የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

October 11, 2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
«ወዘሰ ጸንዐ ወቆመ ምግባሩ ውእቱኬ ዘይነሥእ ዕሴቶ ፥
ሥራው ጸንቶ የተገኘለት ሰው ዋጋውን የሚቀበል እርሱ ነው።»
(1ኛ ቆሮንቶስ 3፥14)

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በጻፈው መልእክቱ በሐዋርያዊ ተልእኮ ውስጥ በትምህርተ ሃይማኖት የመትከል፥ በሥርዓት የመምራት፥ በፍቅር የመንከባከብ ልዩ ልዩ ጸጋ ያላቸው
ሥዩማን ሲኖሩ፤ የሥራው ባለቤት ግን እግዚአብሔር መሆኑን በሕንጻ ግንባታ እየመሰለ ሲያስተምር፤
በነቢያት፥ በሐዋርያትና በሊቃውንት ትምህርት በተገለጠው የክርስቶስ መሠረትነት ላይ ውሉደ
ክህነት አገልግሎታቸውን በታላቅ ጥንቃቄ ማከናወን እንደሚኖርባቸው ያስገነዝባል፡፡

የተጀመረ ሥራ ከፍጻሜ ሲደርስ ከውጥኑ አንሥቶ የመሳተፍ ዕድል የገጠማቸው ሰዎች በልቡናቸው ጥልቅ ስሜት ሊፈጠር እንደሚችል እሙን ነው።
እኛም ዛሬ ባርከን አገልግሎት የምናስጀምረው የቅዱስ
ሲኖዶስ፥ የስብከተ ወንጌልና ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤያትን ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችሉ
አዳራሾች የተካተቱበት ግዙፍ ሕንጻ ዋጋው የሚመዘነው በተሠራበት ቁሳቁስ ብቻ ሳይሆን በተገነባበት ዓላማ
ጭምር ነውና፤ የቦታ አጠቃቀምንና ማራኪ ሥነ ሕንጻን በማዋሐድ ተገንብቶ የቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊ
አገልግሎት በሚፈለገው ልክ የሚጠናከርበትና ለቀጣዩ
ትውልድም የምናቆየው ዘመን ተሻጋሪ ሀብት እንደሆነ በመረዳት ከፍ ያለ መንፈሳዊ ደስታ ይሰማናል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

የዚህ ሕንጻ ግንባታ ሐሳብ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፭ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ መዋዕለ ሕይወት ተነሥቶ የነበረ ቢሆንም፤ ፈቃደ አምላክ
ተጨምሮበት ዕቅዱን የማደራጀትና የግንባታ ተግባሩ በዘመነ ክህነታችን ተጀምሮ መጠናቀቁ የታሪካችን አንድ
ክፍል ሆኖ እንዲታወስ ስለሚያደርገው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

ዓመታትን በወሰደው የሥራ ሂደትም ብዙዎች በዕውቀታቸው፥ በጉልበታቸው፥ በሓላፊነታቸውና በትጋታቸው የየራሳቸውን አሻራ በማሳረፋቸው የዛሬው ምሉእ ውጤት የተገኘው በእነዚህ ባለ ድርሻዎች ጥረት ሲሆን፤ በተለይም የግንባታው ንድፍ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ
አንሥቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እየተመደቡ በጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነትና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸሓፊነት ያገለገሉ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የዚህ ወርቃማ ታሪክ አካል ከመሆናቸውም ባሻገር፤ በልዩ ጥራት ተጠናቆ ለምርቃት ይደርስ ዘንድ አሁን በሥራ ላይ የሚገኙት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ
ዋና ጸሐፊ፥ እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ሓላፊዎች የነበራቸው ሚና የጎላ
በመሆኑ፤ ሁሉንም የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን እንኳን ለዚህ ዕለት አደረሳችሁ! እንኳንም የድካማችሁን ፍሬ
ለማየት አበቃችሁ! ለማለት እንወዳለን፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

ዛሬ ይህንን ሕንጻ በምንመርቅበት ቅጽበት በመላው ዓለምና በሀገራችን መዓዝናት በረሀብ፥ በጦርነት፥ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ሕይወታቸውን
የሚያጡ፤ ከኖሩበት ቀዬም የሚፈናቀሉ ብዙዎች ናቸውና፤ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በዚህ ዘመን ከምንጊዜውም
በላይ በእውነት፥ በፍቅር፥ በመተማመንና በመንፈሳዊ ሕብረት ላይ ተመሥርቶ፤ የተጨነቁትን የሰው ልጆች ተስፋቸው ስለሚለመልምበት ሁኔታ ማሰብ እንደሚገባ በዚሁ አጋጣሚ እናስታውሳለን፡፡

በመጨረሻም በአዲሱ ጽርሐ ተዋሕዶ የሚደረጉ ጉባኤያት ሃይማኖትን ለማጽናት፥ ለቤተ ክርስቲያን
አንድነት፥ ለሕዝባችን ደኅንነትና ለሀገር ሰላም አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ፥ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያናችን
ታሪክ ከነሙሉ ክብሩ ለትውልድ የሚሸጋገርባቸው ሊሆኑ ይገባል እያልን አባታዊ የአደራ መልእክታችንን
በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ
ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን
ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ

ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፩ ቀን ፳፻፲ወ፱ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፥ ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/TST2019.jpeg 444 336 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-10-11 14:43:462026-10-11 14:43:46መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
Search Search

Recent Posts

  • መልዕክተ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር
  • “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ።
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

Archives

  • October 2026
  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: መልዕክተ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ Link to: መልዕክተ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ መልዕክተ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ Link to: የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት Link to: የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት
Scroll to top Scroll to top Scroll to top