የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ

May 14, 2026

ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም | የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
​የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ክብሯንና ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖዋን የሚያሳድጉ የልማት ሥራዎችን አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በግቢው ውስጥ የሚገኘውንና ዘመኑን የዋጁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ያካተተውን ዓለም አቀፍ የስብሰባ አዳራሽ ግንባታ በቦታው ተገኝተው ጎበኙ።
በዚህ ከፍተኛ የሥራ ጉብኝት ላይ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የድርጅት ሥራ አስኪያጆች እና የመምሪያ ኃላፊዎች መገኘታቸው የፕሮጀክቱን ታላቅነት ያመለክታል።
​ስለ ግንባታው ሂደት ዝርዝር መረጃ የሰጡት የ AV Consultant አማካሪ አርክቴክት ሳሙኤል አፈወርቅ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ በ2,500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ግዙፍ ሕንጻ ሲሆን በአንድ ጊዜ 2,500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ዋና አዳራሽን ጨምሮ የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ አዳራሽ፣ የሰንዳኬት (Syndicate) መሰብሰቢያ፣ የቪ.አይ.ፒ (VIP) አዳራሽና ሬስቶራንት እንዲሁም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ቢሮዎችን በውስጡ ይዟል።
ሕንጻው ከመደበኛ የግንባታ ጥበቡ ባሻገር እስከ 30 ቋንቋዎችን በቅጽበት መተርጎም የሚችል የትርጉም ክፍል፣ ዘመናዊ ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት፣ የጋዜጣዊ መግለጫ መስጫ (Press Conference) ክፍል፣ የድምፅ መከላከያ (Soundproof) ሥርዓት እና ዘመናዊ የቅዝቃዜ መቆጣጠሪያ (AC) ግብዓቶች የተሟሉለት በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ያደርገዋል።
​ከቴክኖሎጂው ባሻገር ለተገልጋዮች ምቾትና ለደኅንነት ልዩ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፣ በአንዴ 16 ሰዎችን መጫን የሚችሉ ሁለት ሊፍቶች፣ ለ90 ሰዎች የሚሆኑ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች እና ቀድሞ እስቶር በነበረው ሰፊ ቦታ ላይ ከ300 በላይ መኪናዎችን ማቆም የሚችል ዘመናዊ ፓርኪንግ ተዘጋጅቶለታል። የሕንጻው የውስጥ (Interior) ዲዛይን የቤተ ክርስቲያኒቱን ረጅም ታሪክ፣ ጥበብና መንፈሳዊ ማንነት በሚሰብክ መልኩ የተቀረጸ ከመሆኑም በላይ አጠቃላይ ግንባታው የአረንጓዴ ልማትን (Green Infrastructure) መሠረት ያደረገ ሆኖ ለውበት የሚተከሉ ዕፅዋት በሙሉ ሀገር በቀል እንዲሆኑ ታቅዷል። በተጨማሪም የግቢውን የውሃ ችግር ለመፍታት የከርሰ ምድር ውሃ ወጥቶለታል። በ Atom Construction አማካኝነት እየተገነባ የሚገኘው ይህ ታሪካዊ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለምታካሂዳቸው ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ኩነቶች ታላቅ አቅምና ገጽታ የሚፈጥር መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተመላክቷል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/000301.jpg 336 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-05-14 11:46:332026-05-14 11:46:33ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ
  • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የሥብሰባ አዳራሽ ጎበኙ
  • በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ትጋት ለፍጻሜ የበቃው ባለ 480 ካሬ ሜትር ሁለገብ ሕንጻ ተመረቀ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ቅዱስ ሲኖዶስ በልማትና ዘመናዊ አሠራር ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ6 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤውን አጠናቀቀ

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ትጋት ለፍጻሜ የበቃው ባለ 480 ካሬ ሜትር ሁለገብ ሕንጻ ተመረቀ Link to: በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ትጋት ለፍጻሜ የበቃው ባለ 480 ካሬ ሜትር ሁለገብ ሕንጻ ተመረቀ በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተጀምሮ በብፁዕ አቡነ... Link to: ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ Link to: ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት እየታደሰ የሚገኘውን ዕድሜ ጠገቡን የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ጎበኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጠቅላይ ሚኒስትር...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top