የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

October 14, 2026
በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ ኣሜን፡፡
ብፁዕ ኣቡነ ሳዊሮስ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ ኣስኪያጅ፤
ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና፤
ብፁዓን ኣበው ለቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት፣
የተከበራችሁ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያውና የየርጅቱ ኃላፊዎች
የተከበራችሁ የየኣህጉረ ስብከቱ ስራ ኣስኪያጆችና ተወካዮች
የኣዲስ ኣበባ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ የየገዳማቱና ኣድባራቱ ኣስተዳዳሪዎች፣
በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የተገኛችሁ ክቡራንና ክቡራት በሙሉ!
ፍጥረቱን በትክክለኛ መርሕ የሚያስተዳድር እግዚአብሔር ኣምላክ ከኣራቱ መዓዝነ ዓለም ኣሰባስቦ በዚህ ቅዱስና ሓዋርያዊ ጉባኤ ስለ ሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለእሱ ይሁን፤ እናንተም ወደ ቅድስት እናት ቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ ጉባኤ እንኳን በደኅና መጣችሁ!
“ኲሉ ማዕምቅ ይምላእ፣ ወኲሉ ወግር ይተሓት ወኲሉ መብእስ ይኩን መጽያሕተ ርቱዐ፤ ወይርኣይ ኲሉ ዘነፍስ ኣድኅኖቶ ለእግዚአብሔር፡- ዓዘቅቱ ሁሉ ይሙላ፤ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፤ ሸካራውም ይስተካከል፤ ሥጋዊም ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ (ሉቃ. 3፥6)
የዚህ ትምህርተ መለኮት መሠረታዊ መልእክት ትክክለኛ፣ ፍትሕንና እኩነልነትን በማኅበረ ሰብ መካከል ማረጋግጥ ነው፤
ፍትሕና እኩልነት ለሰው ልጅ ያላቸው ዋጋ፣ ከምግብ፣ ከመጠጥና ከልብስ ፍላጎት ያልተናነሰ ነው፤ የሰው ልጅ ደስታና የኅሊና ነጻነት የሚለካው ኣስተማማኝ በሆነ የፍትሕና የእኩነልነት ሃልዎት እንጂ በምግብ፣ በመጠጥና በልብስ ወይም በሃብት ብዛት አይደለም፤ ብዙ ሃብት ያላቸው ሰዎች ፍትሕንና እኩልነትን ካጡ፣ ኅሊናዊ ተሃውኮ ላይ ይወድቃሉ፤ ኑሮኣቸውም በእጅጉ ይረበሻል፤ ለሃብታቸውም ዋስትና እንደሌለው ስለሚረዱ ነገራቸው ሁሉ ይቃወሳል፣ ይናጋልም፡፡
ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
ፍትሕና ርትዕ ለሰው ልጅ የተቃና ኑሮ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጡ ምርጥ ስጦታዎች ናቸው፤ ፍትሕና እኩልነት በሕግ የበላይነት ጥላ ሥር ሲውሉ ለሰው ኅሊና ፍጹም ነጻነትን ያጐናጽፋሉ፤ ሲዘነጉና ሲናቁ ግን ኑሮው የተመሰቃቀለና ተስፋ ቢስ የሆነ ማኅበረ ሰብ ይፈጠራል፤ ነገሩ ሲራዘም ደግሞ ግጭትን ይወልድና መጠፋፋትን ያስከትላል፤ ፍትሕና እኩነልነት የእግዚአብሔር ገንዘቦች እንደመሆናቸው መጠበቅና መከበር ያለባቸው በቤተ እግዚአብሔር ነው፤ “ፍትሑ ለነዳይ ወለዕጓለ ማውታ ወኣጽድቁ ግፉዐ ወምስኪነ” የሚለውን ትምህርት የምናገኘው በቤተ እግዚአብሔር ነውና፤
ይሁን እንጂ “በኣንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” እያልን ኣንዱ ደብር የተራራ ያህል በሃብት የናጠ፣ ሌላኛው ደብር ደግሞ ሁሉን ኣጥቶ የተዘጋ ነው፤
በሰው ኃይል ኣስተዳደርም ኣንዱ ከበቂ በላይ ደመወዝ ሲያገኝ፣ ሌላው ድቃቂ ሳንቲም ኣጥቶ በችግር ይማቅቃል፤ በኣድልዎ፣ በጥቅም ትስስርና በብልሹ የሃብት ኣያያዝ የሚከሠተው ምዝበራ ሁሉ የፍትሕና የእኩልነት እጦት ውጤት ነው፤
እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን ማስፈንና ቤተ ክርስቲያንን ለቀጣዩ ትውልድ ማሸጋገር የማንወጣው ከባድ ዳገት ይሆንብናል፡፡
ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት
የተከበራችሁ እንግዶች!
የሰው ኃይል ኣስተዳደራችን ፈተና የበዛበት፣ ከፍ ያለው ዝቅ ይበል፤ ዝቅ ያለው ከፍ ይበል፤ የተጣመመው ቀጥ ይበል፤ ሰው ሁሉ የራሱን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ይመልከት ያለውን መለኮታዊ ኣስተምህሮ ወደ ጐን ስለ ተተወ ነው፤ በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችንና ልጆችዋ ካህናት እየተጐዱብን ነው፤ ለዚህም ያለ በቂ ምክንያት ከስራና ደመወዝ እየተፈናቀሉ እሮሮ የሚያሰሙ ካህናትና ሰራተኞች በርካታ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በተፈጸመው የማፈናቀል ክሥተት ከተጐዱ ካህናት መካከልም እስካሁን ዕንባቸው ያልታበሰ ብዙ ናቸው፤ ችግሩም ሲቆም አይታይም፤ በየጊዜው ባለሥልጣን ይነሣል፤ ባለሥልጣን ይተካል፤ ችግሩ ግን ከመባባስ በቀር ምንም ዓይነት መሻሻል ኣይታይበትም፤ ለምን እንደዚህ ሆነ ብለን ብንጠይቅ፣ ችግሩ የቤተ ክርስቲያን ሳይሆን፣ እኛው ራሳችን ፍትሕንና እኩልነትን ለማስፈን ቊርጠኝነቱን ስላጣን ነው የሚል መልስ ያመዝናል፤ ከዚህ ሌላ ምንም ዓይነት ኣመክንዮ ሊቀርብለት ኣይችልም፤
ስለሆነም ይህ ጉባኤ የችግሩን ኣሳሳቢነት ግምት ውስጥ በማስገባት ፍትሕንና እኩልነትን፣ ሥርዓትንና የሕግ የበላይነትን ያረጋገጠ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ አሰራር የሚያዋልድ ኣቅጣጫ መቀየስ ይኖርበታል፤ ወጣ ገባውና ኣንዱ በይ ሌላው የበይ ተመልካች የሚያደርገውን እንደዚሁም ሐዋርያዊ ተልእኮን ያላስቀደመ ልማዳዊ ኣሰራር ማረም አለብን፤ በምትኩም በቴክኖሎጂ ሲስተም የታገዘና ሁሉንም በፍትሕ ፊት እኩል ኣድርጎ የሚያስተናግድ ኣሰራር በዚህ ዓመት ማረጋገጥ ይኖርብናል፤ ስለሆነም ይህ ጉባኤ ለዚህ ትክክለኛና ችግር ፈቺ ውሳኔ እንዲሰጥበት በኣጽንዖት እናሳስባለን፡፡
በመጨረሻም
ከኣራቱ መዓዝነ ዓለም የመጣችሁ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎችና ተጠሪዎች የዘመኑን ፈተና ተቋቊማችሁ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝቡን በቅንነት ከማገልገላችሁም በላይ፣ ደጋ ወጥታችሁ፣ ቆላ ወርዳችሁ ያስገኛሁትን ውጤት በመያዝ በዚህ ጉባኤ መገኘታችሁን በኣድናቆት የምንመለከተውና ምስጋና የምንቸረው መሆኑን እየገለጽን እንኳን ደኅና መጣችሁ በማለት የሁለት ሺሕ ዓሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተከፈተ መሆኑን እናበስራለን፡፡
እግዚአብሔር መልካም ጉባኤ ያድርግልን
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን!!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘኣኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
ጥቅምት 3 ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም
አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/0322019.jpeg 323 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-10-14 01:04:102026-10-14 01:04:10መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
Search Search

Recent Posts

  • መልዕክተ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር
  • “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ።
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

Archives

  • October 2026
  • September 2026
  • August 2026
  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
  • Link to Facebook
Link to: የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት Link to: የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መልዕክት Link to: “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ። Link to: “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ሰርጎ ሊገባ አይገባም” ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አሳሰቡ። “የብሔርና የዘረኝነት ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top