የከሚሴ ደ/ቅ/ገብርኤልና ቅ/ሚካኤል ሰ/ጉባኤ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ይከታተሉ የነበሩ ተማሪዎችን አስመረቀ።
==========================

መስከረም 19/1/2017

በከሚሴ ሀ/ስብከት በአጥቢያዎች ወረዳ ቤተ ክህነት የከሚሴ ደ/ገ/ቅ/ገብርኤልና ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰ/ጉባኤ ከ1ኛ-3ኛ ክፍል አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎችን አስመረቀ።

በዚሁ የተማሪዎች ምርቃት የሀ/ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ደጀን ተስፋዬ እና የወረዳው ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅሊ/ካህናት ፍቅረ ማርያም እንዲሁም የሁለቱ አድባራት አስተዳዳሪ መ/ም/ልዑለ ቃል አሰፋ ተገኝተዋል።

የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መማር ማስተማር ላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ጉልህ አስተዋጽኦ ከማድረጋቸው በተጨማሪ በመምህርነት ሲያስተምሩ ለነበሩት
1ኛ.ለመ/ር ኢሳኢያስ አዳነ የደብሩ የስብከተ ወንጌል ክፍል
2ኛ.ለቀሲስ እንዳሻው ደምስ የሀ/ሰ/ቤቱ ሰብሳቢ
3ኛ.ለዲ/ን ሞላ ዘገየ የማህበረ ቅዱሳን ስራ አስፈጻሚ አባል
4ኛ.ለአቶ ክበበው ጸጋየ የምስጋና ስርተ ፍኬት ተበርክቷል።

በዚህ ስርዓተ ትምህርት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ክፍል ይማሩ የነበሩ የደረጃ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። በሽልማቱ ለደረጃ ከበቁት 9ኝ ተማሪዎች 8ቱ ሴቶቾ ሲሆኑ 1 ወንድ ተማሪ ነው።

በመጨረሻም የሰንበት ትምህርት ቤቱ ምክትል ሰብሳቢና የትምህርት ክፍል ኀላፊው ዲ/ን ኤርምያስ ተፈራ አጠቃላይ የመማር ማስተማሩ ሂደት ምን ይመስል እንደነበረና የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን ያካተተ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን በተለይ ብዙ ፈተናዎች ቢኖሩም የመማሪያ ምቹ ሁኔታ አለመኖር፣የፋይናንስ ችግር መኖር እና የወላጆች ክትትል ማነስን እንደችግር ጠቅሷል።

ከተመረቁት ተማሪዎች ውስጥ ሴት =94 ወንድ =49 ድምር =236 ተማሪዎች ናቸው
በቀጣይም በቅዱስ ሚካኤል ትምህርታቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ 135 ተማሪዎች በቅርብ ቀናት የምርቃት ፕሮግራም እንደሚደረግ ተነግሯል።

በመጨረሻም በሀ/ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በመልአከ ገነት ደጀን ተስፋየና በደብሩ አስተዳዳሪ መልእክት ተላልፎ መርሐ-ግብሩ በጸሎት ተዘግቶ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል ።

መረጃው የሀገረ ስብከቱ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው