የአንጋፋው ጋዜጠኛ መጋቤ ምሥጢር ወልደሩፋኤል ፈታሒ ሁለተኛ ዓመት የሙት ዓመት መታሰቢያ ዛሬ ጷጉሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ፍትሐት ታስቦ ውሏል።
አንጋፋው ጋዜጠኛ መጋቤ ምሥጢር ወልደሩፋኤል ፈታሒ ቤተክርስቲያንን ከሃምሳ ዓመታት በላይ ያገለገሉ ባለ ቅኔ፣ታዋቂ ጸሐፊ፣ሐያሲና ደራሲ ነበሩ።
መጋቤ ምሥጢር ወልየሩፋኤል በሰላ ብዕራቸው የቤተክርስቲያንን አንድነት ለማጽናት፣አጽራረ ቤተክርስቲያንን ለማስታገስና ምዕመናን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የታነጹ መሆን እንዲችሉ እውቀታቸውን ተጠቅመው በርካታ ጽሑፎችን ያስነበቡ አንደበተ ርቱዕ ሰባኬ ወንጌልም ነበሩ።
መጋቤ ምሥጢር ወልደሩፋኤል በቤተክርስቲያናችን የሚስተዋሉ የአስተዳደር በደሎች እንዲስተካከሉ በጠንካራ ብዕራቸው አማካኝነት ሒሶችን በመስጠት አስተዳደሯ እንዲዘምንና ፍትሕ እንዲሰፍን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ አባትም ነበሩ።