ኋላ ቀር የገንዘብ አስተዳደርን በማዘመን የደንበኞችን ውጣ ውረድ የማስቀረት ዓላማን ያነገበው የሞባይል ባንኪንግ አገልግልግሎት በይፋ ተመርቆ ተግባራዊ ተደረገ

ሚያዚያ ፲፭ ቀን ፳፻፲ወ፰ዓ.ም.
ኢኦተቤክ ቤሕአልድ
አዲስአበባ ኢትዮጵያ
የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ይዞት የተነሳውን የደንበኛ ተኮር አስተዳደር ስርዓት አካል የሆነው የዘመናዊ ገንዘብ አስተዳደር ቴክኖሎጂ ማበልጸግ ተግባራዊ ለማድረግ ከበርካታ ባንኮች ፣ ድርጅቶችና ኤጀንትቶች አማራጭ መንገዶችን ለማየት ተደጋጋሚ ውይይቶችን ማድረጉን መዘጋባችን የሚታወስ ነው።
የቀረቡት አማራጮች ሙሉ በሚባል ደረጃ የሚያጓጉ ቢሆኑም ድርጅቱ ጥበብ በተሞላው ምርጫ በመምረጥ ከዐባይ ባንክ አክስዮን ማኅበር አራት ኪሎ ቅርንጫፍ ጋር ለመሥራት የወሰነ ሲሆን ባንኩ ያቀረበው አማራጭ እጅግ ዘመኑን የዋጀና በቀላል መንገድ ሊተገበር የሚችል መሆኑ ታይቶ ስምምነት ተደርጓል ።
በስምምነቱ ደንበኞች ያለምን ውጣ ውረድ ኪያራያቸውን በሞባይል ባንኪን እንዲከፍሉ ማድረግ፣ የመክፈያ ጊዜ ሲደርስ ማስታዎሻ መልእክት መላክ፣ ከክፍያ በኋላ አመስግኖ መቀበል፣ ጊዜው ያለፈባቸውን ከፋዮች ከእነቅጣታቸው እንዲከፍሉ ማንቃትና የመሳሰሉትን የሚተገብር ነው ተብሏል።
ይህንን ቴክኖሎጂ መላው ደንበኞች ተጠቃሚ በመሆን ክፍያን ከፍለው ደረሰኝ ለማወራረድ የሚያባክኑትን ጊዜ ይቆጥባሉ ተብሎ ይታመናል።
ይህ የደንበኞችን ልብ በሐሴት የሞላው ዘመናዊው የኪራይ አሰባሰብ ስርዓት በዛሬው እለት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
ክቡር ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር በማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ
ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ የጠቅላይ ቤተክህነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፤
ክቡራን የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎችና የየድርጅቶች ሥራ አስኪያጆች፤
ክቡራን እና ክቡራት የድርጅቱ ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።