በሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ታህሳስ 19 የሚከበረው የመጋቤ ሐዲስ የቅዱስ ገብርኤልን በዓለ ንግሥ አስመልክቶ ለበዓሉ ድምቀት የእግር ጉዞ እንዲዘጋጅ የክልሉ መንግስት ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ባቀረበው ሀሳብ መሠረት የገዳሙ አስተዳደር ሀሳቡን በይሁንታ በመቀበል መ/ፀ/መ/ር/ቆ/አባ ኪዳነማርያም የገዳሙ አስተዳዳሪ፣ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ የሲዳማ ክልል ሰላም ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣ኮምሽነር ሽመልስ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣አቶ መኩሪያ መርሻዬ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ፣ኮማንደር መልካሙ አየለ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ፣የገዳማችን የሰበካ ጉባኤ አባላት፣የገዳሙ ካህናት፣የበዓል አዘጋጅ ዓቢይ ኮሚቴዎች እና የገዳማችን የሰ/ት/ቤት ዘማርያን በተገኙበት መነሻውን ከሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ያደረገ እስከ ፒያሳ ዳሽን ድረስ በዝማሬና በማርሽ ባንድ በመታጀብ እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ ለበዓሉ ከፍተኛ ድባብ የሆነ የእግር ጉዞ ተከናወነ።
መረጃው የገዳሙ ሕዝብ ግንኙነት ነው