መጋቢት ፳፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””

መጋቢት ፳፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተከናወነው መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው በስምሪቱ ለሚሳተፉ አካላት መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡

በተለያዩ አካበባቢዎች የሚሠማሩት መምህራንም በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያን የገጠማትን ፈተና እንደ አንድ ግብዓት በመውሰድ ምዕመናን በሃይማታቸው ጸንተው ቤተ ክርስቲያንን እንዲጠብቁ፤ እንዲሁም በዕምነታቸው ምክንያት ችግር የገጠማቸው ምዕመናንን የማጽናናት ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲያከናውኑም አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡

በስምሪቱ ወቅት በትምህርት መልክ የሚሰጥ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን እና የቤተ ክርስቲያን ሚናን በተመለከተ የሥልጠና ማንዋል መዘጋጀቱንም የኮሚቴው አባላት ገልጸዋል፡፡
© EOTC TV