 2026
(ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም )
አንጋፋውና ታሪካዊው የባቱ (ዝዋይ) ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ በሥራ አመራር የዲፕሎማ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 23 ደቀ መዛሙርት እንዲሁም በ67ኛው ዙር የሦስት ወራት የካህናት ማሠልጠኛ ክፍል የተከታተሉ 36 ዕጩ አገልጋዮችን በድምሩ 59 ተተኪ መምህራንንና አገልጋዮችን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል።
ይህ ታላቅ የምረቃ መርሐ ግብር በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የጋራ ጸሎት የተከፈተ ሲሆን፣ የዕለቱ የቅዱስ ወንጌል ንባብ በብፁዕ አቡነ ማርቆስ አማካኝነት ቀርቦ ሥነ-ሥርዓቱ በይፋ ተጀምሯል።
በበዓሉ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የኮሌጁና የገዳሙ የበላይ ኃላፊ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ (ሳልሳዊ) እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የኮሌጁና የገዳሙ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፦ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የእንኳን ደህና መጣችሁ፣ ለተመራቂ ደቀ መዛሙርት ደግሞ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት በማስተላለፍ ሰፊ አባታዊ መመሪያና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል።
ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክትም ፦ “የተማራችሁት የሥራ አመራር ሳይንስና የተቀበላችሁት የካህናት ሥልጠና፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በዘመናዊ አሠራርና በጥንታዊው መንፈሳዊ ሥርዓት አስተባብሮ ለመምራት ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው” ብለዋል።
አያይዘውም ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት አብርተው፣ እንደ ጨው አልጭተው፣ የወቅቱን ፈተናዎች በጽናት በማሸነፍና ትውልዱን በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በመቅረጽ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮና ትውፊት በተግባር እንዲያስጠብቁ አደራ ብለዋል።
በተለይም ደግሞ በዕውቀትና በአገልግሎት እጥረት ምክንያት ፈተና በበዛባቸው የአህጉረ ስብከቱ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ላይ በመገኘት፣ ሕዝበ ክርስቲያኑን በማስተማርና ወንጌልን በማስፋፋት አገልጋይነታቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ መመሪያ ሰጥተዋል።
በመቀጠል ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ባስተላለፉት ቃለ ምዕዳን፣ እርሳቸውም የዚሁ የቅዱስ ገብርኤል ገዳም ፍሬ መሆናቸውን በኩራት ገልጸው ታሪክን ወደ ኋላ በመመለስ የገዳሙን መሠረት አስታውሰዋል። ትናንት በችግርና በጥቂት ጅማሮ የነበረው ገዳም፣ ዛሬ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ መሪነት ሁለንተናዊና አርአያነት ያለው የልማትና የትምህርት ማእከል መሆኑን በማነጻጸር አብራርተዋል። ይህ ስኬት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ አገርን ለሚረከበው ተተኪ ትውልድ ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።
የገዳሙ አበምኔት ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ አትናቴዎስ በበኩላቸው፣ የ67ኛ ዙር የካህናት ሥልጠና 36 ደቀ መዛሙርት መመረቃቸውን አብስረው፣ የገዳሙን ታሪካዊ ጉዞና ልማት አብራርተዋል።
አበምኔቱ ባደረጉት ንግግር፤ የቀድሞው የሸዋ ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ (ካልዕ) የነበረውን ታላቅ ራእይና ዓላማ በመንተራስ፣ የአሁኑ የገዳሙ የበላይ ጠባቂና የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ (ሳልሳዊ) ላለፉት 31 ዓመታት ገዳሙ ዛሬ ለደረሰበት የከፍታ ደረጃ እንዲበቃ የከፈሉትን ታላቅ መሥዋዕትነትና ያሳዩትን የረጅም ርቀት አርቆ አሳቢነት በዝርዝር አብራርተዋል።
አያይዘውም በብፁዕነታቸው አርቆ አሳቢነትና መሪነት ተቋሙን ወደ ፊት ወደ “ዩኒቨርሲቲ” ደረጃ ለማሳደግ ታላቅ ዓላማ ተይዞ በገዳሙ ውስጥ የማይጠፉ ዘላቂ አሻራዎች እየተቀመጡ መሆናቸውን ገልጸው፤ በባቱ ከተማ ላይ እየተገነባ የሚገኘውን ግዙፍ የG+8 ሕንጻ የግንባታ ሂደት በመጥቀስ፣ ገዳሙ ወደፊት በራስ አገዝ ልማት ራሱን እንዲያስተዳድር እየተደረገ ያለውን ጥረት ገልጸዋል።
የሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጁ ዲን መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ታፈሰ ስለ ተቋሙ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት 5ኛ ዙር ላይ መድረሱንና እስካሁን 123 ደቀ መዛሙርትን ማፍራቱን ጠቅሰው፣ ዘንድሮ ደግሞ 23 ተማሪዎችን ለምረቃ ማብቃታቸውን ገልጸዋል። ኮሌጁ ከአራቱም አቅጣጫዎች ከተለያዩ አህጉረ ስብከት መሥፈርቱን አሟልተው የመጡ ሰልጣኞችን ተቀብሎ የሚያስተምር መሆኑን ጠቁመው፤ የሥራ አመራር ተማሪዎቹ በቆይታቸው ከተለመደው ትምህርት በተጨማሪ በገዳሙ የአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ በመግባት የቅኔ ትምህርት መቁጠራቸውን በልዩ ስኬትነት አንስተዋል። አያይዘውም ኮሌጁ አድማሱን በማስፋት በአዲስ አበባ፣ በአዳማና በአርባ ምንጭ በርቀት የትምህርት መርሐ ግብር እያስተማረ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በዕለቱ የኮሌጁ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል።
የባቱ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሁስማን ተስሔ በምረቃው ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር የምታስተምረው ሰላምን መሆኑን ገልጸው፤ ገዳሙ ከመንፈሳዊ አገልግሎቱ ጎን ለጎን ማኅበረሰቡን በሥራ አመራር ሳይንስ ማስተማሩና በልማት ላይ እያሳየ ያለው ከፍተኛ ተሳትፎ ለአካባቢው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አረጋግጠዋል። ልማትና ሰላም የማይነጣጠሉ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በጥቂቱ የተጀመረው ይህ ታላቅ ተቋም ዛሬ ለደረሰበት የከፍታ ደረጃ ለገዳሙና ለአባቶች የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ማጠናቀቂያ ላይ፣ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ የደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጀው ልዩ የክብር ሽልማት፤ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እጅ የተበረከተላቸው ሲሆን፣ ተመራቂዎቹም የአባቶችን አምላካዊ ቡራኬ በመቀበል ሽልማታቸውን ተረክበዋል።
በዚህ ደማቅ የበዓል መርሐ ግብር ላይ በገዳሙ የቅኔ መምህርና በተመራቂ ደቀ መዛሙርት አማካኝነት ቅኔ እንዲሁም ያሬዳዊ ወረብ ቀርቦ ሥነ ሥርዓቱ በጸሎት ተጠናቋል።
በምረቃ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ የሀገረ ስብከታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሣሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከታችን ም/ሥራ አስኪያጅ: የሀገረ ስብከታችን የመመሪያው ክፍል ኃላፊዎች፣ የኮሌጁና የገዳሙ የየክፍሉ ኃላፊዎች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ ተመራቂዎችና ወላጆቻቸው አባ ገዳዎች አደ ሥንቄዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የዕለቱን ታላቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓትና አጠቃላይ መርሐ ግብር በብፁዕነተታቸው አባታዊ መመሪያ እና በወጣው ቅደም ተከተል መሠረት በከፍተኛ ትጋት የመሩት የሥራ አመራር ኮሌጁ የሬጅስትራር ክፍል ዋና ኃላፊ መምህር ዲበ ኩሉ ጌታነህ እና በአፋን አሮሞ የገዳማችን ቁጥጥር ናቸው።”
© ሐመረ ተዋሐደ ሚዲያ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000020.jpeg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-06-28 13:24:542026-06-28 13:24:54“ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛውን ዙር የነገረ መለኮት ደቀ መዛሙርት በታላቅ ድምቀት አስመረቀ። Link to: የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛውን ዙር የነገረ መለኮት ደቀ መዛሙርት በታላቅ ድምቀት አስመረቀ። የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሁለተኛውን... Link to: የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ። Link to: የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ። የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top