የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።

June 16, 2026

ሰኔ 9ቀን 2018 ዓ.ም /ቁልቢ/
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅና የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም የደረሰበትን ሁኔታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በዚሁ ጊዜ የሕንጻ ቤተክርስቲያኑ የዕድሳት ሥራ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ እየተካሔደ የሚገኝ ሲሆን የግንባታ ሥራውም ሰባ ፐርሰንት ተሠርቶ የተጠናቀቀ መሆኑንና በቀሪው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የግንባታ ሥራው ተጠናቆ
ሐምሌ 17 ቀን ታቦተ ሕጉ ከመቃኞ በመውጣት ወደ ሕንጻ ቤተክርስቲያኑ እንደሚገባ አማካሪ መሐንዲሱ ፕሮፌሰር ፋሲል
እና የሕንጻ ሥራ ተቋራጩ የአዶር ኮንስትራክሽን ባለቤት ኢንጂነር አዲሱ ደመቀ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ባስተላለፉት አባታዊ የሥራ መመሪያ ቀደምት አባቶች ሠርተው ያቆዩልንን ይህን የመሰለ ጥንታዊ ገዳም ተንከባክቦና ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ በሚቻለው መጠን በርካታ ሥራዎች እየሠራን መሆኑን በተግባር የሚያረጋግጥ ሥራ በዚህ ታላቅ ገዳም እየተከናወነ ስለሆነ ቀሪ ሥራዎች የቤተክርስቲያኑን ጥንታዊነትና ታሪካዊነትን በጠበቀ መልኩ በጊዜው ተጠናቆ ለምርቃት እንዲበቃ።ጠንክራችሁ ሥሩ ካሉ በኋላ የዕድሳት ሥራውን በማከናወን ላይ የሚገኘው አዶር ኮንስትራክሽን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ሥራ እዚህ ደረጃ ላይ ማድረስ በመቻላቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
በመቀጠልሞ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት የዚህ ታሪካዊ ሥራ አካል በመሆናችን እድለኞች
ነን ካሉ በኋላ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አባታዊ አመራር ሰጪነት
ይህን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ለማደስ በመቻላችን ደስተኞች ነን ብለዋል።አያይዘውም እየተሠራ ያለው ሥራ በጣም የሚደነቅና አፈጻጸሙም የሚያስመሰግን በመሆኑ ሥራውን የምታከናውኑ ባለሙያዎችም ምስጋና ይገባችኋል ካሉ በኋላ ይህ አንጋፋ ቤተክርስቲያን የእድሳት ሥራው እጅግ በጥንቃቄ መሰራት
የሚገባው መሆኑን ተገንዝባችሁ ሥራችሁን ከአሁን በበለጠ ትጋት እንድትፈጽሙ አደራ እንላለን በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000016.jpg 336 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-06-16 15:38:392026-06-16 15:38:39ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
  • ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ። Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ። ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top