የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

እናንተ የነገዋ ቤተክርስቲያን ተስፋዎች ናችሁ:- ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬ 11 ደቀመዛሙርት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተመረቁ።

July 11, 2026
ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የከምባታ ሀላባና ጠምባሮ ሀገረ ስብከት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በአብነት ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 11 ደቀመዛሙርት በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ በታላቅ ድምቀት ተመርቀዋል።
በሀገረ ስብከቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ይህ የምረቃ መርሐ ግብር የቤተክርስቲያንን መንፈሳዊ የትምህርት ጥራትና የሰው ኃይል ግንባታ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ታሪካዊ ክንውን ሆኖ አልፏል።
የምረቃ መርሐ ግብሩ በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ ሚካኤል ታደሰ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን አባ ሚካኤል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው ባለፉት ሁለት ዓመታት ደቀ መዛሙርቱ በጽናት የያዙትን የአብነት ትምህርት ጉዞ አስመልክቶ አጠቃላይ ሪፖርት አቅርበዋል።
ለዚህ ታላቅ ዕለት መሳካት የብፁዕ አባታችንን አባታዊ ንቃትና ቀጥተኛ አስተዋጽኦ በጉልህ የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ ማህበረ ቅዱሳን ላደረገው የላቀ ድጋፍና ተሳትፎ በሀገረ ስብከቱ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዕለቱ የከምባታ ሀላባ ጠምባሮና የዳውሮ ኮንታ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በሰጡት አባታዊ ቃለ ምዕዳን ምሩቃኑን “የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ” በማለት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ብፁዕነታቸው አያይዘውም “እድልን የሰጠን እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር የራሱ ጊዜ አለውና በራሱ ጊዜ ሁሉን ፈፅሟል በማለት ገልጸው ማህበረ ቅዱሳን ይህንን የአብነት ትምህርት ቤት ከ4 ዓመታት በኋላ ገንብተው በማጠናቀቅ ትልቅ ድጋፍ ቢያደርጉም አነሆ ህንጻውን ዛሬ ህያው ያደረጋችሁት ግን እናንተ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ ናችሁ” በማለት ለምሩቃኑ ያላቸውን አባታዊ አድናቆት ገልጸዋል።
ለአንድ ሀገረ ስብከት 11 ደቀ መዛሙርትን ማስመረቅ ቁጥሩ ትንሽ መስሎ ቢታይም እናንተ ግን ለእኛ ከ100 በላይ ናችሁ በማለት የገለጹ ሲሆን ምክንያቱም ብዙ የተዘጉብን አብያተ ክርስቲያናት ስላሉ እናንተ ከካህናቱ ጎን በመሆን ያንን ቤተ ክርስቲያን መክፈትና ህዝበ ክርስቲያኑን ማስተማር ይጠበቅባችኋል ሲሉ ብፁዕነታቸው አደራቸውን ጥለዋል።
ደቀ መዛሙርቱ ከቤተሰብ ተለይተው በሚኖሩበት ወቅት ክፍተት እንዳይሰማቸው ሀገረ ስብከቱ በበዓላት የጾም መዋያ ፣ የንጽህና መጠበቂያና አልባሳትን በማቅረብ ከፍተኛ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውሰዋል።
በተጨማሪም ብፁዕነታቸው እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ አሜሪካ በሚገኙት የሲያትል ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ክቡር መልአከ ሳህል አወቀና መልአከ ኃይል አባ ሰይፈ ገብርኤል ምዕመናንን በማስተባበር ደቀ መዛሙርቱ ወደየአጥቢያቸው ሲመሉ መብዓ ይዘው መሄድ አለባቸው በማለት መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ዕጣን ፣ ዘቢብና ጧፍ እንዲሁም የጉዞ ብር ድጋፍ ስላደረጉ በራሳቸውና በሀገረ ስብከቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዕለቱ የሪፖርት አቅራቢ የነበሩት የማህበረ ቅዱሳን ዱራሜ ማዕከል ሰብሳቢ ዲ/ን ታገሰ ሀንዴቦ ማህበሩ የቤተክርስቲያንን የአብነት ትምህርት ቤቶች ለማጠናከር ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ ከ170 በላይ ፕሮጀክቶችን መደገፉን ገልጸው በዘንድሮው ዓመት ብቻ ለ177 የትምህርት ተቋማት፣ ለ2001 ቀሳውስትና ለ238 መምህራን ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉንና ከ17 በላይ አዳዲስ ተቋማት በመገንባት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዲ/ን ታገሰ ምሩቃኑ የያዙትን ዕውቀት ለቤተክርስቲያን እድገት እንዲያውሉት ጥሪ አቅርበው ማህበሩ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም ለ11ዱም ደቀ መዛሙርት የዕውቅና ሰርተፍኬት ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ለሀገረ ስብከቱ ፣ ለመምህራንና ለዱራሜ መንበረ ጵጵስና ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የዕውቅናና የምስጋና ሽልማት በመስጠት መርሐ ግብሩ በብፁዕ አባታችን ቡራኬ ፍፃሜውን አጊንቷል።
© ዜና ጎርጎርዮስ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000033.jpeg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-11 18:58:482026-07-11 18:58:48እናንተ የነገዋ ቤተክርስቲያን ተስፋዎች ናችሁ:- ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬ 11 ደቀመዛሙርት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት ተመረቁ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲግሪ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ሊቃውንት በድምቀት አስመረቀ Link to: የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲግሪ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን ሊቃውንት በድምቀት አስመረቀ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ... Link to: የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ያስገነባው መንበረ ጵጵስና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተመረቀ። Link to: የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ያስገነባው መንበረ ጵጵስና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተመረቀ። የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ያስገነባው መንበረ ጵጵስና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top