ሰበር ዜና

ከቀኖናና ከህግ ውጪ በተደረገው ሲመት ከተሾሙት መካከል መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋዘአብ አዱኛ በዚህ ሰዓት ቤተክርስቲያንን ይቅርታ ለመጠየቅ ቅደለስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የይቅርታ ደብዳቤ አስገብተዋል።
በደብዳቤአቸውም ያሳደገቻቸውን፣ያስተማረቻቸውንና ለዚህ ክብር ያበቃቻቸውን ቤተክርስቲያን ማሳዘናቸውን ገልጸው ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።