የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ላይፍ አዲስ ሆስፒታል ከቤተክርስቲያን ተከራይቶ በዘመናዊ መንገድ የሚያሳድሰውን ሆስፒታል በብፁዓን አባቶች አስጎበኘ።

July 5, 2026
ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
የላይፍ አዲስ ሆስፒታል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት
የተከራየውን ሕንጻና የሕክምና ተቋም አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማዘመንና ዓለም አቀፍ መሥፈርቶችን ወደሚያሟላ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር የጀመረውን ሰፊ የእድሳትና የማስፋፊያ ሥራ አሁናዊ አፈጻጸም ለመገምገም የሚያስችል የሱፐርቪዥን ጉብኝት ተካሂዷል።
በዚህ መርሐ-ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ የሐድያና ስልጤ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቀ ሥዩማን እስክንድ ገብረ ክርስቶስ የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ኀላፊ የመንበረ ፓትርያርክ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የሆስፒታሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰፊ ምልከታ ተደርጓል።
የላይፍ አዲስ ሆስፒታል ከተከራየው የቤተክርስቲያኗ ይዞታ ላይ የመሠረተ-ልማት አደረጃጀቱን ለመለወጥና ተቋሙን በዘመናዊ መልክ ለመቅረጽ እያከናወነ ያለው አጠቃላይ የእድሳት እንቅስቃሴ አበረታች ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በጉብኝቱ ወቅት ተመልክቷል። በተደረገው ምልከታ፣ ብፁዓን አባቶችና የሥራ ኃላፊዎቹ አጠቃላይ የሆስፒታሉን የውስጥ ክፍሎች ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን፣ ክፍሎቹ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ጠብቀው ሙሉ የላቦራቶሪና የሕክምና አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት መልኩ ሰፊ የብርሃንና የቦታ አጠቃቀምን ታሳቢ አድርገው እየተገነቡ መሆኑ በማብራሪያው ላይ ተገልጿል።
በተጨማሪም ሆስፒታሉ ለብፁዓን አባቶችና ለክቡራን እንግዶች የሚመጥን ልዩ የቪአይፒ (VIP) የእንግዳ መቀበያና ማረፊያ ቦታዎችንም ጭምር ያካተተ ዘመናዊ አደረጃጀት ማዘጋጀቱ ተገልጿል።
በመቀጠልም በሆስፒታሉ ውስጥ ለተለያዩ የሕክምና ዘርፎችና ለታካሚዎች ማቆያነት የተዘጋጁትን የውስጥ መተላለፊያ ኮሪደሮች፣ የሕክምና መስጫዎችና የክፍል አደረጃጀቶች በዝርዝር ተጎብኝቷል ። ይህ ሰፊ የእድሳት ሥራ ሆስፒታሉ ከቤተክርስቲያን በተከራየው በዚህ ተቋም ለኅብረተሰቡ የሚሰጠውን የሕክምና ጥራት፣ ደኅንነትና ምቾት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ተመላክቷል።
በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ብፁዓን አባቶች ሆስፒታሉ የቤተክርስቲያንን ንብረት ይዞታ ይበልጥ በሚያሳምርና የሕዝቡን ጤና ለመጠበቅ በተሟላ መልኩ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት እያከናወነ ያለውን ይህንን ዘመናዊ የልማትና የእድሳት እንቅስቃሴ በላቀ ሁኔታ አድንቀዋል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000026.jpg 252 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-05 11:16:032026-07-05 11:19:10ላይፍ አዲስ ሆስፒታል ከቤተክርስቲያን ተከራይቶ በዘመናዊ መንገድ የሚያሳድሰውን ሆስፒታል በብፁዓን አባቶች አስጎበኘ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ። Link to: የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ። የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ... Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ለሁለተኛ ዙር አስመረቀ። Link to: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ለሁለተኛ ዙር አስመረቀ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top