የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡

July 1, 2026
ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና ዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ በዘመናዊ የዲጂታል ዓለም ውስጥ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ተደራሽ ማድረግ የምትችልባቸውንና አስተዳደራዊ አቅሟን ለማሳደግ የሚረዱ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦችንና ስልታዊ ጥናቶችን በማቅረብ እንዲሠራ የተቋቋመ ኮሚቴ ነው፡፡
የኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ ዮሐንስ ተስፋዬ ለአስተዳደር ጉባኤ ባቀረቡት ጥናት “ቤተክርስቲያን በቴክኖሎጂ የዳበረ ዘመናዊ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ሥርዐትን ለመገንባት ከመንፈሳዊ እሴቶች ጋር የተጣጣመ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ ለቀጣይ ትውልድ አገልግሎት መስጠት የሚችል የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደሚያስፈልጋት አስረድተዋል፡፡
የዲጂታል ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤትክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ለማስፋፋት፣ አስተዳደሯን ለማዘመን፣ የፋይናንስ ሥራዎቿን ለማቀላጠፍ፣ የቤተክርስቲያን ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርሶቿን ለማስጠበቅና ለማስተዳደር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስቀድሞ ለአገልግሎት ትጠቀምባቸው የነበሩ ሀርድ ኮፒዎች ዲጂታይዝ ለማድረግ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና ዲጂታል ሽግግር አማካሪ ስትራቴጂክ ሰነድ መዘጋጀቱን ሰብሳቢው ገልጸዋል።
ቤተክርስቲያን ለዘመናት የቆዩ የብራና መጻሕፍት፣ የቅኔ፣ የያሬዳዊ ዜማዎችና የቅዱሳት ሥዕላት ባለቤት መሆኖከአጥቢያ እስከ መንበረ ፓትርያርክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ካህናትና ምእመናንን የምትመራ ቢሆንም እነዚህ ሁሉ ትላልቅ መረጃዎችና መዛግብት ግን በአንድ ላይ ተሰንደው ከመቀመጥ ይልቅ በተበታታነ ሁኔታ እንደሚገኙ ተገልጿል። በመሆኑም የቤተክርስቲያን ቅርስና ሀብት ዘመኑ የሚጠይቀውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ በመጠቀም በአንድ ማዕከል ሠንዶ ማስቀመጥ እንደሚገባ ሰብሳቢው አስገንዝበዋል ፡፡
የአስተዳደር ጉባኤ አባላቱም በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አመራር ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረትና የተከናወኑ ተግባራትን በማድነቅ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፤ እነዚህ ትላልቅ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው በአዲሱ በጀት ዓመት ተግባራዊ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጥናቱን በማዘጋጀት ያቀረቡ የኮሚቴ አባላትን አመስግነው፤ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት በግንቦት ፳፻፲፰ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አጀንዳው መቅረቡን ጠቅሰዋል። ምልዓተ ጉባኤውም በአጀንዳውና የቀረቡለት የተለያዩ ሥራዎችን በመገምገም የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መመሪያ መስጠቱን አውስተዋል።ዛሬ የቀረቡትም የተለያዩ የጥናት ሰነዶችም ይህንኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት በማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በብፁነታቸው የተመራው የአስተዳደር ጉባኤ አባላት በመንበረ ፓትርያተርክ ቅጽር ግቢ የሚሠራውን የልማት ሥራ ተመልክተውዋል፤ በተለይም ለብፁዓን አባቶች ማረፊያ ቤት አጠገብ የሚሠራውን ግንባታ በልዩ ትኩረት በአፋጣኝ ተሠርቶ እንዲጠናቀቅ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡©Eotc tv
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000023.jpg 299 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-01 19:29:432026-07-01 19:29:43በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ። Link to: የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ። የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን ... Link to: የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ። Link to: የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ። የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top