በበረዶዋማ ፊንላንድ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የጥምቀት በዓልን በድምቀት አከበሩ።

የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን፣ ዛሬ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሰሱ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኘበት በድምቀት ተከሯል።

የበዓሉ ሥነ ሥርዓት የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሆኑት በመልአከ አሚን የተመራ ሲሆን፤ በዓሉን የተመለከ ትምህርት ከኢትዮጵያ በመጡት በዲያቆን ታደሰ ወርቁ ትምህርት ተሰጥቷል።

በፊንላንድ ተወልደው ያደጉ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት የጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ተተኪ መዘምራንም በዓሉን የሚያዘክር ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል።መረጃውን ያደረሱን መምህር ታደሰ ወርቁ ናቸው አፊንላንድ፤