ጥቅምት፩ ቀን ፳፻ ፲ ወ፮ ዓ.ም
****
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከነሐሴ ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን አሜሪካ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ዛሬ ማለዳ ዘደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም መመለሳቸው ይታወቃል።

የቅዱስ ፓትርያርኩን ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም መመለስን አስመልክቶ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለቅዱስነታቸው ክብር በሚመጥን መልኩ የተዘጋጀው መርሐ ግብር የተሳካና ውጤታማ መሆን ይችል ዘንድ የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታና የደብረ መድሐኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ሊቃውንትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ለመርሐ ግብሩ የሚመጥኑ ልዩልዩ ያሬዳዊ ዜማዎችን በማቅረብ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር አድርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ለቅዱስነታቸው፣ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ለክብር እንግዶች የምሳ መስተንግዶ በማቅረብ ከቅዱስ ፓትርያርኩ እና ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በረከትን ተቀብሏል።

ለዚህም የደብሩ አስተደዳዳሪ፣የደብሩ ዋና ጸሐፊ፣የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት፣የደብሩ አስተዳደር ሰራተኞች፣የደብሩ ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ላደረጋችሁት በልጅነት
መንፈስ መታዘዝና ላከናወናችሁት የተቀደሰ ተግባር በአጠቃላይ ለበዓሉ ድምቀትና ማማር ላበሰከታችሁት አስተዋጽኦ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቀባበል ኮሚቴ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።

የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን።