++++++++++++++++++++++++++++
ጥር 4ቀን 2017ዓ.ም (ብሕንሳ ሚዲያ ሆሳዕና)
++++++++++++++++++++++++++++
በ2006 ዓ.ም የግንባታ ሥራው ተጀምሮ ከ11ዓመታት የግንባታ ሥራ በኃላ ሥራው ተጠናቆ ለምረቃ የበቃው በሚሻ ወረዳ ቤተክህነት በቦኮሙራ ቀበሌ የሚገኘው የዌራሞ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዩሐንስ ቤተክርስቲያን ጥር 4ቀን 2017 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ አባታዊ ቡራኬና መመርያ ሊቃነ ጳጳሳት ጸሎተ ቡራኬ ተመረቀ፡፡
በምረቃ ሥረሥርዓቱ ላይ የተገኙት ክቡር መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ የሀዲያና ስልጤ ሀገረስብከት ዋና ስራአስኪያጅ ባስተላለፉት መልዕክት በዛሬው ዕለት በዚህ ደብር የሥራ ኃላፊዎችና ካህናት የታየው አርአያነት ያለው የልማት ተግባር ያላችሁን መንፈሳዊ ጥንካሬና ክርስቲያናዊ አንድነት የሚያሳይ ነው፤ ካሉ በኋላ ወደፊትም በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ሊሰሩ የታሰቡና የቀሩ የልማት ሥራዎችን በማጠናቀቅ፣ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣የአብነት ትምህርት ቤትና የሰ/ት/ቤትን በማጠናከር እንደምትደግሙት አልጠራጠርም ብለዋል።
ይህን ቤተ ክርስቲያን የአካባቢውን ማኅበረሰብ በማስተባበር ለምረቃ እንዲበቃና ጥቂት የሚባሉ ሕዝበ ክርስቲያንን በማስተባበር ከአዲስ አበባ የተለያዩ ማሕበራትን ወደ አከባቢው እንዲመጡ በማድረግ እንዲሰራ ያደረጉት አቶ ጌታቸው ኢያሱ ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል ።
በመቀጠል ሕንጻ ቤተ መቅደሱ ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ የበኩላቸውን ለተወጣጡ ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ለሚገኙ የሰርተፍኬት እንዲሁም ልዩ ልዩ ሽልማት በክቡር ስራአስኪያጁ ተበርክቶላቸዋል
በምረቃ መርሐግብሩ ላይ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ፤ የወረዳ ቤተክህነት ስራአስኪያጆች፤ ከአዲስ አበባ የመጡ የተለያዩ ማሕበራት ፤ከሆሳዕናና አካባቢዋ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ማሕበረ ቅዱሳን የሆሳዕና ማዕከል አባላት፤ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተዋል።
በመጨረሻም ክቡር ስራአስኪያጁ የብፁዕነታቸውን የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት በማስተለለፍ በጸሎት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል ።
©የሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሚዲያ።