የቦታው ስም ቀራንዮ ነው
የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
ከታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲገነባ በቆየው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ በተለያየ ወረዳ ተበታትነው የነበሩ ቦታዎች ወደአንድ ወረዳ እንዲካተቱ እና ደብሩ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲያገኝ ተደርጓል። በከፍተኛ ወጪ በአጭር ጊዜ የተከናወነው ግንባታ በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስአበባ የሀዲያ እና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሰሜን አሜሪካ ሚኒሶታ እና ኮሎራዶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ […]
በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በሸገር ሀገረ ስብከት በስሉልታና መነአብቹ ክፍላተ ከተማ በአትሌት ፕሮጀክት መንደር የተገነባ የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል፣ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና ልደታ ለማርያም አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በዛሬ ዕለት ግንቦት 19/2018 ዓ/ም በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የምስካየ ሕዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ጠባቂ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ […]
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምሥራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ በፊት በቅዱስ ሲኖዶስ በተወሰነው መሠረት ሀገረ ስብከቱን እንዲመሩ መድቧቸዋል። በዚሁም መሠረት ብፁዕነታቸው በም0ሥራቅ አርሲ አሰላ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ። በአቀባበሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ […]
ከግንቦት እስከ ግንቦት ክፍል ሦስት
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ሆነው እንዲሠሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በከፍተኛ ድምጽ ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ደረጃውን በጠበቀና የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር በሚመጥን መልኩ እንዲደራጅ ፣ እንዲጸዳና እንዲዋብ በማድረግ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ምንም ዓይነት ወጪ ሳይጠይቁ በጎ አድራጊ ምዕመናንን በማስተባበር የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ያማረና ግሩም እንዲሆን አድርገውታል። ይህም በመሆኑ […]
የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 81ኛ ዓመት የአንድነት ኑሮ ምሥረታ ክብረ በዓል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከብረ
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 81ኛ ዓመት የአንድነት ኑሮ ምሥረታ ክብረ እጅግ ባማረ በድምቀት ተከብረ በበዓሉም ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ […]
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ የሰላምና የያብሮነት የጸሎት መርሐ ግብር ” ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን ” በሚል መሪ ቃል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሌሎች ሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት አደረገ
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በአራዳ ፓርክ በተከናወነው ጸሎት መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤አገኘሁ ተሻገር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ አቶ አደም ፋራህ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር […]
የአዳማ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ካቴድራል 1ኛ ዓመት የቅዳሴ ቤት ክብረ በዓል ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ በተገኙበት ተከበረ
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀማዳዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቡራኬ ተባርኮ የተመረቀው የአዳማ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት ካቴድራል አንደኛ ዓመት የቅዳሴ ቤቷ ክብረ በዓል በዛሬዋ ዕለት፤ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የዝዋይ […]
በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ ሲከበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ […]
ደንበኛ ተኮር ስርዓት የወለደው የነዋሪዎች አንድነት ከድርጅቱ አልፎ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጋርም እያስተሳሰረ መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የተጀመረው ደንበኛ ተኮር ስርዓት ደንበኞችን ከድርጅቱ ጋር ከማቆራኘት አልፎ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጋር መናበብን የፈጠረ ሲሆን ይህንኑ በሚገልጽና ተባባሪነትን በሚያሳይ መልኩ በዛሬው እለት የጽዳት ዘመቻ አካሂዷል። የጽዳት ዘመቻው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት […]
በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከናወነ
ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓ.ም በቡራኬ ቤተክርስቲያን መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ድርጅት የበላይ ሓላፊ የሰሜንና ምሥራቅ አፍሪካ […]