የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የውል እድሳት አገልግሎትን በዘመናዊና ቀልጣፋ ሲስተም መስጠት ጀመረ።

July 11, 2026
ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም |የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት፣ ዘመኑን የዋጀ የዲጂታል አሠራርና የእንግዳ አቀባበል ሥርዓት በመዘርጋት የ፳፻፲፱ ዓ.ም. የደንበኞች ውል እድሳትን በታላቅ እመርታ መጀመሩን ይፋ አደረገ። ድርጅቱ የሚያስተዳድራቸውን የንግድ እና የመኖሪያ ቤት ተከራይ ደንበኞቹን የውል እድሳት አገልግሎት ከሐምሌ ፩ ቀን ጀምሮ በይፋ መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ ሂደቱ እስከ ሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. ድረስ እንደሚቆይ ታውቋል።
ድርጅቱ ተገልጋዮችን ማዕከል ያደረገ ሥር ነቀል የአሠራርና የቴክኖሎጂ ሽግግር (Digital Transformation) በማድረጉ ምክንያት፣ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ታሪካዊ ሊባል የሚችል ከፍተኛ እመርታ ተመዝግቧል። ከዚህ ቀደም የነበረው አሠራር በተንዛዙ ሂደቶች የተሞላ በመሆኑ፣ ደንበኞች የኪራይ ውል ለማደስ ብቻ በትንሹ ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት (ከ15 እስከ 30 ቀናት) የሚወስድባቸው ከመሆኑም በላይ ለተደጋጋሚ መጉላላትና እንግልት ይዳረጉ ነበር።
በአሁኑ ወቅት ግን ይህንን ቢሮክራሲ ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ዘመናዊ የዲጂታል ሲስተም በመዘርጋቱ፣ ባለጉዳዮች የሚጠበቁባቸውን መሠረታዊ ሰነዶች ብቻ አሟልተው ሲገኙ፣ ምንም ዓይነት ወረፋና መደርደር ሳይኖርባቸው ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ባለው እጅግ አጭር ጊዜ ውስጥ ውላቸው ተሻሽሎ፣ ታትሞና ተፈርሞላቸዉ በታላቅ አክብሮት እንዲሸኙ እየተደረገ ይገኛል።
ይህንን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽና ዘመናዊ ለማድረግም፣ ተቋማዊ አሠራሩ ከባንክ የክፍያ ሥርዓት ጋር በቀጥታ እንዲተሳሰር ተደርጓል። ይህም በመሆኑ ምክንያት ደንበኞች ቀደም ሲል ይደረግ እንደነበረው ገንዘብ ለመክፈልና ደረሰኝ ለማስመታት ወደ ድርጅቱ መምጣትና በየቢሮው መንከራተት ሳይኖርባቸው፣ ባሉበት ሆነው በባንክ አማካኝነት ክፍያቸውን በቀላሉ እንዲፈጽሙ ተደርጓል። ይህ ቴክኖሎጂን ያቀናጀ አሠራር የምዕመናንንና የደንበኞችን ውድ ጊዜና ጉልበት በከፍተኛ ደረጃ ከመቆጠቡም በላይ፣ ተቋሙ ለተገልጋዮቹ የሰጠውን የላቀ የክብር ደረጃ የሚያሳይ ሕያው ማረጋገጫ ሆኗል።
ቀደም ሲል በተቋሙ ውስጥ የተደራጀ የእንግዳ መቀበያና መረጃ ሰጪ (Reception) ክፍል ባለመኖሩ ምክንያት፣ ባለጉዳዮች የሚፈልጉትን አገልግሎት በየትኛው ቢሮና በየትኛው የሥራ ክፍል እንደሚያገኙ ግልጽ መረጃ ባለማግኘት ለከፍተኛ መጉላላትና ግራ መጋባት ይዳረጉ ነበር። ይህንን ክፍተት በዘላቂነት ለመቅረፍ ተቋሙ ባደረገው አዲስ መዋቅራዊ ማሻሻያ፣ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የእንግዳ መቀበያ ማዕከል ያቋቋመ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ተገልጋዮች ገና ወደ ሕንፃው መግቢያ ሲደርሱ በሰለጠኑ ባለሙያዎች በታላቅ አክብሮትና ቀናነት አቀባበል ይደረግላቸዋል።
ማዕከሉ ወደ ቢሮው ለሚመጡ እንግዶች በሙሉ ወዴት መሄድ እንዳለባቸውና ምን ምን ሰነዶችን ማቅረብ እንደሚገባቸው ፈጣን ኦረንቴሽንና ግልጽ መረጃ የሚሰጥ በመሆኑ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን እጅግ ያቀላጠፈውና ተንዛዛውን አሠራር ያስቀረ ሆኗል። ይህንን ሥር ነቀል የባህልና የሥራ አካባቢ ለውጥ (Organizational Culture Shift) ተከትሎ፣ በተቋሙ ተገኝተው የተስተናገዱ ደንበኞች በሙሉ ካለፈው ዓመታት መጉላላት በመላቀቃቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታና የላቀ የዕርካታ (Customer Satisfaction) አስተያየታቸውን በከፍተኛ አድናቆት እየገለጹ ይገኛሉ።
በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል የተቋሙ የመኖሪያ ቤት ተከራይ የሆኑት አቶ አውላቸው አሰፋ ሲናገሩ፦ “ከዚህ በፊት ከ6 እስከ 7 ጊዜ በላይ ውል ሞልቼ አውቃለሁ፤ በዚህ ፍጥነት ግን ተስተናግጄ አላቅም። ዛሬ በመጣሁ በ10 ደቂቃ ውስጥ ብቻ ሁሉንም ነገር ጨርሼ ወጥቻለሁ። የቢሮው ሁኔታ በጣም የሚገርም ነው፤ ከበር ጀምሮ ያለው የእንግዳ አቀባበል የተለየና ቢሮው እጅግ ዘመናዊ ሆኖ የታደሰ ነው። አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ከመጡ በኋላ በፊት በአእምሯችን ላይ የነበረውን መጥፎ አሠራር የሚያስቀር ትልቅ ለውጥ እያየን ነው” ብለዋል።
ሌላኛው የተቋሙ ደንበኛ መጋቤ ብሉይ አእምሮ ዘውዴ በበኩላቸው ድርጅቱ የሚገኝበት የ4 ኪሎ አካባቢ የከተማዋ እንብርት መሆኑን ጠቅሰው፦ “ቢሮዎቹ የአካባቢውን ስታንዳርድ በጠበቀ መልኩ ታድሰውና ዘመናዊ በሆነ አሠራር ደንበኛን እያስተናገዱ ይገኛሉ። እኔ ዛሬ ውል ለመውሰድ መጥቼ በ30 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የታደሰውን ውል ተቀብያለሁ። ይህ ዘመኑን የዋጀና በቤተ ክርስቲያናችን ልማት ላይ እንደ ማሳያ የሚወሰድ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት ስለሆነ እጅግ ደስ ብሎኛል፤ ለዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ስዩማን እስክንድርና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መልካም የሥራ ዘመን እመኛለሁ” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
በተቋሙ ቀደም ሲል ያገለግሉ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የድርጅቱ ደንበኛ የሆኑት መልአከ ሕይወት ቀለመወርቅ በበኩላቸው በተደረገው ለውጥ መደመማቸውን ገልጸው፦ “አመታዊ የኪራይ ውል አሰጣጡ በአጭር ደቂቃ ውስጥ መጠናቀቁ ደንበኞች ይማረሩበት የነበረውን ማንዛዛት አስቀርቷል። ጥያቄ ስንጠይቅ ወዲያውኑ መፍትሔ ማግኘታችን በተቋሙ ውስጥ ያለውን የተለየ ለውጥ ያሳያል። ሌላው ትልቁ ስኬት የሕንፃው እድሳት ከድርጅቱ ወጪ ሳይወጣ በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር መከናወኑ ነው። ሠራተኛው በጥሩ መሪ ሥር ተናቦ እየሠራ ነው፤ ሥራ አስኪያጁን ስንጠይቅ ሥራን ለነገ አያሳድሩም፤ በዚህም ሥራ አስኪያጁንና ሠራተኞቹን በሙሉ አደንቃለሁ” ብለዋል።
በአጠቃላይ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶች እና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት በአሁኑ ወቅት እያሳየ ያለው ሥር ነቀል የአሠራር ለውጥ፤ ተቋሙ ካለበት አሮጌና የተንዛዛ ቢሮክራሲ ወጥቶ ወደ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ዲጂታላይዝድ ወደሆነ አሠራር መሸጋገሩን በተግባር ያሳየበት ሆኗል። ከአራት ሳምንታት እንግልት ወደ 20 ደቂቃዎች መስተንግዶ የተደረገው የጊዜ ቅነሳ፣ ደረጃውን የጠበቀ የእንግዳ መቀበያ (Reception) ማቋቋም መቻሉ እና ከባንክ የክፍያ ሥርዓት ጋር የተገነባው ትስስር ተቋሙ ለደንበኞቹ የሰጠውን የላቀ የክብር ደረጃ የሚያረጋግጡ አበይት ማሳያዎች ናቸው።
ይህ በድርጅቱ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው ደንበኛ ተኮር አገልግሎትና የቢሮዎች መታደስ፤ በአዲሱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ መሪነትና በሥራ ባልደረቦቻቸው ቁርጠኝነት የመጣ መሆኑን ተገልጋዮች በታላቅ ዕርካታ መስክረዋል። ለውጡ ከድርጅቱ ካፒታል ላይ ምንም ዓይነት ወጪ ሳይደረግ፣ በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር የተከናወነ መሆኑ ደግሞ የአመራሩን ስልታዊና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሥራ መሪነት ይበልጥ ጎልቶ እንዲታይ አድርጎታል።
የቤቶች እና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት ይህንን የተጀመረውን የልማት፣ የማዘመንና የቀናነት ጉዞ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ያረጋገጠ ሲሆን፤ ይህ ስኬታማ ተሞክሮ በሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ ተቋማትና መዋቅሮች ዘንድ እንደ መልካም ተሞክሮ (Best Practice) የሚወሰድና የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ዕድገትና ልማት ይበልጥ የሚያፋጥን መሆኑ ታምኖበታል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000029.jpg 336 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-11 05:52:502026-07-11 05:52:50የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የውል እድሳት አገልግሎትን በዘመናዊና ቀልጣፋ ሲስተም መስጠት ጀመረ።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የአራቱ ጉባኤያት የምስክር ጉባኤ ቤት 19 ደቀመዛሙርትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት አስመረቀ። Link to: የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የአራቱ ጉባኤያት የምስክር ጉባኤ ቤት 19 ደቀመዛሙርትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት አስመረቀ። የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የአራቱ ጉባኤያት የምስክር... Link to: ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው በዛሬው ዕለት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቁ ። Link to: ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው በዛሬው ዕለት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተመረቁ ። ከባሌ ጎባ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የኮርስ ሰልጣኞች...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top