ሰኔ ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
*****
ሰሜን አሜሪካን ኪንግ ጆርጅ ቨርጂኒያ
“””””””””””””””””””””””””””””””””””

በገዳሙ አማርኛ ቋንቋ ፣ግዕዝ፣ውዳሴ ማርያም፣ የቅዳሴ ትምህርት እና ሌሎችም ኮርሶች ይሰጣሉ።

በሰሜን አሜሪካን ቨርጂኒያ ግዛት ኪንግ ጆርጅ ካውንቲ የሚገኘው ዳግማዊ ደብረ ሊባኖስ ቅዱስ ያሬድና አቡነ ፊሊጶስ ገዳም አንድ መቶ ሃያ ተማሪዎችን በሁለት ዙር በመቀበል በልዩልዩ መንፈሳዊ ትምህርት ዘርፎች ማስተማር ጀመረ።

ገዳሙ በአማርኛ ቋንቋ፣በግዕዝ፣በውዳሴ ማርያም፣ በቅዳሴትምህርት፣በበገና፣በክራር፣በከበሮ፣በኮምፒዩተርና በቅዱሳት ሥዕላት አሳሳል ሥልቶች ዙሪያ ሥልጠናው የሚሰጥ ሲሆን በአብነት ትምህርት ዘርፍ አሉ የተባሉ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ትምህርቱን እንዲሰጡ በማድረግ ውጤታማ ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

አብነት ትምህርት ቤቱ በሰሜን አሜሪካን ከፍ ሲል በተጠቀሱ የትምህርት አይነቾች ትምህርት መስጠት በመጀመሩ ወላጆች በከፍተኛ ሁኔታ ደስታቸውን መግለጽ ገዳሙ በዚህ ጊዜ የአብነት ትምህርት መስጠት በመጀመሩ ልጆቻቸው ሃይማኖታቸውን እንዲያውቁ፣ ለሃይማኖታቸው ፍቅር እንዲኖራቸው፣ ከማድረግ ባለፈ ተተኪ ወጣት መምህራንና ምሁራንን ፨ሰሜን አሜሪካን ለማግኘት የሚያስችል በመሆኑ ደስታቸን እጥፍ ድርብ ነው ብለዋል።

አያይዘውም በሰለጠነው ዓለም ዙሪያ የተለያዩ ባህሎችን በምታስተናግደው አሜሪካን ልጆች ሃይማኖታቸውን፣ ወግና ሥርዓታቸውን አውቀው በሁሉም ዘርፍ የተዋጣለት ስብዕና የተላበሱ እንዲሆኑ ይህንን የመሰለ መንፈሳዊ ተቋም በእጅጉ እንደሚያስፈልግና አገልግሎቱን የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል ይቻል ዘንድ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የተማሪዎች ወላጆች በሰጡት አስተያጀት ጨምረው ገልጸዋል።

ገዳሙ በቀጥታ ከሚሰጠው የገጽ ለገጽ ትምህርት በተጨማሪ ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት የኦንላይን ትምህርት ለበርካታ ተማሪዎች በመስጠት ውጤት እያስመዘገበ የሚገኝ ሲሆን በአሌክሳንድሪያ በገዛው ዴይኬርና አካዳሚ ውስጥም በየሳምንቱ የመንፈሳዊ ትምህርት ከሰባ ለሚበልጡ ታዳጊዎች በመስጠት ቴክኖሎጂና እድገት በሚያስከትለው ጣጣ ልጆች ሃይማኖታቸውን ከማወቅ ውጪ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል።

ገዳሙ ወደፊት የመማሪያ ፣የመኝታና የመመገቢያ ክፍሎችን አጠቃሎ የያዘ ባለ ሁለት ወለል ሕንጻ በማስገንባት የአብነት ትምህርት ቤቱን ለማስፋፋትና በርካታ ተማሪዎችን በማፍራት በሰሜን አሜሪካን የስብከተወንጌልና የመንፈሳዊ አገሎግሎት እንዲስፋፋ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የገዳሙ ኃላፊ መልአከ ጥበባት አባ ገብርኤል ገልጸዋል።