ታኅሣሥ ፲ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
******
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን በሰበታ ጌተሴማኒ ገዳም በመገኘት የ፳፻ ፲ወ፭ዓ,ም የትንሣኤ በዓልን አከበሩ።
በዚሁ ጊዜ በገዳሙ የሚኖሩ ሕጻናት ለቅዱስነታቸው፣ ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ለሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ለደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ቤተ ክርስቲያን አቅፋና ደግፋ፣ሁሉን አሟልታ በሥነምግባር አንጻ እናንተን የምታሳድገው በትምህርታችሁ ጠንክራችሁ ወደ ፊት አገራችሁንና ቤተክርስቲያናችሁን እንድትጠቅሙ ስለሆነ በርትታችሁ ትምህርታችሁን ተከታተሉ ለገዳማዊያኑ እናቶቻችሁም በፍጹም ትህትና ታዘዙ በማለት ትምህርት ሰጥተዋል።
የገዳሙ እመ ምኔትና የገዳሙ መናንያን የገዳሙን ገቢ ለማሳደግ፣በግብርናና ግብርና ነክ በሆኑ ተግባራት ላይ በመሰማራት እንዲሁም በእደ ጥበብ ውጤቶች ዙሪያ የምታከናውኗቸው ውጤታማ ሥራዎችን በማጠናከርና በማስፋፋትም ተጨማሪ ሥራዎችን ለመሥራት ስለሚያስችላችሁ በርትታችሁ ሥሩ በማት ትምህርተ
ወንጌል ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል ።