ልዩ ልዩ ጽ/ቤት
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ ቤት ራእይ
- በተከታታይ ዓመታት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ጸድቀው በሥራ ላይ እንዲውሉ የወጡትንና የሚወጡትን ዕቅዶች ተፈጻሚ ማድረግ ነው፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ዓላማ
- የብፁዕ ወቅዱስ ፓርያርክ የሚተላለፋትንና የሚሰጡትን መመሪያዎች ውሳኔዎች ወደ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማስተላለፍ፤
- የብፁዕ ወቅዱስ ፓርያርኩን ከበርካታ ሃይማኖታዊ ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፍዊ ጉዳዮች ጋር ድልድይ ሆኖ ማገናኘት፤
- የባለድርሻ አካትን ልዩ ልዩ ፍላጎቶችና ጥያቄዎችን እንዲሁም በይግባኝ የሚመጡ የተለያዩ ጉዳዮችን አመራር እንዲሰጥባቸው ወደ ቅዱስነታቸው ማቅረብ ፣
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዕሴት
– ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ በተዋረድ የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች ወደ ጽ/ቤቱ ለሥራ ጉዳይ ሲመጡ ምቹ ግልጽና ቀልጣፋ በሆነ አሠራር መስተንግዶ እንዲያገኙ በማድረግ ቤተክርስቲያን የሠጠቻቸውን ተልዕኮ እንዲወጡ ተገቢውን መድላድል መፍጠር፤
– የኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የሆኑት ማኅበረ ካህናት ወም እመናን በእምነታቸውና በተቀደሰ ባሕላቸው ጸንተው ይኖሩ ዘንድ ደረጃውን ጠብቀው የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎችና ፍላጐቶች ማሟላት ፤
– የነገይቱን ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ የሆኑት ወጣቶችና ጎልማሶች በመልካም ሥነ ምግባር ታንጸውና ተደራጅተው ሀገራቸውንና ቤተክርስቲያናቸውን እየጠበቁ እንዲኖሩ ያለውን አስቻይ ሁኔታዎችን አመቻችቶ መገኘትና ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሐዋርያዊ ተልዕኮ አፈጻጸም በልጅነት መንፈስ ወጣቶችም ሆኑ ጎልማሶች ሁለንተናዊ አለኝታ ሆነው እንዲኖሩ ማድረግ ናቸው