“ሩፋኤል ግሩም በመንፈስ ቅዱስ ኅቱም
መዓዛ ቅዳሴከ ጥዑም ከመ ጽጌ ገዳም
ነዓ ነዓ ማዕከሌነ ቁም
በበዓልከ ባርከነ ዮም።
ዚቅ ዘበዓለ ሩፋኤል ዘወርሐ ጳጉሜን
ጷጉሜን ፫ ፳፻፲፮ ዓ/ም
በምሥራቅ ሐረርጌ ሀ/ስብከት በሐረር ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ቅ/ሚካኤል ወቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ሢመት የንሥስ በዓል ብፁዕ አባታችን አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀ/ስብከት ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሀ/ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች የገዳማት እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ወምዕመናት በተገኙበት እየተከበረ እንዲሁም በብፁዕነታቸው የዕለቱን በዓል በተመለከተ ትምህርተ ወንጌል እየተከናወነ ይገኛል።
ዘገባው ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ነው።