የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም መንፈሳዊ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

July 19, 2026
ሐምሌ ፲፩ ቀን ፳፻፲ወ፰ ዓ.ም
በርካታ እውቅ ሊቃውንትን ያፈራውና በታሪክ ታላቅ ስፍራ ያለው የጥንታዊው የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም የመምህራንና ቀሳውስት ማሠልጠኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ያስተማራቸውን ደቀመዛሙርት የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በአሁኑ ሰዓት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ ታላቅ መርሐ-ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የገዳሙ የበላይ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች ታድመዋል።
ተመራቂዎቹ በገዳሙ የነበራቸውን የመንፈሳዊና የቀለም ትምህርት አጠናቀው ለዚህ ማዕረግ የበቁ ሲሆን፣ በዚህ ታላቅ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መርሐ ግብሩን በፀሎት ከፍተዋል።በመቀጠልም በገዳሙ አስተዳደር በሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ተ/ኃይማኖት ወልዱ ሪፖርት ቀርቧል።
በሪፖርቱም እንደተጠቀሰው ገዳሙ ከ1995 ጀምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርት ማፍራቱ ተገልጿል። በዚህም የማስተማር ሥራው በዓለማዊውም መድረክ ቢሆን ሀገር ከመምራት ጀምሮ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ ደቀ መዛሙርትን ያፈራ የሀገር ባለ ውለታ መሆኑን አንስተዋል።ገዳሙ በዛሬው የምረቃ መርሐ ግብርም 263 ተማሪዎችን ለምርቃት ያበቃ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 79 የአብነት ተማሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ በቅዳሜና እሑድ በመጽሐፍ ቅዱስ እና በሌሎች የትምህርት ዘርፎች የሚመረቁ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
አክለውም የገዳሙ ትምሕርት ቤት በኮሪደር ልማት ምክንያት የፈረሰ በመሆኑ አዲስ ለመሥራት በዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ተመራቂ ደቀመዛሙርት ወረብ ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የሠርተፊኬት አሳጣጥ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከናወን እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብራት ይከወኑበታል ተብሎ ይጠበቃል።
የሥነ-ሥርዓቱን አጠቃላይ ሂደትና ማጠቃለያ ዝርዝር መረጃ መርሐ-ግብሩ ከተጠናቀቀ በኋላ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/pr000041.jpeg 202 448 eotceth https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg eotceth2026-07-19 14:47:002026-07-19 14:47:00የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም መንፈሳዊ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
Search Search

Recent Posts

  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።
  • አሐዱ ባንክ ላደረገው ሁለተናዊ እገዛ በቋሚ ሲኖዶስ የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት።
  • የመቱ ፈለገ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዙር እጩ መምህራን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመረቀ

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለመንበረ ፓትርያርክና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዘመናዊ ኮምፒውተር በስጦታ አበረከተ። Link to: የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለመንበረ ፓትርያርክና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዘመናዊ ኮምፒውተር በስጦታ አበረከተ። የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለመንበረ... Link to: የቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲግሪ መርሐ ግብር እና በቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመረቀ። Link to: የቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲግሪ መርሐ ግብር እና በቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመረቀ። የቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲግሪ መርሐ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top