በሸገር ሲቲ በፉሪ ክ/ከተማ04 ፓሊስ ጣቢያ ታስረው ከነበሩ እስረኞች መካከል ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑት መፈታታቸውን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር ገለጹ።

*******
የካቲት 10 ቀን 2015ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
******
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር በሸገር ሲቲ በ ፉሪ ከ/ከተማ 04 ፖሊስ ጣብያ የሚገኙ እስረኞችን ጠነቁ።ብፁነታቸው በፓሊስ ጣቢያው የሚገኙ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በእስር ቤቱ በመገኘት ከጠየቁና ካጽናኑ በኋላ ከሚመለከታ ቸው የአቃቤ ሕግና የፖሊስ ጣቢያው ኋላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል ። ከውይይቱ በኋላም ከአንድ መቶ ሃምሳ በላይ እስረኞች ተፈተዋል። ሲሉ ብፁዕነታቸው ገልጸውልናል።

ብፁዕነታቸው በጉብኝታቸው ወቅት ከአቃቤ ሕጉና ከፓሊስ ኃላፊዎች ለተደረገላቸው ግሩም የሆነ መስተንግዶና አቀባበል የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ምስጋናቸውን በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም አቅርበዋል።የቀሩትና በፓሊስ ጣቢያው ውስጥ የሚገኙ እስረኞችም በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚፈቱ ከአቃቤ ህጉና ከፓሊስ ኃላፊዎቹ ማረጋገጫ እንደተሰጣቸው ብፁዕነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።