የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 76ኛ ዓመት ቅዳሴ ቤት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከበሮ ዋለ

May 5, 2026

ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም
በየዓመቱ ሚያዚያ 27 ቀን በዓመት እንድ ግዜ ብቻ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በአውደ ምሕረት ምዕመናን የሚባርክበት ዕለት እና የኢትዮጵያ የነጻነት በዓል በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም በድምቀት ተከብሮ ውሏል ።
በበዓሉ ላይም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንበረ ፓትርያርክ ዋና ስራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የራያ አላማጣ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የማኅበራት ማደራጃ የቤተ መዛግብት ወመጻሕፍት መመሪያ ኃላፊ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣የመንበረ ፓትርያሪክ የመመሪያ የሥራ ኃላፊዎች ፣ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ባቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ፣ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የማኅበራዊ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ፣ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሴ የአዲስ አበባ ዋና ስራ አስኪያጅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመምሪያ የሥራ ኃላፊዎች ፣ መጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ዋና አስተዳዳሪ ፣ የገዳማት አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ፣ በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ታቦት ከኢየሩሳሌም ዴር ሱልጣን ገዳም ሀገር በጠላት ወረራ ውስጥ በሆነችበት ጊዜ በንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ጥያቄ ለጸሎት ማድረሻ እና ለመማጸኛ ከጥቂት አገልጋዮችጋር በ 1929 ዓ ም ተጓዘ ።
በእንግሊዝ ለንደን ባት በተባለ ቦታ አርፎ እስከ1933 አገልግሎት እየሰጠ ቆይቷል በቀድሞ ስሙ ገነተ ልዑል ቤተ መንግስት የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2 ዓመታት ከቆየ በኃላ በቀድሞ ስሙ ቤተ ሳይዳ ወይም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሆስፒታል የአሁኑ የካቲት 12 ሆስፒታል ማረፊያ ተዘጋጅቶለት ከቆየ በኃላ ሚያዚያ 27 1942 ዓ.ም ወደ አሁኑ ያለበት ስፍራ በመምጣት በገዳምነት እያገለገለ ይገኛል።
በዚህ ቦታም ምስካየ ኅዙናን ተብሎ የተሰየመው በንጉሡ ሲሆን በቀድሞው ቤተ ሳይዳ ሆስፒታል በነበረበት ወቅት ነው የኃዘንተኞች ሁሉ መፅናኛ በመሆኑ ስያሜውን አግኝቷል ፣ ዴር ሱልጣን መድኃኔ ዓለም በኢየሩሳሌም በንጉሳውያን ገዳም በነበረበት ነው።
ስደተኛው መድኃኔ ዓለም መባሉ ደግሞ ኢትዮጵያ ነፃነቷን እስክታገኝ ለንጉሡና ለሰራዊቱ መፅናኛ በመሆን በስደት ከንጉሱ ጋር ከሀገር ሀገር መሰደድ ነው ።
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የድል ቀን እና የምስካ የኅዙናን መድኃኔ ዓለም ቅዳሴ ቤት 76ኛ ዓመት በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ ላይም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በበዓሉ የታደሙትንብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የክብር እንግዶች እንዲሁም ምዕመናንን የእንኳን አደረሳችሁ በማለት የበዓሉን የአከባበር ሁኔታ እና የታቦቱን ታሪካ የገለፁ ሲሆን በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድን ግሪክ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትምህርተ ወንጌል ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ በመስጠት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።
©ም/ስ/ኀ/ዙ/መ/ገዳም ሚዲያ፤

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/0014.jpg 427 640 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-05 09:20:102026-05-05 09:20:10የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም 76ኛ ዓመት ቅዳሴ ቤት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከበሮ ዋለ
Search Search

Recent Posts

  • የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው “የሕክምና መንደር” የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ።
  • የላሊበላ ቅርሶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ።
  • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡
  • የቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት ሠራተኞቹን አመሰገነ።
  • “ተመራቂዎች በየተሰማሩበት የስምሪት መስክ ሁሉ እንደ መብራት ሊያበሩ ይገባል” ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ለምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም የ76ኛ ዓመት ቅዳሴ ቤት እና በጀግኖች አባቶቻችን ለተገኘው 85ኛው የኢትዮጵያ የድል በዓል ያስተላለፉት መልዕክት Link to: ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ለምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም የ76ኛ ዓመት ቅዳሴ ቤት እና በጀግኖች አባቶቻችን ለተገኘው 85ኛው የኢትዮጵያ የድል በዓል ያስተላለፉት መልዕክት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ... Link to: የ፳፻ ፲ወ፰ ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናወነ Link to: የ፳፻ ፲ወ፰ ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናወነ የ፳፻ ፲ወ፰ ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top