መጋቢት ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
*******
አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
በቤቶችና ህንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት በኩል በተለምዶ አሮጌ ቄራ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ከሰባት ዓመታት በፊት በ480 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ B+ g+10 እንዲሁም በ፩ ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ባለ ዘጠኝ ወለል ህንጻዎችን ማስገንባት የጀመረች ቢሆንም የህንጻ ግንባታ ሥራዎቹ በልዩ ልዩ ምክንያቶች በመጓተታቸው ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ የግንባታ ሥራዎቹን ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ ድርጅቱ ጨረታ አውጥቶ ግንባታውን ለማከናወን ካሸነፉ ድርጅቶች ጋር ውል ተፈራርሟል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በህንጻዎቹ ግንባታ ዙሪያ የነበሩ ክፍተቶች በቤቶችና ህንጻዎች ቦርድ በተገቢው ሁኔታ እንዲጠኑ በማድረግ ችግሮቹ ከተለዩ በኋላ ግልጽ የሆነ የጨረታ ሒደት ተከናውኖ እንደተጠናቀቀ ዝርዝር የጨረታ ሒደቱ በቋሚ ሲኖዶስ ከጸደቀ በኋላ በዛሬው ዕለት አሸናፊ ድርጅቱ የቤቶችና ህንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ በተገኙበት የግንባታ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ሥራውን ቀግንባር ቀደምነት የሚያስተባብሩና የሚመሩት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ መዊዕ ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የበጀትና ሒሳብ መምሪያ ዋና ኃላፊ ወ/ሮ ጽጌሬዳ ዓለሙ ተገኝተዋል።