ስብከተ ወንጌል

ራእይ፡-

  • የክርስቶን ወንጌል መንግሥት ለአማንያን ሁሉ ማዳረስ፣
  • ኢአማንያን  በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ተጠምቀው የእምነቱ  ተከታይ ሲሆኑ ማየት፣

ዓላማ፡-

  • የቤተ ክርስቲያኒቱ እምትና ሥርዓት በማያቋርጥ ሐዋርያዊ የወንጌል ተልዕኮ እስከ ዓለም ፍጻሜ ፀንቶ እንዲኖር ማድረግ፣
  • በዮሐንስ ወንጌል 21÷15 ‹‹ረዐይኬ አባግዕየ››በማት እግዚአብሔር አምላክ ለቅዱስ ጴጥሮስ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት፣
  • ምእምናንን መጠበቅና በእምት እንዲጸኑ  ማድረግ ፣
  • ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ፣ሕዝበ ክርስቲያኑን በሥነ ምግባርና  በሃይማኖት ማነጽ ለንሰሐ ማብቃት፣

ተልዕኮ፡-

  • ሰባክያነ ወንጌልን ማስጠንና ለሐዋርያዊ ተልዕኮ አብቅቶ ዓመቱን በሙሉ ትምህርተ ወንጌል ሳይቋረጥ ቅድስት ቤተክርስቲያኒቱ ባለችበት ሁሉ  እንዲሰጥ ማድረግ፣
  • በአህጉረ ስብከት ፣በወረዳና በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት ጉባኤዎችን በማዘጋጀት ትምህርተ ወንጌልን ለሁሉም ማደረስ፣
  • በጎ ፈቃድ ካላቸው ምእመናንና የቤተክርስቲያን አባቶች የበጀት ድጋፍ በመጠየቅ ሊዲያቆናት፣ለቀሳውስት ፣ለመዘምራንና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልጋዮች በስብከተ ወንጌል ዙሪ ግንዛቤያቸው እንዲሰፋ ሥልጠና መስጠት ፣
  • የስብከተ ወንጌል አገልግትን በአጭር ፣በመካከለኛና በረጅም ጊዜ በሚል ለይቶ ማቀድ፣ማደራጀት፣መፈጸምና ማስፈጸም፣
  • ሀገሩን የሚወድ ፣ ሰውን የሚያከብር በሥነ ምግባርና በኦርቶዶክሳዊ እምነት የተቀረጸ ትውልድ ማፍራት በቅንነት በታማኝነት መንፈሳዊ አገልግሎት ማበርከት፣

ግብ፡-

  • በ2015 ዓ.ም የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ በእቅዱ መሠረተ  የ1ኛ፣የ2ኛ እና 3ኛ ሩብ ዓመት ዝርዝር ተግባራትን በትጋት ማሳካት ነው፡፡
  • አገልጋዮም ሆነ ገተልጋዩ ህብረተሰብ ከቃል ባለፈ ምሳሌ የሆነ ሕይወት እንዲኖረው ማስቻል፡፡