ሐምሌ ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””””
ዱራሜ
**
ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የከንባታ፣ሐላባ፣ጠንባሮ፣
ዳውሮና ኮንታ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በከምባታ ሐላባና ጠምባሮ አህጉረ ስብከት በዱራሜ ከተማ በሚገኘው መንበረ ጵጵስና አ/ተ/ሃይል ማኖት ቤተክርስቲያን ሐምሌ ፲፫ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዐ ዓ/ም ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት ፳፬ ቀን ፳፻ ወ፮ ዓ.ም ባደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብፀዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የከምባታ ሐላባና ጠምባሮ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ በዛሬው እለት ወደ ሀገረ ስብከታቸው ተጉዘዋል። ይህንን ተከትሎም በዱራሜ ከተማ መንበረ ጵጵስና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በአቀባበል ሥነሥርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በሰሜን አሜሪካ የሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ሊ/ት እስክንድር ገብረክርስቶስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሕውብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ፣የሀገረ ስብከቱ የየክክሉ ኃላፊዎች፣ ተገኝተዋል።
በዚሁ የአቀባበል ሥነሥርዓት ላይ ቃለ ቡራኬ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በከምባትኛ ቋንቋ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ብፁዓን አባቶች ይሄንን ደግ ህዝብ ለማየት ስላበቃችሁ እድለኞች ናችሁ።እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ሀገረ ስብከቱን በሁለንተናዊ ልማት ተቀዳሚ ለማድረግ ሕዝበ ክርስቲያኑን በማስተባበር እንደሚሰሩ በመግለጽና ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና በማቅረብ አባታዊ መልዕኮታቸውን አጠቃለዋል።
በበዓሉ ላይ በብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን በሊቃውንተ ቤተከርስቲያንና በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ያሬዳዊ ዜማ ቀርቧል፤ሊቃውንትም ልዩለዩ ቅንያትን አቅርበዋል።በአቀባበል ሥነሥርዓቱ ላይ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሀሆኑ ምዕመናንና ወጣቶች ከከተማው ወጥተው በመኪና፣በባጃጅና በሞተር ብስክሌት በማጀብ ደማቅና በአይነቱ ልዩ የሆነ አቀባበል አድርገውላቸዋል።