ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ምድሬዳዋ -ኢትዮጵያ
በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ያሳደሰውን የሀገረ ስብከቱን ጽሕፈት ቤትና በሀገረ ስብከቱ ወጪና የአዋጪነት ጥናት መሰረት በድሬዳዋ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊሊጶስ ቤተክርስቲያን በመገንባት ላይ የሚገኘውን የገበያ ማዕከል ጎብኝተዋል።
በተያያዘ ዜና ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የድሬዳዋ በመልካጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወከርሴማ ገዳም ሕጻናት ማሳደጊያ የሚኖሩ ዕጓለማውታ ሕጻናትንና በተቋሙ የተከናወኑ ልዩልዩ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።ሕጻናቱ በዕውቀትና በፈሪሐ እግዚአብሔር እናዲያድጉ በማድረግ ረገድም ተቋሙ እየሰራ ያለውን ሥራም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አድንቀዋል።
ለገዳሙ ማኅበረሰብዕም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ፣ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገ፣ረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች ተገኝተዋል።በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትምህርተ ወንጌልና ቃለ ምዕዳን ተሰጥቶ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።