የመርካቶ ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ተባርኮለአገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በ፲፰፻፺ወ፰ ዓ/ም በንጉሠ ነገሥት አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የተመሠረተውና ፻፲፰ ዓመታት ያስቆጠረው ሕንጻ ቤተመቅደስ በእድሜ ርዝመት ምክንያት በመጎዳቱ ምክንያት ለመንፈሳዊ አገልግሎት አመቺ በሆነ መንገድ እድሳት ተደርጎለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተባርኮ መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

አገር አቀፍ የስብከተ ወንጌል አልግሎትን ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሔደ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ አገር አቀፍ የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት በተጠና፣ተቋማዊ በሆነና ለውጥ ሊያመጣ በሚያስችል መልኩ ማከናወን የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላትና ከስባቱ ክፍላተ ከተማ ሥራ አስኪያጆችና የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊዎች ጋር ጥር ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር መድረክ አካሔደ።