የቦታው ስም ቀራንዮ ነው
የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።
ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለአገልግሎት የሚሆን ፕራዶ መኪና ገዝቶ በስጦታ አበረከተ
ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የመኪናውን ቁልፍ ለብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሸካ ቤንች ማጂ እና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ የበላይ ኃላፊ አበርክተዋል፡፡ ቅዱስነታቸው በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት “ሥራ የሚሠራ ሰው ዋጋ ይገባዋል፡፡ ለአገልግሎት የሚሆን መኪና አስፈላጊ […]
ክፍል ሁለት …..” ከግንቦት እስከ ግንቦት ” እንደሚከተለው ይቀርባል
ባለፈው “ከግንቦት እስከ ግንቦት” ዝግጅታችን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ዘመነ ሢመት የተከናወኑ ዋናዋና ሥራዎችን በመጠኑ የዳሰስንበትን ዘገባ ለንባብ ማቅረባችን ይታወሳል።ቀጣዩን ክፍል እንደሚከተለው እናቀርባለን፦ 7.ኛ ቤተክርስቲያን በመጪው ዘመን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማሳለጥ፣ ቀደምት አባቶቻችን ጥለውልን በሄዱት ይዞታዎች ላይ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ ሠርታ ለማስተላለፍ እንዲሁም በከተማችን የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍና በከተማችን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ […]
የለገጣፎ ደብረ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም እና አቡነ ሐራ ድንግል ዘመናዊ የፀበል ቤት በብፁዕ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተባርኮ ተመረቀ
ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣ በለገጣፎ ለገዳዲ እና ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ ሥር የሚገኘው የደብረ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም ወአቡነ ሐራ ድንግል በዘመናዊ መልክ ያስገነባው የፀበል ቤት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ […]
በአዶላ ወዩ በሚገኙ አድባራት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ክፍል ለሚማሩ ደቀመዛሙርት አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተሰጠ
ግንቦት 10ቀን 2018ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል ተዘጋጅቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት፣ በብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ የጉጂ ቦረና ሊበን እና የምዕራብ አርሲ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ መሠረት በሁለቱም አኅጉረ ስብከቶች ተግባራዊ እየሆነ መሆኑ ተገልጿል። በግንቦት 09 ቀን 2018 ዓ.ም በአዶላ ወዩ ለሚገኙ አድባራት […]
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ወሊሶ ማዕከል ጋር በመተባበር በአፋን ኦሮሞ የሚያገለግሉ 15 ተተኪ መምህራንን አስመረቀ
ግንቦት 09 2018 ዓ/ም ዛሬ የተመረቁት ተተኪ መምህራን ለ፫ ወራት ግብረ ዲቁና ፣ኪዳን ፣ ሊጦን ፣ መስተበቁዕ ፣ መልክዓ ሥዕል ፣ መልክዓ ቁርባን ፣ መልክዓ ውዳሴ ፣ መልክዓ ማርያም ፣ መልከዓ ኢየሱስ በአፋን ኦሮሞ እንዲሁም ነገረ ሃይማኖታዊ ፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ፣ የስብከት ዘዴ ፣ ሐዋሪያዊ ተልዕኮ ፣ ነገረ ቅዱሳን ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ኮርሶችን […]
በሸገር ሀገረ ስብከት የዓለምገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተመረቀ
ግንቦት 09 2018 ዓ/ም በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ […]
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካሏት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም አንዱ በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው ወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ነው። ገዳሙ በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተ በወንጪ ሐይቅ ደሴት ላይ የሚገኝ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም ነው። ገዳሙ ከ800 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኝ በመሆኑ ገዳሙ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችን […]
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ
ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም | የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ክብሯንና ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖዋን የሚያሳድጉ የልማት ሥራዎችን አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በግቢው ውስጥ የሚገኘውንና ዘመኑን የዋጁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ያካተተውን ዓለም አቀፍ የስብሰባ አዳራሽ ግንባታ በቦታው ተገኝተው ጎበኙ። በዚህ ከፍተኛ የሥራ […]
በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ትጋት ለፍጻሜ የበቃው ባለ 480 ካሬ ሜትር ሁለገብ ሕንጻ ተመረቀ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ምዕመናን በተገኙበት፣ በአዲስ አበባ አሮጌ ቄራ አካባቢ የተገነባው ዘመናዊ ሁለገብ ሕንጻ በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል። ይህ በ480 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ባለ 11 ወለል (B+G+10) የሆነው ሕንጻ፣ ግንባታው የተጀመረው በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት ዘመነ ሢመት ነበር። ሆኖም ግንባታው በአራት የተለያዩ ኮንትራክተሮች እጅ በማለፉ […]
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ በመሆኗ አበው ቅዱሳን በፍትሕ መንፈሳዊና በጉባኤ አድያም ዘአንጾኪያ “ወይኩን ሲኖዶስ ዘጳጳሳት ፪ተ ጊዜያተ በበዓመት – የጳጳሳት ጉባኤም በዓመት ሁለት ጊዜ ይሁን” […]