የቦታው ስም ቀራንዮ ነው

የ2018 ዓ.ም. መስቀል በዓል ልዩ እትም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶና ተመርምሮ፤ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተዘጋጀ

ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

ቅዱስ ሲኖዶስ በልማትና ዘመናዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ6 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤውን አጠናቀቀ

ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን መደበኛ የምልኣተ ጉባኤ ስብሰባውን በ22 አጀንዳዎች ላይ በመወያየትና ለቤተክርስቲያናችን ቀጣይ ጉዞ ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ማጠናቀቁን የቅዱስ ሲኖዶስ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ቀሲስ ዳንኤል ሰይፈ-ሚካኤል ለEOTCTV በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ አስታውዋል። ኃላፊው በሰጡት ማብራርያ፣ ጉባኤው በተለይም በመንበረ ፓትርያርክ […]

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ፈደራል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ “ጠንካራ ትብብር ለሀገር ሰላም! ሰላም የወል ሀብታችን ነው!” በሚል መሪቃል ስለሰላም በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራረመ

ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከየቤተ እምነቱ የተወከሉ አባቶች በተገኙበት “ጠንካራ ትብብር ለሀገር ሰላም በሚል የተከናወነው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የጋራ ስምምነት ፊርማ ፤ በሀገራችን በሚከናወኑ ምክክሮች ሰላምን ለማረጋገጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑ ተገልጿል ። የስምነት ስነዱን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እና የፌደራል […]

ከግንቦት እስከ ግንቦት

ክፍል አንድ አምና በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የግንቦቱን ርክበ ካህናት ጉባኤውን በሚያካሒድበት ወቅት አንዱ አጀንዳ አድርጎ የያዘው የጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ምርጫን ነበር። በምርጫውም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የራያ ሀገረ ስብከት […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦ መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ‹‹ተዘከሩ መቁሓነ ዘከመ ተሞቃሕክሙ ምስሌሆሙ ወእለ ተሣቀዩ ከመ ዘሀለውክሙ በሥጋክሙ፡- ከእነርሱ ጋር አብራችኋቸው እንደታሰራችሁ ሆናችሁ እስረኞችን ዐስቡ፤ መከራ የጸናባቸውንም በሥጋችሁ ከእነርሱ ጋር እንዳላችሁ ሆናችሁ ዐስቡ›› (ዕብ. 13፡3) እውነተኛ እምነትም […]

የአዳማ ሰቀቀሎ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ

ግንቦት ፪ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዳማ — በአዳማ ከተማ በውብ የኪነ-ሕንጻ ጥበብ የታነጸው የአዳማ ሰቀቀሎ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ ቤተ መቅደስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት በዛሬው ዕለት ቅዳሴ ቤቱ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከብሯል። ትላንት ግንቦት ፩ ቀን በብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ (የምሥራቅ ሸዋ […]

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በቃሊቲ አካባቢ ለበጎ አድራጎት ሥራ ከ23 ዓመት በፊት ያስገነቡትን Gተ1 የመኖሪያ ሕንጻ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማኅበር በስጦታ አበረከቱ

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት የስጦታ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል። ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ለበጎ አድራጎተት እንዲውል የሕንጻ ቁጥሩ 982 የሆነውንና በግል ገንዘባቸው በ544 ካሬ ሜትር ቦታ ያረፈ ሕንጻ በመገንባት ለዚሁ ዓላማ እንዲውል አድርገዋል። ሕንጻው […]

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ ኣሜን! ብፁዕ ኣቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ ኣስኪያጅ፤ ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፤ ብፁዕ ኣቡነ ሕርያቆስ የኣዲስ ኣበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት፣ በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦ ማሕየዊት በምትሆን ሞቱ ሰማያውያንና […]

የ፳፻ ፲ወ፰ ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናወነ

ሚያዚያ ፳፯ ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓ/ም አዲስአበባ -ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፳፻ ፲ወ፰ ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናወነ። በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተከናወነው የጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ […]

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 76ኛ ዓመት ቅዳሴ ቤት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከበሮ ዋለ

ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በየዓመቱ ሚያዚያ 27 ቀን በዓመት እንድ ግዜ ብቻ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በአውደ ምሕረት ምዕመናን የሚባርክበት ዕለት እና የኢትዮጵያ የነጻነት በዓል በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም በድምቀት ተከብሮ ውሏል ። በበዓሉ ላይም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንበረ ፓትርያርክ ዋና ስራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ […]

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ለምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም የ76ኛ ዓመት ቅዳሴ ቤት እና በጀግኖች አባቶቻችን ለተገኘው 85ኛው የኢትዮጵያ የድል በዓል ያስተላለፉት መልዕክት

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን — በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን — አግአዞ ለአዳም ሰላም — እምይእዜሰ ኮነ — ፍሥሐ ወሰላም ​”ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር” “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ” መዝ. 68፡31 • ​ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ • ​የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመመሪያ ኃላፊዎች፤ • ​የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የመመሪያ ኃላፊዎች፤ • […]

በፌስቡክ ያግኙን

የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ

የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ልማት በቤተ ክርስቲያን

ይህ ልዩ ዕትም መጽሔት ጽርሐ ምኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሕንጻ ፈርሶና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተዘጋጀ።

ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ርእይ

ሁለንተናዊ ስብእናው የተጠበቀ፣ በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የደመቀ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጣዕመ ሕይወትን የተላበሰ፣ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት በዝቶ ማየት

ተልእኮ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተማርና ማዳረስ

  • ሰውን በሁለንተናዊ ሰብእናው ማገልገልና ማዳን

  • ሰውን ሁሉ በነገረ መለኮትና በነገረ ጥበብ ትምህርት በማልማት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ሕይወቱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረው ማድረግ

  • ጥራትና ብቃት፣ ፍትሐዊነትና እኩል ተደራሽነት ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለሰው ሁሉ ማበርከት

  • የተለያዩ የልማት መርሀ ግብሮችን በመንደፍ ቤተ ክርስቲያንን በኢኮኖሚ ማበልጸግ

  • በቴክኖሎጂ ስልት የሚመራና አዋጭነቱ አስተማማኝ የሆነ የጠቅላላ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ማድረግ

  • የሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ፣ ፍቅርና ስምምነት እንዲጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ

  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰራር ግልጽ፣ ለሁሉም ተደራሽና ችግር ፈቺ እንዲሆን ማድረግ

ዕሴቶች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅሊናን የሚረታ፣ አእምሮን የሚመሥጥ፣ ከጥንተ ፍጥረት ተነሥቶ በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ብሉይ በሕግ ኦሪት፣ ተራምዶ መዳረሻውን ሕገ ወንጌል ያደረገ ጥንታዊ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ የታጀበ ሥርዐተ አምልኮ፣ በጽሑፍና በትውልድ ቅብብሎሽ የተወረሰ የረጅም ጊዜ ትውፊት ባህልና ታሪክ

  • በሃይማኖትና በሥነ ምግባር የበለጸገ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝና ምክረ ካህን የሚቀበል ከስልሳ ሚልዮን በላይ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ የክርስቲያን ማኅበረሰብ

  • ለምጣኔ ሃብት ዕድገት እጅግ የምትጠቅም በውብ ሥነ ተፈጥሮና በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብና በኪነ ጥበብ፣ በታሪክና በቅርስ ሃብት የበለጸገች እንዲሁም በሃይማኖት፣ በነጻነትና በአንድነት የደመቀች ሃገር

  • የእግዚአብሔርን ቃል ከሃገር ውስጥ ባሻገር ለመላው ዓለም ማዳረስ የሚችሉ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሱ ሊቃውንት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ከሁለት ሺሕ ያላነሱ ገዳማት

  • መላውን ዓለም እያዳረሰና እየሰፋ የሚገኝ ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረ ጠንካራ መዋቅር ያላት መሆኗ

ያግኙን

+251 111 55 0098 P.O.Box 1283 A.A. 5 KILLO, ADDIS ABABA, ETHIOPIA በፌስቡክ ያግኙን የዩትዩብ ቻነል የቴሌግራም ቻነል